TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
27 ' ማንችስተር ሲቲ 2-1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን ሳንቾ

14 ' ማንችስተር ሲቲ 1-0 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን

√ ኬቨን ዴ ብሩይን ለማንችስተር ሲቲ #ሀምሳ አንደኛ የ ፕርሚየር ሊግ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል ።

√ ዴ ብሩይን በተጨማሪም በ ፕርሚየር ሊጉ #ሰማንያ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#PremierLeague🇬🇧

ማንችስተር ሲቲ 4 - 0 ማንችስተር ዩናይትድ

ፊል ፎደን
ኤርሊንግ ሀላንድ

√ ኤርሊንግ ሀላንድ ለሲቲ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ አስራ ስድስት ከፍ አድርጓል።

√ ማንችስተር ሲቲ አስቀድሞ ግብ ባስቆጠሩበት ያለፉት ሰላሳ አምስት #የሊጉ ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

√ ፊል ፎደን የመጀመሪያ የማንችስተር ደርቢ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

√ ፊል ፎደን በስምንት የሊጉ ጨዋታዎች በስድስት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል።

√ ኤርሊንግ ሀላንድ ለሲቲ በፕርሚየር ሊጉ አስራ ሶስተኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

√ ፊል ፎደን ለማንችስተር ሲቲ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ #ሀምሳ ማሳደግ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ ማን ይሆናል ? አስራ ስድስተኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አሁንም ፉክክሩ ለተመልካች አዝናኝ ሆኖ መርሐ ግብሮቹ በመካሄድ ላይ ይገኛሉ። ለኮከብ ግብ አግቢነት በሚደረገው ፍልሚያ የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በሀያ ጎሎች በበላይነት እየመራ ይገኛል። ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ማን ያጠናቅቃል ? 1. ኤርሊንግ ሀላንድ :- 20 ጎሎች 2. ሀሪ…
ሀላንድ ምን ያህል ጎሎችን ያስቆጥራል ?

ኖርዌያዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጫዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በፕርሚየር ሊጉ በርካታ ሪከርዶችን የግሉ ማድረግ ሲችል ከወዲሁ ሀያ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ " አሁን ባለው " ወቅታዊ የግብ አስቆጣሪነቱ የሚቀጥል ከሆነ በዓመቱ መጨረሻ #ሀምሳ #የሊግ ጎሎችን ሊያስቆጠር እንደሚችል ተገልጿል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በሊጉ ምን ያህል ጎል ያስቆጥራል ብለው ያስባሉ?

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ጆሴፍ ዊሎክ እና ካሉም ዊልሰን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኒውካስል ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን #ሀምሳ በማድረስ ማንችስተር ዩናይትድን በግብ ክፍያ በመብለጥ #ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ማንችስተር ዩናይትድ በበኩላቸው መሸነፋቸውን ተከትሎ በሀምሳ ነጥብ በኒውካስል ዩናይትድ በግብ ክፍያ ተበልጠው አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ከ ዌስትሀም ዩናይትድ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | አስቶን ቪላ 3-0 ኒውካስል ዩናይትድ

ራምሴይ
ዋትኪንስ

- በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመሩት አስቶን ቪላዎች በሊጉ ተከታታይ #አምስተኛ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

- የአሰልጣኝ ኤዲ ሆው ስብስብ ኒውካስል ዩናይትድ ከአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግደዋል።

- አስቶን ቪላ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን #ሀምሳ በማድረስ #ስድስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- ኒውካስል ዩናይትድ በሀምሳ ስድስት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባህርዳር ከተማ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባህርዳር ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አደም አባስ ተቀይሮ በመግባት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ባህርዳር ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን #ሀምሳ በማድረስ አንድ ጨዋታ ከሚቀረው የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አንድ ማጥበብ ችሏል።

አዳማ ከተማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ናስር ድል አድርጓል !

በሳውዲ አረቢያ ሊግ እስረኛ ሳምንት መርሐ ግብር የክርስቲያኖ ሮናልዶው ክለብ አል ናስር ከዳማክ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ታሊስካ የአል ናስርን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 #ሀምሳ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

- ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባላንዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከየትኛውም ተጨዋች በበለጠ በ2023 አርባ አንድ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

- አል ናስር በሊጉ ሀያ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአስራ አንድ ግቦች የሳውዲ አረቢያ ሮሸን ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃን በመምራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮናልዶ በግብ አግቢነቱ ቀጥሏል !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ከአል ሸባብ ጋር ያደረገውን የሳውዲ ኪንግስ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ 5ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

የአል ናስርን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ሲዲዮ ማኔ ፣ ፎፋና ፣ ማራን እና ጋሬብ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ለአል ናስር ሀያ ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 ያስቆጠራቸውን ግቦች #ሀምሳ ማድረስ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሊቨርኩሰን ባለመሸነፍ ጉዞው ቀጥሏል !

የጀርመን ቡንደስሊጋ ዋንጫ አሸናፊው ባየር ሊቨርኩሰን ከቦህም ጋር ያደረገውን የሰላሳ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 5ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባየር ሊቨርኩሰንን የማሸነፊያ ግቦች ፓትሪክ ሺክ ፣ ቦንፌስ ፣ አሚን አድሊ ፣ ግሪማልዶ እና ስታንሲች ከመረብ አሳርፈዋል።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ባየር ሊቨርኩሰን በዘንድሮው የውድድር ዘመን ካደረጋቸው ሰላሳ ሶስት የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ሀያ ሰባቱን ሲያሸንፍ በስድስቱ አቻ ተለያይተዋል።

ባየር ሊቨርኩሰን በዘንድሮው የውድድር አመት ያደረጋቸውን ያለፉት #ሀምሳ ጨዋታዎች ሳይሸነፍ መጓዙን ቀጥሏል።

ባየር ሊቨርኩሰን በቀጣይ የመጨረሻ የሊግ ጨዋታውን ከኦግስበርግ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe