#update በግብጽ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ ከተጀመረ 13 ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን ወደቀጣዩ ዙር ያለፉት 16 ሃገራት ተለይተው ታውቀዋል።
ከምድብ ሀ አዘጋጇ ግብጽ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎና ዩጋንዳ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በምድ ለ ደግሞ ናይጄሪያ፣ ጊኒና ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈቸው ማደጋስካር አልፈዋል።
በምድብ ሐ ሴኔጋል እና አልጄሪያ፤ በምድብ መ ሞሮኮ፣ አይቮሪ ኮስትና ደቡብ አፍሪካ ምርጥ 16ቱን የተቀላቀሉ ሲሆን በምድብ ሠ ቱኒዚያና ማሊ እንዲሁም በምድብ ረ ካሜሩን፣ ጋናና ቤኒን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
በዚህም መሰረት ከመጪው አርብ ጀምሮ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ሞሮኮ ከቤኒን
ዩጋንዳ ከሴኔጋል
ግብጽ ከደቡብ አፍሪካ
ማደጋስካር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ
ናይጄሪያ ከካሜሩን
አልጄሪያ ከጊኒ
ማሊ ከአይቮሮ ኮስት
ጋና ከቱኒዚያ የሚጠበቁ ጨዋታዎች ናቸው።
Via #bbc
@tikvahethsport

ፍራንክ ላምፓርድ የቼልሲ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
--------------------------------------------------
የቀድሞ የቼልሲው አማካይ ፍራንክ ላምፓርድ የቀድሞ ክለቡን ለማሰልጠን የሶስት ዓመታት ውል ፈርሟል።
13 ዓመታትን በቼልሲ ቤት ያሳለፈው ላምፓርድ ከክለቡ ጋር 13 ዋንጫዎችን አንስቷል።
አዲሱ የሰማያዊዮቹ አለቃ “ወደ ቀድሞ ክለቤ አሰልጣኝ ሆኜ በመመለሴ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል” ያለ ሲሆን፤ “ለክለቡ ያለኝን ፍቅር ሁሉም ይረዳዋል። አሁን ትኩረቴን በቀጣዩ የውድድር ዘመን ላይ ማድረግ ነው የምፈልገው” ሲል ላምፓርድ ተናግሯል።
ደርቢ ካውንቲን ሲያሰለጥን የነበረው ላምፓርድ ወደ ጁቬንቱስ ያመሩትን ማውሪሲዮ ሳሪን በመተካት ቼልሲን የማሰልጣን ኃላፊነትን ተረክቧል።
Via #BBC

የእገዳ ውሳኔ አልተላለፈም...
የኢትዮጵያ የማራቶን ውድድር ሯጮች ላይ ምንም አይነት የእገዳ ውሳኔ እንዳልተላለፈ ከአትሌቶቹ ጋር ካታር የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክትር ዱቤ ጂሎ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌቶች ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት እረፍት አድርገው እንዲያገግሙ እንጂ እገዳ አለመሆኑን ገልጸዋል።
ውሳኔው ከ42 ኪሎሜትሮች በላይ በሚሮጥበት ከባድ በሚባለው የማራቶን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሯጮችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰድ ተቀባይነት ያለው እረፍት ነው ብለዋል ዱቤ ጅሎ።
አትሌቶች የሦስት ወራት የማገገሚያ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ በዓለም አቀፍ የውድድር ሕግና ደንብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውና በሌሎችም ሃገራት የሚሰራበት እንደሆነ አመልክተዋል።
Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ኢትዮጵያዊው በ1500 ማጣሪያ ላይ ተጠልፎ ከወደቀ በሗላ ይግባኝ ጠይቆ ወደቀጣይ ዙር አለፈ!!!!!
ካታር እየተካሄደ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር በመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያዊው ታደሰ ለሚ ተጠልፎ በመውደቁ ማጣሪያውን ሳያልፍ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም በክስተቱ ላይ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት አግኝቶ ወደቀጣይ ዙር ለማለፍ ችሏል::
ታደሰ ለሚ (ፎቶ) በማጣሪያው ውድድር ላይ ተጠልፎ ከወደቀ በሗላ ከወደቀበት ተነስቶ ሩጫውን ቢያጠናቀቅም ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚያስችለውን ሰዓት ማስመዝገብ ሳይችል ቀርቶ ነበር::
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር የሆኑት ዱቤ ጂሎ ዶሃ ላይ ለቢቢሲ ዘጋቢ እንደገለጹት ስለክስተቱ ለውድድሩ አዘጋጆች ይግባኝ እንደሚያቀርቡ ተናግረው የነበረ ሲሆን የቀረበው ቅሬታ ተገቢ በመሆኑ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል::
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሳሙኤል ተፈራ ግን ተፈላጊውን ሰዓት በማስመዝገቡ ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍ ችሏል::
የዚህ ውድድር ቀጣይ ማጣሪያ ዛሬ ምሽት 2:20 ላይ የሚደረግ ሲሆንሁለት ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊ ይሆናሉ::
Via #BBC
@tikvahethsport @kidusyoftahe @GoitomH

ዲድየር ድሮግባ እና ሳሙኤል ኤቶ ዘረኝነትን አውግዘዋል !
ሁለት የፈረንሳይ ዶክተሮች በቴሌቪዥን ላይ በነበረ ውይይት የኮሮናቫይረስ የሙከራ ክትባት መጀመሪያ በአፍሪካ ሊሞከር ይገባል ማለታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ውግዘትን እያስተናገዱ ሲሆን፤ ታዋቂዎቹ አፍሪካውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ዲዲየር ድሮግባና ሳሙኤል ኤቶም የሰላ ትችታቸውን ሰንዝረዋል።
"አፍሪካ መሞከሪያ ላብራቶሪ አይደለችም፤ አፍሪካውያንም የላብራቶሪ አይጦች አይደለንም" በማለት ድሮግባ በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።
የቀድሞው የካሜሮን እግር ኳስ ተጫዋች ሳሙኤል ኤቶ በበኩሉ ዶክተሮቹን "ነፍሰ ገዳይ" ብሏቸዋል።
VIA #BBC
@tikvahethsport @kidusyoftahe

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BiniyamGirmay🇪🇷
ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ስፍራ የሚሰጠውን ቱር ደ ፍራንስ የተሰኘውን የፈረንሳዩን የብስክሌት ውድድር ‘ስቴጅ 3’ በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ በመሆን ለኤርትራ እና ለአፍሪካ ታሪክ ሰርቷል።
ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የውድድሩ ተሳታፊዎች ወደ ቢኒያም በመሄድ " እንኳን ደስ አለህ ! አንተ በጣም ምርጡ ነበርክ ፤ በጣምም ጠንካራ ነህ፤ ለአፍሪካ እና ለዓለም ታሪክ ሰርተሃል ፤ እንኮራብሃለን " ሲሉ አወድሰውታል።
ቢኒያም ፤ " ሁሉንም ጥንካሬ እና ድጋፍ ስለሰጠኝ ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን " ሲል ተናግሯል።
ኤርትራዊው ቢኒያም በተለያዩ ጊዜያት ባስመዘገበው ስኬት " የአፍሪካ የብስክሌት ንጉሥ " የሚል ስም ተሰጥቶታል።
ኤርትራውያን በተለይ በብስክሌት ግልቢያ በዓለም መድረክ በእጅጉ ይታወቃሉ።
#Eritrea
#NBC_Sport
#BBC
@tikvahethiopia