TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

ቶተንሀም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ባደረጋቸው ሁሉም የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር የቻለ ብቸኛ ክለብ ነው።

ብራይተን በዘንድሮው የውድድር ዘመን ባደረጋቸው ሁሉም የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ግብ የተቆጠረበት ብቸኛው ክለብ ነው።

አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ያሰለጠኗቸውን ቡድኖች እየመሩ ኤምሬትስ ስታዲየም ላይ ያደረጓቸውን ያለፉት አስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

ዌስትሀም ዩናይትድ አርሰናልን በፕርሚየር ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈው ከአራት አመት በፊት ጥር ወር ላይ ነበር።

ዛሬ ምሽት የሚጠበቁ ጨዋታዎች :-

4፡30 ብራይተን ከ ቶተንሀም

5፡15 አርሰናል ከ ዌስትሀም ዩናይትድ


@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

አስቶን ቪላ ከበርንሌይ ጋር ያደረገውን የሀያኛ ሳምንት የሊግ መርሐ ግብር 3ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ድል መመለስ ችለዋል።

የአስቶን ቪላን የማሸነፊያ ግቦች ቤይሊ ፣ ዲያቢ እና ሉዊዝ ከመረብ ሲያሳርፉ አምዱኒ እና እና ፎስተር ለበርንሌይ አስቆጥሯል።

አስቶን ቪላ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል እኩል ነጥቡን አርባ ሁለት በማድረስ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች ዎልቭስ ኤቨርተንን 3ለ0 እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ብሬንትፎርድን 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት መርሀ ግብር አርሰናል ከ ክሪስታል ፓላስ ጋር እያደረጉ ያሉትን ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

- መድፈኞቹን መሪ ማድረግ የቻሉ ሁለት ግቦች ተከላካዩ ጋብርኤል ማግሀሌስ እና ዲን ሄንደርሰን በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል።

- ጋብሬል ማግሀሌስ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ሶስተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

- ጋብሬል ማግሀሌስ አርሰናልን ከተቀላቀለ ወዲህ ከየትኛውም የፕርሚየር ሊግ ተከላካይ በበለጠ አስራ ሁለት የሊግ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- አርሰናል በመጀመሪያው አጋማሽ 64% - 36% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Premiereleague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በሀያ ሶስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቶተንሀም ከኤቨርተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የቶተንሀምን ግቦች ሪቻርልሰን 2x ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ሀሪሰን እና ብራንዝዌት የኤቨርተንን የአቻነት ግብ አስቆጥረዋል።

ብራዚላዊው የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ሪቻርልሰን በውድድር ዘመኑ አስረኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

4️⃣ኛ :- ቶተንሀም ( 44 ነጥብ )

1️⃣7️⃣ኛ :- ኤቨርተን ( 19 ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ማንችስተር ሲቲ ከ ኤቨርተን

ቅዳሜ - ቶተንሀም ከ ብራይተን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#premiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐግብር ብራይተን ክሪስታል ፓላስን 4ለ1 ሲያሸንፍ ኒውካስል ዩናይትድ ከሉተን ታውን ጋር 4ለ4 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ግቦችን ለኒውካስል ዩናይትድ ሎንግስታፍ 2x ፣ ትሪፔር እና ባርንስ ሲያስቆጥሩ ለሉተን ታውን ኦሾ ፣ ባርክሌይ ፣ ሞሪስ እና አዴባዮ ከመረብ አሳርፈዋል።

የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ደንክ ፣ ሂንሸልውድ ፣ ቡናኖቴ እና ፔድር ከመረብ ሲያሳርፉ ማቴታ የ ክሪስታል ፓላስን ግብ አስቆጥሯል።

በሌላ ጨዋታ ፉልሀም እና በርንሌይ ጨዋታቸውን 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

7️⃣ ብራይተን :- 35 ነጥብ

9️⃣ ኒውካስል ዩናይትድ :- 33 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊጉ የሚሳተፈው ሉተን ታውን ባለፉት አስራ ስምንት ተከታታይ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ግብ አስቆጠረው መውጣት ችለዋል።

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር የሉተን ታውን አስራ ስምንት ከፍተኛው መሆኑ ተነግሯል።

ያለፉትን ዘጠኝ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻሉት ሉተን ታውኖች በተከታታይ ግብ ካስቆጠሩባቸው አስራ ስምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት አራቱን ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague

ማንችስተር ዩናይትድ በአንድ የውድድር አመት አስራ ሰባት ጨዋታዎች ሲሸነፍ ከሰላሳ አራት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ቼልሲ እ.ኤ.አ ከ 2017 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን በፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ማሸነፍ ችሏል።

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ብቻ ሰማንያ አራት የግብ ሙከራዎች ተደርገውባቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኒውካስል ፉልሀምን 1ለ0 ፣ ዌስትሀም ዎልቭስን 2ለ1 ፣ ኤቨርተን በርንሌይን 1ለ0 ሲያሸንፉ አስቶን ቪላ ከብሬንትፎርድ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።

የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግብ ብሩኖ ጉማሬስ ከመረብ አሳርፏል።

ለአስቶን ቪላ ግቦችን ኦሊ ዋትኪንስ 2x እና ሮጀርስ ሲያስቆጥሩ ለብሬንትፎርድ ምቤሞ ፣ ዛንካ እና ዊሳ ከመረብ አሳርፈዋል።

የዌስትሀም ዩናይትድን የማሸነፊያ ግብ ጄምስ ፕራውስ እና ፓኩዌታ እንዲሁም ለዎልቭስ ሳራቢያ አስቆጥሯል።

ኤቨርተን በርንሌይን ሲያሸንፍ ካልቨርት ሌዊን ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።

ሉተን ታውን በበኩሉ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

ኦሊ ዋትኪንስ በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስምንት ማድረስ ችሏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ?

4️⃣ አስቶን ቪላ :- 60 ነጥብ

7️⃣ ዌስትሀም ዩናይትድ :- 48 ነጥብ

8️⃣ ኒውካስል ዩናይትድ :- 47 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Premiereleague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ጥሩ የሚባል ጊዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሁን ላይ ሊጉን በአራት ነጥቦች ልዩነት መምራት ጀምረዋል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል በዚህ አመት በሊጉ ምን አሳካ ?

- ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች ካሉት ማንችስተር ሲቲ በአራት ነጥብ ርቀው ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ።

- በሊጉ ሰማንያ አምስት ግቦችን በማስቆጠር ብዙ ግብ ያስቆጠረ ክለብ ነው።

- በውድድር አመቱ በሊጉ ሀያ ስምንት ግቦች የተቆጠሩበት ሲሆን ይህም ከየትኛውም የሊጉ ክለብ ያነሰ ነው።

- በአስራ ስድስት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት የወጣ ቀዳሚው ክለብ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት እድሜ የቀረው ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር በአጓጊነቱ ሲቀጥል በዛሬው ዕለት ማንችስተር ሲቲን ወደ መሪነት አምጥቷል።

ለረጅም ጊዜ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የቆየው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከዋንጫ ፉክክሩ ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።

በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር የሚለያዩት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የሊቨርፑል ቆይታቸውን አንድ የእንግሊዝ ፕርሚየር ዋንጫን በማሸነፍ ለማጠናቀቅ ተገደዋል።

ወቅታዊ የዋንጫ ተፎካካሪዎች ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 85 ነጥብ ( 58 ንፁህ ግብ )

2️⃣ አርሰናል :- 83 ነጥብ ( 60 ንፁህ ግብ )

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

- ማንችስተር ሲቲ :- ቶተንሀም እና ዌስትሀም

- አርሰናል :- ማንችስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን

ሊጉን ማን ያሳካዋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe