TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
የጨዋታ አሰላለፍ !

11:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ዎልቭስ

11:00 ቼልሲ ከ ኖቲንግሀም ፎረስት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ሊድስ ዩናይትድ 2-2 ኒውካስል ዩናይትድ

አይሊንግ ካሉም ዊልሰን
ክሪስቴንሰን

- የኒውካስል ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ካሉም ዊልሰን በውድድር አመቱ አስራ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- የአሰልጣኝ ኤዲ ሆው ቡድን ኒውካስል ዩናይትድ በስልሳ ስድስት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- ሊድስ ዩናይትድ በሰላሳ አንድ ነጥቦች በወራጅ ቀጠናው አስራ ስምንተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቫራን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል ያውቃል "

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ከደቂቃዎች በኋላ ከሚጀምረው ጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት ቀላል የሚባል ጨዋታ እንደሌለ ተናግረዋል።

" ቫራን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል ያውቃል ቡድኑን በማገዝ ለድል ያበቃል ፣ እሱ አዚህ ብቻ ሳይሆን ለሀገሩ እና ለሪያል ማድሪድም ትልቅ አገልግሎት ሰጥቷል ዋንጫ እንዴት እንደሚመጣ ያውቃል።

ቀላል የሚባል ጨዋታ እንደሌለ ሁሉም ሰው ሊያውቅ ይገባል ጨዋታውን ለማሸነፍ ሁሉንም ነገር መስጠት አለብን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
13' ማንችስተር ዩናይትድ 0-0 ዎልቭስ

13' ቼልሲ 0-1 ኖቲንግሀም ፎረስት

አዎኒዪ

13' አስቶን ቪላ 1-0 ቶተንሀም

ራምሴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
32' ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ዎልቭስ

ማርሻል

32' ቼልሲ 0-1 ኖቲንግሀም ፎረስት

                አዎኒዪ

32' አስቶን ቪላ 1-0 ቶተንሀም

     ራምሴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ዎልቭስ

        ማርሻል

ቼልሲ 0-1 ኖቲንግሀም ፎረስት

                አዎኒዪ

እረፍት | አስቶን ቪላ 1-0 ቶተንሀም

     ራምሴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
60' ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ዎልቭስ

        ማርሻል

60' ቼልሲ 2-1 ኖቲንግሀም ፎረስት

      ስተርሊንግ          አዎኒዪ

60' አስቶን ቪላ 1-0 ቶተንሀም

     ራምሴ

52' ሳውዝሀምፕተን 0-1 ፉልሀም

                 ቪኒሰስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
64' ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ዎልቭስ

        ማርሻል

64' ቼልሲ 2-2 ኖቲንግሀም ፎረስት

      ስተርሊንግ        አዎኒዪ

64' አስቶን ቪላ 1-0 ቶተንሀም

     ራምሴ

66' ሳውዝሀምፕተን 0-1 ፉልሀም

                 ቪኒሰስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ድል አድርጓል !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ከ ሻልክ 04 ጋር ያደረጉትን የሊግ መርሐ ግብር 6ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።

የባየር ሙኒክን የማሸነፊያ ግቦች ቶማስ ሙለር ፣ ኪሚች ፣ ናብሪ 2x ፣ ቴል እና ናዝራዊ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ባየር ሙኒክ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ ስምንት በማድረስ አንድ ጨዋታ ከሚቀረው ተከታዩ ዶርትመንድ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አራት ከፍ ማድረግ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ከሌፕዚግ የሚገናኝ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75' ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ዎልቭስ

        ማርሻል

75' ቼልሲ 2-2 ኖቲንግሀም ፎረስት

      ስተርሊንግ         አዎኒዪ

75' አስቶን ቪላ 2-0 ቶተንሀም

     ራምሴ
ልዊስ

78' ሳውዝሀምፕተን 0-2 ፉልሀም

                 ቪኒሰስ
ሚትሮቪች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90' ማንችስተር ዩናይትድ 2-0 ዎልቭስ

        ማርሻል
ጋርናቾ


85' ቼልሲ 2-2 ኖቲንግሀም ፎረስት

      ስተርሊንግ         አዎኒዪ

90' አስቶን ቪላ 2-0 ቶተንሀም

     ራምሴ
    ልዊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ሲያሸንፍ ቼልሲ ነጥብ ጥሏል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር ያደረገውን የሊግ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ቼልሲ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረገውን አቻ ጨዋታ 2ለ2 በሆነ ውጤት አጠናቋል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግብ አንቶኒ ማርሻል እና አሌሀንድሮ ጋርናቾ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የቼልሲን ሁለት ግቦች ራሂም ስተርሊንግ ከመረብ ሲያሳርፍ ለኖቲንግሀም ፎረስት አዎኒዪ ሁለቱን ግቦች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ ስድስት በማድረስ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቼልሲ በአርባ ሶስት ነጥብ አስራ አንደኛ ደረጃን ይዟል።

በሌላ ጨዋታ አስቶን ቪላ ቶተንሀምን 2ለ1 በሆነ ውጤት ሲረታ ፉልሀም ሳውዝሀምፕተንን 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን በውድድር አመቱ ሀያ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ በርንማውዝ ፣ ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ እንዲሁም ቶተንሀም ከ ብሬንትፎርድ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሳውዝሀምፕተን ዛሬ መውረዱን ሊያረጋግጥ ይችላል ! በአሰልጣኝ ሩበን ሴሌስ የሚመራው ሳውዝሀምፕተን ዛሬ ከፉልሀም ጋር የሚያደርገውን ወሳኝ የሊግ መርሐ ግብር ማሸነፍ የማይችል ከሆነ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱን ያረጋግጣል። ሳውዝሀምፕተን በፕርሚየር ሊግ የመቆየት ዕድሉን ለማለምለም በዛሬው ጨዋታ ፉልሀምን የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ የገባ ሲሆን በጨዋታው የሚሸነፍ ወይም አቻ የሚለያይ ከሆነ ከወዲሁ መውረዱን ያረጋግጣል።…
ሳውዝሀምፕተን ከሊጉ መውረዱን አረጋግጧል !

በአሰልጣኝ ሩበን ሴሌስ የሚመራው ሳውዝሀምፕተን ከፉልሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት መሸነፉን ተከትሎ ከወዲሁ ወደ ሻምፒዮን ሺፑ መውረዱን አረጋግጧል።

ሳውዝሀምፕተን በውድድር አመቱ ሀያ አራት ጨዋታዎችን በመሸነፍ በአንድ የውድድር አመት በርካታ ጨዋታዎችን የተሸነፈ ቀዳሚው ክለብ መሆን ችሏል።

ሳውዝህምፕተን ከአስራ አንድ ዓመታት የሊጉ ቆይታ በኋላ ወደ ሻምፒየን ሺፑ ሊወርዱ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማሸነፍ ነበረብን አሸንፈናል "

ማንችስተር ዩናይትድ በዎልቭስ ላይ ወሳኝ ድል ማስመዝገቡን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ በንግግራቸውም " ወሳኝ ድል አስመዝግበናል ፣ ከሽንፈቶች እና ከግለሰብ ስህተቶች ማገገም ችለናል ማሸነፍ ነበረብን አሸንፈናል።

አሌሀንድሮ ጋርናቾ በፍጥነት ተፅዕኖ ማሳደር ችሏል ፣ በዚህ አመት ብዙ ጊዜ መመልከት ችለናል ይህ ትልቅ በራስ መተማመን ይሰጠዋል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የሌሎችን ውጤት ማየት አያስፈልገንም "

የቀያይ ሴጣኖቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቡድናቸው የሌሎችን ውጤት ማየት እንደማያስፈልገው እና ሁሉም ነገር በእጁ መሆኑን ተናግሯል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በንግግሩም " ለአራት ውስጥ ፉክክሩ በጣም አስፈላጊ ድል ነው ያስመዘገብነው ፣ የሻምፒየንስ ሊግ ቦታችንን ለማስጠበቅ ስድስት ነጥብ እንፈልጋለን።

ከፊታችን ያሉትን ጨዋታዎች ካሸነፍን በሻምፒየንስ ሊግ እንሳተፋለን የሌሎች ውጤት ማየት የለብንም ሁሉም ነገር በእጃን ነው የሚገኘው

ዛሬ ለዎልቭስ ግብ ጠባቂ ጥሩ ጨዋታ ነበር ፣ የሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታው ለእሱ ድንቅ ነበር ፣ ጥሩ የሆኑ ኳሶችን ማዳን ችሏል እንኳን ደስ አለህ ልንለው ይገባል።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዶርትመንድ ድል አድርጓል !

በጀርመን ቡንደስሊጋ ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዶርትመንድ ከ ምንቻግላድባች ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የዶርትመንድን የማሸነፊያ ግብ ማለን ፣ ቤሊንግሀም ፣ ሀለር 2x እና ሬይና ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ስቲንድል እና በንሰባይኒ የምንቻግላድባችን ግቦች አስቆጥረዋል።

ዶርትመንድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ ሰባት በማድረስ ከሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አንድ ማጥበብ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቦርስያ ዶርትመንድ ከኦግስበርግ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቲያጎ ሲልቫ በቼልሲ ቤት ይቆያል !

ብራዚላዊው የቼልሲ የመሐል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ቲያጎ ሲልቫ በቀጣይ የውድድር ዓመቱ በለንደኑ ክለብ እንደሚቆይ የተጫዋቹ ባለቤት አሳውቃለች።

እንደ ቲያጎ ሲልቫ ባለቤት ቤላ ሲልቫ መልዕክት በለንደን ቆይታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ስትገልፅ " በለንደን በጣም ደስተኞች ነን ለተጨማሪ ዓመት እንቆያለን " በማለት ተናግራለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ክለቡን ከቀጣይ ክረምት ጀምሮ በይፋ ማሰልጠን እንደሚጀምሩ ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት እንደሚፈርሙ ሲነገር በቀጣይ ቀናት በይፋ በሀላፊነት እንደሚሾሙ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ ድል አድርጓል !

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ከአጃስዮ ጋር ያደረጉትን የሊግ መርሐ ግብር 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።

የፒኤስጂንን የማሸነፊያ ግቦች ክሊያን ምባፔ 2x ፣ ሀኪሚ ፣ ሩይዝ እና ዮሱፍ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የፒኤስጂው የፊት መስመር ተጨዋች ክሊያን ምባፔ በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ ሀያ ስድስት ከፍ ማድረግ ችሏል።

ፒኤስጂ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰማንያ አንድ በማድረስ ከተከታዩ ሌንስ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #ስድስት ከፍ ማድረግ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe