TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አራተኛ ጨዋታዎች አርሰናል ፣ ሪያል ማድሪድ ፣ ባየር ሙኒክ እና ኢንተር ሚላን ተጋጣሚዎቻቸውን መርታት ችለዋል።

አርሰናል ሲቪያን በትሮሳርድ እና ቡካዩ ሳካ ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ሪያል ማድሪድ ከብራጋ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በብራሂም ዲያዝ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር እና ሮድሪጎ ግቦች 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ባየር ሙኒክ ከጋላታሳራይ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በሀሪ ኬን ሁለት ግቦች 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

በሌላ ጨዋታ ኢንተር ሚላን በላውታሮ ማርቲኔዝ ብቸኛ ግብ ሳልዝቡርግን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ሪያል ማድሪድ ፣ ባየር ሙኒክ እና ኢንተር ሚላን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ጥሎ ማለፉን መቀላቀል ችለዋል።

የክለቦች የምድብ ደረጃ ምን ይመስላል ?

ምድብ አንድ :-

1️⃣ኛ. ባየር ሙኒክ ( 1️⃣2️⃣ ነጥብ )

ምድብ ሁለት :-

1️⃣ኛ. አርሰናል ( 9️⃣ ነጥብ )

ምድብ ሶስት :-

1️⃣ኛ. ሪያል ማድሪድ ( 1️⃣2️⃣ ነጥብ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አምስተኛ ጨዋታዎች ሲደረጉ ማንችስተር ሲቲ ፣ ዶርትሙንድ እና ባርሴሎና ተጋጣሚዎቻቸውን መርታት ችለዋል።

ማንችስተር ሲቲ ሌፕዚግን በኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ፎደን እና አልቫሬዝ ግቦች 3ለ2 ያሸነፈ ሲሆን ኦፔንዳ ሌፕዚግን ቀዳሚ ያደረጉ ሁለት ግቦች አስቆጥሯል።

ኒውካስል ዩናይትድ ከፒኤስጂ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 ሲያጠናቅቁ በአሌክሳንደር አይሳክ ለኒውካስል እንዲሁም ምባፔ ለፒኤስጂ ግብ አስቆጥረዋል።

ቦርስያ ዶርትመንድ በበኩሉ ከኤሲ ሚላን ጋር ያደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ባርሴሎና ከፖርቶ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በካንሴሎ እና ጇ ፌሊክስ ግቦች 2ለ1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ የፖርቶን ብቸኛ ገብ ፔፔ አስቆጥሯል።

ኤርሊንግ ሀላንድ ያስቆጠራቸውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ገቦች አርባ ያደረሰ ሲሆን ሌፕዚግ ላይ ከየትኛውም ክለብ በበለጠ አስራ ሁለት ግቦች አስቆጥሯል።

ቦርስያ ዶርትመንድ እና ባርሴሎና ማሸነፋቸውን ተከትሎ ጥሎ ማለፉን መቀላቀል ችለዋል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

ምድብ ስድስት

1️⃣ ዶርትመንድ :- 1️⃣0️⃣ ነጥብ
2️⃣ ፒኤስጂ:- 7️⃣ ነጥብ
3️⃣ ኒውካስል :- 5️⃣ ነጠብ
4️⃣ ኤሲ ሚላን :- 5️⃣ ነጥብ

ምድብ ሰባት

1️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 1️⃣5️⃣ ነጥብ
2️⃣ ሌፕዚግ  :- 9️⃣ ነጥብ

ምድብ ስምንት

1️⃣ ባርሴሎና :- 1️⃣2️⃣ ነጥብ
2️⃣ ፖርቶ  :- 9️⃣ ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አምስተኛ ጨዋታ አርሰናል እና ሪያል ማድሪድ ተጋጣሚያቸውን ሲረቱ ባየር ሙኒክ እና ኢንተር ሚላን አቻ ተለያይተዋል።

አርሰናል ሌንስን 6ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ግቦቹን ቡካዩ ሳካ ፣ ማርቲኔሊ ፣ ኦዴጋርድ ፣ ጄሱስ ፣ ካይ ሀቨርትዝ እና ጆርጂንሆ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ሪያል ማድሪድ ናፖሊን 4ለ2 ሲያሸንፍ ግቦቹን ቤሊንግሀም ፣ ሆሴሉ ፣ ሮድሪጎ እና ኒኮ ፓዝ አስቆጥረዋል ለናፖሊ ሲሞኒ እና አንጉይሳ ከመረብ አሳርፈዋል።

ኢንተር ሚላን ከቤኔፊካ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል።

የምድብ አንድ መሪው ባየር ሙኒክ በበኩሉ ከኮፐንሀገን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ ጥሎ ማለፉን መቀላቀል ችሏል።

መድፈኞቹ በመጀመሪያው አጋማሽ አምስት ግቦችን በማስቆጠር የመሩ የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ መሆን ችለዋል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣. ሪያል ማድሪድ 1️⃣5️⃣
2️⃣. ናፖሊ :- 7️⃣

1️⃣ አርሰናል :- 1️⃣2️⃣
2️⃣ ፒኤስቪ :- 8️⃣

1️⃣ ሪያል ሶሴዳድ :- 1️⃣1️⃣
2️⃣ ኢንተር ሚላን :- 1️⃣1️⃣

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ዩኒየን በርሊንን 3ለ2 ሲያሸንፍ ማንችስተር ዩናይትድ በባየር ሙኒክ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ሆሴሉ  2x እና ሴባዮስ ከመረብ ሲያሳርፉ ለዩኒየን በርሊን ክራል እና ቮላንድ አስቆጥረዋል።

ባር ሙኒክን አሸናፊ ያደረገች ብቸኛ ግብ ኪንግስሊ ኮማን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በሌሎች ጨዋታዎች ናፖሊ ብራጋን 2ለ0 ፣ ኮፐንሀገን ጋላታሳራይን 1 ለ 0 እንዲሁም ቤኔፊካ ሳልዝበርግን 3ለ1 ሲያሸንፉ ኢንተር ሚላን ከሪያል ሶሴዳድ አቻ ተለያይተዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ ከአውሮፓ ውድድሮች ውጪ መሆኑን አረጋግጧል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ምድብ ጨዋታዎች አስራ አምስት ግቦች ያስተናገደ የመጀመሪያው የእንግሊዝ ክለብ መሆኑ ተገልጿል።

ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ክለቦች እነማን ናቸው ?

ምድብ አንድ

1️⃣ ባየር ሙኒክ
2️⃣ ኮፐንሀገን

ምድብ ሶስት

1️⃣ ሪያል ማድሪድ
2️⃣ ናፖሊ

ምድብ አራት

1️⃣ ሪያል ሶሴዳድ
2️⃣ ኢንተር ሚላን

ዩሮፓ ሊግ የገቡ ክለቦች እነማን ናቸው ?

- ጋላታሳራይ
- ብራጋ
- ቤኔፊካ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ አንትወርፕ ባርሴሎናን 3ለ2 እንዲሁም ኤሲ ሚላን ኒውካስል ዩናይትድን 2ለ1 ሲያሸንፉ ዶርትመንድ ከፒኤስጂ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ፑልሲች እና ቹኩዌዜ ከመረብ ሲያሳርፉ ለኒውካስል ዩናይትድ ጆኢልንተን አስቆጥሯል።

የቦርስያ ዶርትመንድን ግብ አዴይሚ ሲያስቆጥር የፒኤሴጂን የአቻነት ግብ ኤምሬ ከመረብ አሳርፏል።

በሌሎች ጨዋታዎች አትሌቲኮ ማድሪድ ላዝዮን 2 ለ 0 እንዲሁም ፖርቶ ሻክታር ዶኔስክን ን 5ለ3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ክለቦች እነማን ናቸው ?

ምድብ አምስት

1️⃣ አትሌቲኮ ማድሪድ
2️⃣ ላዝዮ

ምድብ ስድስት

1️⃣ ዶርትመንድ
2️⃣ ፒኤስጂ

ምድብ ሰባት

1️⃣ ባርሴሎና
2️⃣ ፖርቶ

ዩሮፓ ሊግ የገቡ ክለቦች እነማን ናቸው ?

- ሻክታር ዶኔስክ
- ፊኖርድ
- ኤሲ ሚላን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

ፍፃሜውን ለንደን ዌምብሌይ ስታዲየም ላይ የሚያደርገው የዘንሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ይካሄዳል።

በዚህም መሰረት ፡-

5፡00 ኮፐንሀገን ከ ማንችስተር ሲቲ

5፡00 ሌፕዚግ ከ ሪያል ማድሪድ

ሊታዩ የሚገባቸው ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

የሌፕዚጉ የፊት መስመር አጥቂ ሉዊስ ኦፔንዳ ሊታዩ ከሚገባቸው ተጫዋቾች መካከል ሲጠቀስ በቡንደስ ሊጋው አስራ አራት ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሲደረጉ ሪያል ማድሪድ ሌፕዚግን 1ለ0 እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ ኮፐንሀገንን 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሪያል ማድሪድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ብራሂም ዲያዝ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የማሸነፊያ ግቦችን ለማንችስተር ሲቲ ኬቨን ዴብሮይን ፣ በርናርዶ ሲልቫ እና ፊል ፎደን ከመረብ ሲያሳርፉ ለኮፐንሀገን ማትሰን አስቆጥሯል።

ሪያል ማድሪድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ያደረጋቸውን ሰባት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣት ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ ያለፉትን ዘጠኝ ተከታታይ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል።

የመልስ ጨዋታዎች ከሀያ አንድ ቀናት በኋላ የሚደረጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታ ፒኤስጂ ሪያል ሶሴዳድን 2ለ0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ባየር ሙኒክ በላዚዮ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ እና ብራድሌይ ባርኮላ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የላዚዮን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሲሮ ኢሞቢሌ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።

የመልስ ጨዋታዎች ከአስራ ዘጠኝ ቀናት በኋላ የሚደረጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታ ኢንተር ሚላን አትሌቲኮ ማድሪድን 1ለ0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ዶርትመንድ እና ፒኤስቪ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የኢንተር ሚላንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ማርኮ አርናቶቪች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የቦርስያ ዶርትመንድን ግብ ዶንዬል ማለን ከመረብ ሲያሳርፍ ሉክ ዲ ዮንግ ፒኤስቪ ኢንዶቨንን በፍፁም ቅጣት ምት አቻ አድርጓል።

የጣልያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን በሁሉም ውድድሮች ዘጠነኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

የመልስ ጨዋታዎች ከሀያ አንድ ቀናት በኋላ የሚደረጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

ሪያል ማድሪድ ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርገውን ተጠባቂ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ለመታደም በርካታ ደጋፊዎች ከሳንቲያጎ በርናቦ ውጪ ለቡድኑ አቀባበል አድርገዋል።

በጎል ቻናላችን በቪዲዮ መመልከት ይቻላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://t.iss.one/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe