TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ፈረሰኞቹ ወሳኝ ድል አስመዝግበዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

-የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግብ እስማኤል ኦሮ-አጎሮ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ኦሮ-አጎሮ በውድድር አመቱ አስራ ዘጠነኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

-አፄዎቹ በውድድር አመቱ ሰባተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን አርባ አምስት በማድረስ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

- ሽንፈት ያስተናገዱት ፋሲል ከነማዎች በበኩላቸው በሀያ ሰባት ነጥቦች #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ፋሲል ከነማ ከ ሀዋሳ ከተማ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ድል አድርጓል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ዲያጎ ጆታ 2x እና ሞሀመድ ሳላህ ሲያስቆጥሩ ለኖቲንግሃም ፎረስት ዊሊያምስ እና ጊብስ ዋይት ከመረብ አሳርፈዋል።

የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ በውድድር አመቱ አስራ ስድስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሊቨርፑል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀምሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ኖቲንግሃም ፎረስት በሀያ ሰባት ነጥብ አስራ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ዌስትሀም እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ብራይተን የሚገናኙ ይሆናል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሌስተር ሲቲ ሲያሸንፍ ኤቨርተን ከ ክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከ አስቶንቪላ ጋር ነጥብ ተጋርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የኢትዮጵያ ቡናን ሁለት ግቦች መሐመድ ኑር ናስር ሲያስቆጥር ለአዳማ ከተማ አድናን ረሻድ እና ደስታ ዮሀንስ ከመረብ አሳርፈዋል።

- የኢትዮጵያ ቡናው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ኑር ናስር በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል

- ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አዳማ ከተማ በተመሳሳይ ሰላሳ አንድ ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ሀይቆቹ በተከታታይ ያደረጓቸውን #አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም በሶስቱ ሲሸነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና በዚህ አመት በተመሳሳይ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው ስምንት አሸንፈው ሰባት ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀድያ ሆሳዕና በሰላሳ ሁለት ነጥቦች #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ በተመሳሳይ ሰላሳ ሁለት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- አዳማ ከተማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ ስድስት ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ሀዋሳ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድን ግቦች ሲሞን ፒተር 2x ሲያስቆጥር ለሀዋሳ ከተማ የአቻነት ግቦችን ሰዒድ ሀሳን 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ መድኑ የፊት መስመር ተጨዋች ሲሞን ፒተር በውድድር አመቱ ስድስተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ በሰላሳ አራት ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከ መቻል ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ድል አድርጓል !

በአምስተኛ ሳምንት የጀርመን ቡንደስሊጋ የ2023/24 የውድድር አመት ባየር ሙኒክ ከቦቹም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 7ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የባየር ሙኒክን የማሸነፊያ ግቦች ሀሪ ኬን ( 3x ) ቺፖ ሞቲንግ ፣ ዴሊት ፣ ሌሮይ ሳኔ እና ቴል ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን በአምስት የጀርመን ቡንደስሊጋ ጨዋታዎች #ሰባተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ሀሪ ኬን በባየር ሙኒክ ማልያ የመጀመሪያ ሀትሪኩንም መስራት ችሏል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ :- ባየር ሙኒክ ( 1️⃣3️⃣ ነጥብ )

1️⃣4️⃣ኛ :- ቦቹም ( 3️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ባየር ሙኒክ ከ ሌፕዚግ

ቅዳሜ - ቦቹም ከ ሞንቼግላድባህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

በአስራ ስድስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከበርንማውዝ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የበርንማውዝን የማሸነፊያ ግቦ ሶላንኬ ፣ ቢሊንግ እና ሴሌሲ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት የሊቨርፑል ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን #ሰባተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

6️⃣ኛ :- ማንችስተር ዩናይትድ ( 2️⃣7️⃣ ነጥብ )

1️⃣3️⃣ኛ :- በርንማውዝ ( 1️⃣9️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ዕሁድ - ሊቨርፑል ከ ማንችስተር ዩናይትድ

ቅዳሜ - በርንማውዝ ከ ሉተን ታውን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃቸውን ማሻሻል ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች አብዲሳ ጀማል እና ምንተስኖት ከበደ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ያለፉትን አስር ጨዋታዎች ያልተሸነፈው ኢትዮጵያ መድን #ሰባተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን ባለፉት ስባት ጨዋታዎች አስራ ዘጠኝ ግቦችን በተጋጣሚ መረብ ላይ ሲያስቆጥር የተቆጠረበት ሁለት ግብ ብቻ ነው

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

9️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 37 ነጥብ

1️⃣5️⃣ ሻሸመኔ ከተማ :- 14 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

- ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ቡና

- ሻሸመኔ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲሞን ባይልስ ሶስተኛ ወርቅ ሜዳልያዋን አሳካች !

ታሪካዊቷ አሜሪካዊ የጂምናስቲክ ተወዳዳሪ ሲሞን ባይልስ ሶስተኛውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያዋን በጂምናስቲክ ውድድር ማሳካት ችላለች።

የ 27ዓመቷ የጂምናስቲክ ተወዳዳሪ ሲሞን ባይልስ በኦሎምፒክ ውድድር ታሪክ #ሰባተኛ የወርቅ ሜዳልያዋን ማስመዝገብም ችላለች።

ሲሞን ባይልስ አጠቃላይ በኦሎምፒክ ውድድር አስር ሜዳልያዎችን በማሳካት ስኬታማዋ አሜሪካዊ የጂምናስቲክ ተወዳዳሪ በመሆን ባለታሪክ ሆናለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe