TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ማን ይሆናል ?

የዘንድሮው የውድድር ዓመት የተደረጉ ውድድሮችን ተከትሎ #ሰባት ግብ ጠባቂዎች የዓመቱ ምርጥ ለመባል በፉክክር ላይ ይገኛሉ።

በዚህም መሰርት :-

- ያሲን ቦኑ ( ሞሮኮ )

- አሊሰን ቤከር ( ብራዚል )

- ቲቡዋ ኩርቱዋ ( ቤልጅዬም )

- ዶሚኒክ ሌቫኮቪች ( ክሮሽያ )

- ኤምሊያኖ ማርቲኔዝ ( አርጀንቲና )

- ማይክ ማይጋን ( ፈረንሳይ )

- ማኑኤል ኑየር ( ጀርመን ) ለዓመቱ የፊፋ ምርጥ ግብ ጠባቂት በእጩነት የቀረቡ ግብ ጣበቂዎች ሆነዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የሰባት ተጫዋቾችን ግልጋሎት አያገኝም !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የበዓል ቀናት ( BOXING DAY ) ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ መካሄዳቸውን ሲጀምሩ ሊቨርፑል #ሰባት ተጫዋቾችን እንደማያገኙ ተገልጿል።

የአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ስብስብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ በበዓል ሰሞን ጨዋታዎች የማይኖር ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው።

- ጄምስ ሚልነር - ሮቤርቶ ፊርሚንሆ

- ከርትስ ጆንስ - ዲያጎ ጆታ

- ሉዊስ ዲያዝ - አርተር ሜሎ እና

- ኢብራሂም ኮናቴ መሆናቸው ለክለቡ ቅርበ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ይፋ አድርገዋል።

ሊቨርፑል የሊጉ አስራ አምስተኛ መርሐ ግብራቸውን #ነገ ምሽት 2:30 ከአስቶን ቪላ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን ድል ቀንቶታል !

በጣልያን ሴርያ የሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢንተር ሚላን ከ ኤስ ሚላን ጋር ያደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የኢንተር ሚላንን ብቸኛ የማሸነፍያ ግብ ላውታሮ ማርቲኔዝ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኤስ ሚላን በሊጉ ካደረጓቸውን #ሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ውስጥ ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም።

ኤስ ሚላን ባደረጓቸው ያለፉት አስራ ሶስት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣት አልቻሉም።

ኢንተር ሚላን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ኤስ ሚላን በሰላሳ ስምንት ነጥቦች #ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢንተር ሚላን ከሳምፕዶሪያ እንዲሁም ኤስ ሚላን ከ ቶራኖ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ናስር ድል ቀንቷቸዋል !

በሳውዲ ፕርሚየር ሊግ የአስራ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የክርስቲያኖ ሮናልዶው ክለብ አል ናስር ከ አል ታዎን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአል ናስርን የማሸነፊያ ግቦች አብዱልራህማን ግሀሬብ እና አብዱላህ ማዱ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው የአል ናስር የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ሲቆጠሩ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በውድድር ዓመቱ ለአል ናስር በሊጉ አራት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን #ሰባት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

የክርስቲያኖ ሮናልዶው ክለብ አል ናስር ማሸነፉን ተከትሎ ተከታዮቹን በግብ ክፍያ በመብለጥ በአርባ ነጥብ ሊጉን #በአንደኝነት እየመራ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የቡድኑ ችግር እኔ አይደለሁም "

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ግርሀም ፖተር የቡድኑ ውጤት ማጣት ዋና ችግር እርሳቸው እንደሆኑ እንደማያስቡ ተናግረዋል።

" የክለቡ ውጤት ማጣት ችግር እኔ ነኝ ብለው የሚያስቡ ሰዎች እንደሚኖሩ እርግጠኛ ነኝ ፣ ትክክል ናቸው ብዬ አላምንም ፣ እዚህ የመጣሁት ቡድኑን ለማገዝ ነው ፣ በክለቡ ውስጥ መስራቴን እቀጥላለሁ።" ሲሉ አሰልጣኝ ግርሀም ፖተር ተናግረዋል።

ሰማያዊዎቹ በሁሉም ውድድሮች ያደረጓቸውን ያለፉት ተከታታይ #ሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻሉ ሲሆን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ከመሪው አርሰናል በሀያ ሶስት ነጥቦች ርቀው በሰላሳ አንድ ነጥብ አስረኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ድል ቀንቶታል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ማርከስ ራሽፎርድ 2x እና ጄደን ሳንቾ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ሀያ አራት ግቦች ሲያስቆጥር ስምንት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

- ማርከስ ራሽፎርድ በኦልድትራፎርድ ባደረጋቸው ተከታታይ #ሰባት ጨዋታዎች ላይ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

- ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን አርባ ዘጠኝ በማድረስ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት በማጥበብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- ሌስተር ሲቲ በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ አራት ነጥቦች በመሰብሰብ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

- በቀጣይ ሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል እንዲሁም ሌስተር ሲቲ ከ አርሰናል የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊጉ ጨዋታዎች መራዘማቸውን ቀጥለዋል !

አስራ ሰባተኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በመደረግ ላይ ይገኛል።

ውድድር ከቻን የአፍሪካ ዋንጫ መልስ ዳግም ወደ ድሬዳዋ ያቀና ሲሆን በከተማው ባለው ነበራዊ የአየር ሁኔታ #ሰባት ጨዋታዎች ሊራዘሙ ችለዋል።

ምን ያህል ጨዋታዎች ተራዝመዋል ?

1. ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ :- በከባድ ዝናብ ምክንያት ሜዳ ማጫወት ባለመቻሉ ጨዋታ ተቋርጦ ሲራዘም በቀጣይ ቀናት ሊደረግ ችሏል።

2. አርባምንጭ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ :- ሜዳው ለጨዋታ ምቹ ባለመሆኑ ጨዋታ ተራዝሞ ከቀናት በፊት ሐሙስ ሊደረግ ችሏል።

3. መቻል ከ አዳማ ከተማ

4. ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

5. ሲዳማ ቡና ከ ሀድያ ሆሳዕና

6. ድሬዳዋ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ

7. ፋሲል ከነማ ከ ወላይታ ድቻ

8. አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድህን

9. ባህርዳር ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ

ከተራ ቁጥር ሶስት እስከ ዘጠኝ ያሉ ጨዋታዎች ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች መልስ ሊጉ ሲቀጥል እንደሚካሄድ የሊጉ አወዳዳሪ አካል አሳውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኡመድ ኡክሪ ግብ አስቆጥሯል !

የዋልያዎቹ የፊት መስመር አጥቂ ኡመድ ኡክሪ ቡድኑ አል ሱዋይክ በትላንትናው ዕለት አል ባሽራን 4ለ2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ አንድ ግብ አስቆጥሯል።

ኡመድ ኡክሪ በኦማን ቆይታው በአስራ አንድ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ያደረገ ሲሆን #ሰባት ጎሎችን አስቆጥሮ #አራት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የኡመድ ኡክሪው ክለብ አል ሱዋይክ ከሊጉ መሪ አል ናሀዳ በሶስት ነጥብ ርቆ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ኡመድ ኡክሪ ጊኒን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሚገጥመው የዋልያዎቹ የቡድን አባል ሲሆን በቀጣይ ቀናት ቡድኑን በሞሮኮ በመቀላቀል ልምምዱን እንደሚጀምር ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የባየር ሙኒክ እና ሲቲን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የፊታችን ዕሮብ የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጉትን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

አልያንዝ አሬና ስታዲየም ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ የመልስ ጨዋታ ፈረንሳዊው ዳኛ ክሌመንት ቱርፒን በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ፈረንሳዊው ዳኛ ክሌመንት ቱርፒን ከዚህ በፊት #ሰባት ጊዜ የባየር ሙኒክን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የመሩ ሲሆን የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ምንም ጨዋታ አልተሸነፈም።

ሁለቱ ቡድኖች ከሳምንት በፊት ኢትሀድ ላይ ያደረጉትን የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ 3ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ እና ሲቲ አቻ ተለያይተዋል !

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሪያል ማድሪድን ግብ ቪንሰስ ጁኒየር ሲያስቆጥር ለማንችስተር ሲቲ የአቻነቷን ግብ ኬቨን ዴብሮይነ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቪንሰስ ጁኒየር በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሻምፒየንስ ሊግ ግቦች ወደ #ሰባት ከፍ ማድረግ ችሏል።

ሁለቱ ቡድኖች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታቸውን ቀጣይ ሳምንት ኢትሀድ ስታዲየም ላይ የሚያደርጉ ይሆናል።

#CheersToPassion
#CheersToAllFans
#Heineken

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ አመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የዘንድሮው የ2022/23 ውድድር አመት የውድድሩ ምርጥ ተጨዋች #ሰባት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ቡካዩ ሳካ ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ማርከስ ራሽፎርድ ፣ ኬቨን ዴብሮይን ፣ ሀሪ ኬን እና ትሪፒየር የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው ቀርበዋል።

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ነው ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ማነው ?

የአንድ ጨዋታ ሳምንት ጊዜ ብቻ የቀረው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች #ሰባት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

1. እስማኤል ኦሮ አጎሮ

2. ፉዓድ ፈረጃ

3. ያሬድ ባየህ

4. ጌታነህ ከበደ

5. ባሲሩ ኡመር

6. አለልኝ አዘነ

7. ቢኒያም በላይ በመሆን በእጩነት መቅረባቸውን አወዳዳሪው አካል ይፋ አድርጓል።

የስፖርቱ ቤተሰብም ምርጫውን እስከ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ብቻ ማከናወን እንደሚችል አክስዮን ማህበሩ ገልጿል።

የእርስዎ የአመቱ ኮከብ ማን ነበር ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ እና ሊቨርፑል ነጥብ ተጋርተዋል !

በመጀመሪያ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2023/24 የውድድር አመት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ቼልሲ እና ሊቨርፑል 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- ሊቨርፑልን መሪ ያደረገች ግብ ሉዊስ ዲያዝ ሲያስቆጥር አክሴል ዲሳሲ ቼልሲን አቻ ማድረግ ችሏል።

- ሞሀመድ ሳላህ ለመጀመርያ ጊዜ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ ለሊቨርፑል ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል።

- ቼልሲ ከሊቨርፑል ጋር ያደረጓቸውን ያለፉት #ሰባት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

9️⃣ኛ :- ቼልሲ ( 1️⃣ ነጥብ )

🔟ኛ :- ሊቨርፑል ( 1️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

- ቼልሲ ከ ዌስትሀም ዩናይትድ

- ሊቨርፑል ከ በርንማውዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮናልዶ የስታዲየም መቀመጫ ሊሰየምለት ነው !

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበን የስታዲየማቸው አንደኛው ክፍል የሆነውን መግቢያ በር ቁጥር #ሰባት በቀድሞ ተጨዋቻቸው ፖርቹጋላዊ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ስም ለመሰየም ማቀዳቸው ተገልጿል።

ስፖርቲንግ ሊስበን ከዚህ በፊት የታዳጊ አካዳሚያቸውን ስያሜ " Academia Cristiano Ronaldo " በማለት መሰየማቸው ይታወቃል።

ክለቡ በተጨማሪም በዘንድሮው የውድድር ዘመን የሚጠቀሙበትን ሶስተኛ ማልያ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ መታሰቢያ በማድረግ " CR7 " የሚል አርማ በማልያው ላይ ማስቀመጥ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

ሰባተኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሰባት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

👉 ጁሊያን አልቫሬዝ

👉 ጃሮድ ቦውን

👉 ፔድሮ ኔቶ

👉 ሞሀመድ ሳላህ

👉 ሰን ሁንግ ሚን

👉 ኬራን ትሪፔር

👉 ኦሊ ዋትኪንስ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

ሰላሳ አንደኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሰባት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት አሌክሳንደር አይሳክ ፣ ማክ አሊስተር ፣ ሮድሪጎ ሙኒዝ ፣ ኮል ፓልመር ፣ ሴሜንዮ ሰን ሁንግ ሚን እና ቤን ዋይት በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸዉ።

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ ጣፋጭ ድል ተቀዳጅተዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሰላሳ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረጉትን ተጠባቂ ጨዋታ 4ለ3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ኮል ፓልመር 3x እና ኮነር ጋላገር ከመረብ ሲያሳርፉ ለማንችስተር ዩናይትድ አሌሀንድሮ ጋርናች 2x እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመረብ አሳርፈዋል።

የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር በዚህ አመት በሊጉ አስራ ስድስት ግቦች አስቆጥሮ #ስምንት ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ወደ #ሰባት ከፍ አድርጓል።

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ አስራ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

6️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ :- 48 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ቼልሲ :-  43 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል

እሁድ - ሼፍልድ ዩናይትድ ከ ቼልሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ድል አድርጓል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከካዲዝ ጋር ያደረገውን የስፔን ላሊጋ ሰላሳ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባርሴሎናንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጇ ፊሊክስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፖርቹጋላዊው የባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፊሊክስ በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች #ሰባት አድርሷል።

በአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ የሚመራው ባርሴሎና ያለፉትን አስራ ሶስት ጨዋታዎች አልተሸነፈም።

የሁለቱ ክለቦች ደረጃ ምን ይመስላል ?

2️⃣ ባርሴሎና - 70 ነጥብ

1️⃣8️⃣ ካዲዝ - 25 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ጂሮና ከ ካዲዝ

እሁድ - ሪያል ማድሪድ ከ ባርሴሎና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው የአርሰናል ታዳጊ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከ 18ዓመት በታች ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች የሆነው ኦቢ ማርቲን በርካታ ግቦች እያስቆጠረ ድንቅ ጊዜ ማሳለፉን ቀጥሏል።

የ 16ዓመቱ ኦቢ ማርቲን ቡድኑ ዛሬ የኖርዊች ሲቲ አቻውን 9ለ0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ #ሰባት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ማርቲን ቡድኑ ባለፉት ሰባት የ 18ዓመት በታች ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ብቻ ሀያ አራት ግቦችን ማስቆጠር እንደቻለ ተነግሯል።

ተጨዋቹ የናይጄሪያ ፣ እንግሊዝ እና ዴንማርክ ዜግነት እንዳለው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ እና ሙኒክ ጨዋታን ማን ይመራዋል ?

ሪያል ማድሪድ ከባየር ሙኒክ ጋር የሚያደርጉትን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ የሚመሩት የመሐል ዳኛ ይፋ ተደርገዋል።

የፊታችን እሮብ ማድሪድ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ፖላንዳዊው ዳኛ ሲሞን ማርሲንያክ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ በሲሞን ማርሲንያክ እየተመራ ካደረጋቸው #ሰባት የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በሁለቱ ሲሆን በሶስቱ ተሸንፎ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል።

የ 42ዓመቱ ፖላንዳዊ ዳኛ ሲሞን ማርሲንያክ ባለፈው አመት በማንችስተር ሲቲ አሸናፊነት የተጠናቀቀውን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ መምራታቸው አይዘነጋም።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe