TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#AddisAbabaCityCup

የ መጨረሻ ተፋላሚዎቹን ለመለየት ከ ጫፍ የደረሰው የ ዘንድሮው የ ሲቲ ካፕ ውድድር ለ አሸናፊው የሚሰጠው ልዩ ዋንጫ ይፋ ሆኗል ።

አንድ ሜትር ከ አስር ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ይህ ዋንጫ ዛሬ ከ ጀርመን ሀገር የ ውድድሩ አዘጋጅ በሆነው ሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽን ጋር ድርሷል ።

የ 15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ የ ዋንጫ ባለቤት ከሚሆነው በተጨማሪም ለ #ደረጃ ተፋላሚ እና ለ ፀባይ ዋንጫ አሸናፊ ተጨማሪ ሽልማት ይኖራል ።

የ ወርቅ ፣ብር እና ነሀስ ሜዳሊያዎችም ዛሬ ከ ጀርመን ሀገር ሲገባ ተሳታፊ ቡድኖች እንደ ደረጃቸው የ ገንዘብ ሽልማታቸውም እንደተጠበቀ ነው ።

የዚህ ልዩ ዋንጫ ባለቤት ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹

ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በሚጀምረው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አዳዲስ ነገሮች ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ከእነዚህም መካከል :-

- ከ 800 ሜትር በላይ ባሉ የማጣሪያ ውድድሮች ቀጣዩን ዙር የሚቀላቀሉ አትሌቶች የሚለዩት ከሁሉም የውድድር ምድቦች በሚያስመዘግቡት ደረጃ #ብቻ ሆኗል።

- የውድድሩ አሸናፊ አትሌት አሰልጣኞች በተመሳሳይ የሜዳሊያ ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል።

- የ1,500ሜትር ፣ 3,000መሰናክል እና 5,000 ሜትር ማጣሪያ ተወዳዳሪዎች ቀጣዩን ዙር የሚቀላቀሉት በሚያስመዘግቡት #ደረጃ ብቻ ይሆናል።

- ይህም ከዚህ ቀደም በነበሩ የዓለም ሻምፒዮናዎች ላይ የተሻለ ሰዓት ያላቸው አትሌቶች ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፈውን አሰራር #ያስቀረ ሆኗል።

የአዲሱ ህግ ሙሉ መረጃ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe