TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሎሚ ሙለታ ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

አትሌት ሎሚ ሙለታ በማጣሪያ ውድድሩ 9:10.73 በሆነ ሰዓት በመግባት የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ #አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሲምቦ አለማየሁ በሚቀጥለው ምድብ የማጣሪያ ውድድሯን በማድረግ ላይ ትገኛለች።

የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ማክሰኞ ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር የተካፈሉት ሁለቱም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሲምቦ አለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ለፍፃሜ አልፈዋል።

በሁለተኛው ምድብ ማጣሪያ የተካፈለችው አትሌት ሲምቦ አለማየሁ 9:15.42 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ ማለፍ ችላለች።

በመጀመሪያው ምድብ የማጣሪያ ውድድሯን ያደረገችው ሎሚ ሙለታ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ መድረሷ ይታወቃል።

የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ማክሰኞ ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች የግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድሯን በመጀመሪያ ምድብ ያደረገችው ኢትዮጵያዊቷ ወርቅነሽ መሰለ ለፍፃሜ ደርሳለች።

አትሌት ወርቅነሽ መሰለ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን 1:58.06 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

የ800ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ምሽት 4:45 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች የግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድሯን በሁለተኛው ምድብ ያደረገችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለፍፃሜ ደርሳለች።

አትሌት ፅጌ ዱጉማ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን 1:57:47 á‰ áˆ†áŠ ሰዓት በመግባት #በአንደኛነት ማጠናቀቅ ችላለች።

በመጀመሪያው ምድብ የተወዳደረችው አትሌት ወርቅነሽ መሰለ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ መድረሷ ይታወቃል።

የ800ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ምሽት 4:45 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 1,500ሜ ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድር የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለፍፃሜ መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል።

በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለው አትሌት ኤርሚያስ ግርማ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሩን የመጨረሻውን ደረጃ በመያዝ አጠናቋል።

በሁለተኛው ምድብ የተወዳደረው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በበኩሉ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

ኢትዮጵያ የማትወከልበት የ1500ሜ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ማክሰኞ ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም ምሽት 3:50 ሰዓት የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024           #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍፃሜ እና ማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የሴቶች 800 እና 5000 ሜትር ፍፃሜ እንዲሁም የወንዶች 3000ሜ መሰናክል ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

- ምሽት 2:04 :- 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ማጣሪያ ( አትሌት ጌትነት ዋለ ፣ ለሜቻ ግርማ እና ሳሙኤል ፍሬው )

- ምሽት 4:45 :- 800ሜ ሴቶች ፍፃሜ ( አትሌት ወርቅነሽ መሰለ  እና ፅጌ ድጉማ )

- ምሽት 4:15 :- 5000ሜ ሴቶች ፍፃሜ ( ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ )

*በውድድሩ ኢትዮጵያ እስካሁን አንድ የብር ሜዳልያ ማሳካት ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ወንዶች መሰናክል የግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድሩን በመጀመሪያው ምድብ ያደረገው ኢትዮጵያዊው አትሌት ጌትነት ዋለ ለፍፃሜ ደርሷል።

አትሌት ጌትነት ዋለ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሩን 8:18:25 በሆነ ሰዓት በመግባት በሶስኛነት ማጠናቀቅ ችሏል።

በሚቀጥሉት ምድቦች አትሌት ለሜቻ ግርማ እና ሳሙኤል ፍሬው የማጣሪያ ውድድራቸውን ያደርጋሉ።

የ 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ውድድር እሮብ ነሐሴ 1/2016 ዓ.ም ምሽት 4:40 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ወንዶች መሰናክል የግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድሩን በሁለተኛው ምድብ ያደረገው ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ለፍፃሜ ደርሷል።

አትሌት ሳሙኤል ፍሬው የግማሽ ፍፃሜ ውድድሩን 8:11:61 በሆነ ሰዓት በመግባት በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

በውድድሩ የሚጠበቀው ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በቀጣይ የማጣሪያ ውድድሩን ያደርጋል።

የ 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ውድድር እሮብ ነሐሴ 1/2016 ዓ.ም ምሽት 4:40 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ወንዶች መሰናክል የማጣሪያ ውድድሩን በሶስተኛው ምድብ ያደረገው ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ለፍፃሜ ደርሷል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ የማጣሪያ ውድድሩን 8:23:89 በሆነ ሰዓት በመግባት #በአንደኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

በማጣሪያው የተካፈሉት ሶስቱም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለ 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

የ 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ውድድር እሮብ ነሐሴ 1/2016 ዓ.ም ምሽት 4:40 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024           #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍፃሜ እና ማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ፍፃሜ እንዲሁም የሴቶች 1500ሜ ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

- ቀን 5:05 :- 1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ( አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ፣ ብርቄ ሀየሎም እና ድርቤ ወልተጂ )

- ምሽት 4:10 :- 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ( አትሌት ሎሚ ሙለታ እና ሲምቦ አለማየሁ )

@tikvahethsport @kidusyoftahe