TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
TIKVAH-SPORT
አርሰናል የተጫዋቹን ውል በይፋ አራዘመ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የጃፓናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋ ታኬሂሮ ቶሚያሱ ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል። የ 25ዓመቱ ጃፓናዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ታኬሂሮ ቶሚያሱ በመድፈኞቹ ቤት እስከ 2026 የሚያቆየውን ውል መፈረሙ ተገልጿል። ከሶስት አመታት በፊት ከቦሎኛ አርሰናልን የተቀላቀለው ተጨዋቹ በቆይታቸውም በሁሉም ውድድሮች…
" ለአርሰናል መጫወት ህልሜ ነው " ቶሚያሱ

በመድፈኞቹ ቤት ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት ውሉን ያራዘመው ጃፓናዊው ተከላካይ ታኬሂሮ ቶሚያሱ ለአርሰናል መጫወት ህልሙ መሆኑን ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

" እዚህ ለመቆየት ውሌን በማራዘሜ በጣም ደስተኛ ነኝ " ሲል የተደመጠው ታኬሂሮ ቶሚያሱ አርሰናል ከአለማችን ምርጥ ክለቦች አንዱ ነው እዚ መጫወት ህልሜ ነው ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ የመጨረሻ ልምምዳቸውን ሰርተዋል !

በቀጣይ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያሉበት የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ረፋድ ጨዋታውን በሚያደርግበት አዲስ አበባ ስታዲየም መስራት ችሏል።

ብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን ከ3:00 እስከ 4:30 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሰራ ሲሆን በልምምድ ወቅት ሁሉም ተጨዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በልምምዱ ላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳኛቸው ንገሩ እንዲሁም ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የስነ ልቦና ባለሞያ ማግኘቴ ጠቅሞኛል " ሪቻርልሰን

ብራዚላዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ሪቻርልሰን የስነ ልቦና ባለሞያ እርዳታ ማግኘቱ ትልቅ ጥቅም እያስገኘለት እንደሚገኝ ገልጿል።

ሪቻርልሰን ከወራቶች በፊት የስነ ልቦና ባለሞያ ማግኘት እንደሚፈልግ ገልፆ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ጥቅም እንዳገኘበት እና ሌሎች ተጨዋቾች እገዛ ቢያገኙ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ መክሯል።

" አሁን ላይ የስነ ልቦና ባለሞያ አለኝ ለተጨዋቾች አስፈላጊ ነገር ነው " የሚለው ሪቻርልሰን በየሳምንቱ ከባለሞያ ጋር ቀጠሮ አለኝ በጣም ጠቅሞኛል ብሏል።

ሌሎች ተጨዋቾች የስነ ልቦና ባለሞያ ጠቃሚ መሆኑን መረዳት እንዳለባቸው የጠቆመው ሪቻርልሰን " አንድ ጊዜ ቢጀምሩ ምን እንደምል ይገባቸዋል ሜዳ ውስጥ ትልቅ ጥቅም አለው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ምርጥ ተጨዋች ለማድሪድ መጫወት አለበት " ካርቫል

ስፔናዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የመስመር ተጨዋች ዳኒ ካርቫል ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ወደ ሪያል ማድሪድ መዘዋወር እንዳለበት ተናግሯል።

" ምርጥ ተጨዋቾች ሀሉ ለሪያል ማድሪድ ግዴታ መጫወት አለባቸው " የሚለው ዳኒ ካርቫል ኪሊያን ምባፔ ደግሞ ከእነሱ አንዱ ነው ስለዚህ በአመቱ መጨረሻ የሚመጣበት እድል አለ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በመዲናችን አይን ቦታ ከቦሌ በ7ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ለቡ መብራት በተንጣለለው 65,395ካሬ ላይ ያረፈ ሠፊ መንደር፤ 5  የመዋኛ ገንዳወች፣ የከርሰምድር ውሀ፣ የልጆች መጫወቻ፣ አረንጓዴ ስፍራወችን እያንዳንዱ ህንጻወች 5 ቤዝመንት፣ ሠፊ ሰገነት፣ 5 ሊፍቶች ያላቸው፣ 50% ባንክ የተመቻቸለት፤

እጅግ ዘመናዊ በሆነው የግንባታ መሳሪያ በኮንካል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከእስቱዲዎ እስከ ባለ 4መኝታ ድረስ እንዲሁም የንግድ ሱቆችን በማራኪ ዲዛይንና በላቀ ጥራት የተዘጋጁ፤

እስከ 25% የዋጋ ቅናሽ (6,000,000ብር)
10% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ
ማለትም  ስትድዮ 👉56.6ካሬ=605,000ብር
    
አንድ መኝታ
    👉77.7ካሬ,=831,000ብር
ሁለት መኝታ
     👉123.3ካሬ=1,318,000ብር
ሶስት መኝታ
    👉146.8ካሬ=1,570,000ብር
አራት መኝታ
      👉186.9ካሬ=1,998,000ብር
ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ
ልብ ይበሉ አንድ ቤት ሲገዙ አንድ ቤት በነፃ አለው።

ለበለጠ  መረጃ  
💚በ+251988887999
       +251918642895
     ሀሎ      ይበሉ።
https://t.iss.one/Engineergashaw
🇪🇹 Sport, Peace, Unity, and Partnership! 🇪🇹

WANAW SPORT - Proud Partner of the 2024 AAU Sport Festival!

💪🏾 When there's competition, there's #WANAW! 💪🏾

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ቀጥሯል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የቀድሞ የበርንማውዝ ሀላፊ ሪቻርድ ሂውዝን የክለቡ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የቀድሞ የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ማይክል ኤድዋርድስ ወደ ሊቨርፑል በከፍተኛ ሀላፊነት መመለሱን ተከትሎ ክለቡን የተቀላቀለው ሪቻርድ ሂውዝ በአመቱ መጨረሻ ስራውን እንደሚጀመር ተገልጿል።

" ይህንን እድል በማግኘቴ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል ሊቨርፑል ልዩ የሆነ ክለብ ነው በዚህ ሀላፊነት እንዳገለግል እድሉ ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ።"ሲል ሪቻርድ ሂውዝ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሁሉም ጋርዲዮላን መሆን ይፈልጋል " ብሩኖ ፈርናንዴዝ

የማንችስተር ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአለምን እግር ኳስ መቀየር መቻሉን ገልጿል።

" አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአለምን እግር ኳስ ቀይሯል " የሚለው ብሩኖ ፈርናንዴዝ አሁን ላይ ሁሉም ፔፕ ጋርዲዮላን መሆን ይፈልጋል መደበቅ አያስፈልግም።"ብሏል።

ማንችስተር ሲቲ ባለው ውጤት እና ስኬት ምክንያት ሁሉም ክለቦች እንደ እነሱ ለመጫወት ይሞክራሉ ሲል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

ሀያ ዘጠነኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የ 2023/24 የውድድር ዘመን የስፔን ላሊጋ የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ቪኒሰስ ጁኒየር ፣ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ፣ ብራይስ ሜንዴዝ ፣ ሶርሎት እና ጉሩዜታ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

የወሩ ምርጥ ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ?

የ 2023/24 የውድድር ዘመን የስፔን ላሊጋ የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ #ሶስት እጩ አሰልጣኞች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት የሊጉ መሪ ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ፣ የባርሴሎናው አሰልጣኝ ዣቪ እና የቪያሪያሉ አሰልጣኝ ማርሴሊኖ ጋርሺያ በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

አሰልጣኞቹ በወሩ ውስጥ ከክለባቸው ጋር ያላቸው ቁጥር ምን ይመስላል ?

- አሰልጣኝ ማርሴሊኖ ጋርሺያ :- በወሩ ውስጥ ያደረጓቸውን ሶስት ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

- አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ :- ካደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ውስጥ ሁለቱን አሸንፈው በአንዱ አቻ ተለያዩ።

- አሰልጣኝ ዣቪ :- ካደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ውስጥ ሁለቱን አሸንፈው በአንዱ አቻ ወጥተዋል።

የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ነው ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኔይማር አባት የዳኒ አልቬዝን የዋስ ገንዘብ ይከፍላል !

ብራዚላዊው የቀድሞ የባርሴሎና ተጨዋች ዳኒ አልቬዝ በጊዜያዊነት በአንድ ሚልዮን ዩሮ ገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤት እንደተወሰነለት ተገልጿል።

የዋስትና አንድ ሚልዮን ዩሮ ገንዘቡን የብራዚላዊው የቀድሞ የቡድን አጋሩ ኔይማር ቤተሰቦች እንደሚከፍሉለት ተነግሯል።

ኔይማር በቅርቡ ዳኒ አልቬዝ ለተጎጂ ቤተሰቦች እንዲከፍል የተወሰነበትን 150,000 ዩሮ ከፍሎለት እንደነበር ይታወቃል።

ዳኒ አልቬዝ በፆታዊ ጥቃት ተከሶ ለስድስት ወራት በእስር ቤት ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን በቅርቡ የአራት አመት ከስድስት ወር እስር እንደተፈረደበት አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማኑኤል ኑዌር ጉዳት አጋጠመው !

ጀርመናዊው የባየር ሙኒክ ግብ ጠባቂ ማኑኤል ኑዌር በዛሬው ዕለት በነበረው የብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ ላይ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ማኑኤል ኑዌር ጀርመን በቀጣይ ቀናት ከኔዘርላንድ እና ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የምታደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያመልጡት ተነግሯል።

ማኑኤል ኑዌር የብሔራዊ ቡድኑን ስብስብ በመልቀቅ ወደ ክለቡ ባየር ሙኒክ እንደሚመለስ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው! እንዳያመልጥዎ!
Wales - Finland
Greece - Kazakhstan
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!