TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ከሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 9:00 ሰዓት የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል።

- ጨዋታውን በምን መከታተል ይቻላል ?

ጨዋታውን በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይቻላል youtube.com/c/EthiopiaFF

- ጨዋታውን ማን ይመራዋል ?

የዛሬውን ጨዋታ ጅቡቲያኑ መሐመድ ጉዌዲ በዋና ዳኝነት እንዲሁም ኤሌዬ ዲሪር እና ራሺድ ቦራሌህ በረዳት ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

በዛሬው ዕለት እና እሁድ የሚደረገውን ጨዋታ በፊፋ የተመዘገበ መሆኑን ተከትሎ ኢንተርናሽናል ዳኞች የሚመሩት ይሆናል።

- ጨዋታውን በስታዲየም መከታተል ይቻላል ?

ጨዋታው የሚደረግበት የአዲስ አበባ ሰታዲየም የእድሳት ሥራ ሙሉ ለሙሉ ባለመጠናቀቁ ምክንያት ጨዋታው #ያለደጋፊ በዝግ እንደሚደረግ ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

መረጃው ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተወሰደ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia  🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት እና በጋና አክራ ሲካሄድ የቆየው የ 2023 የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ትላንት ምሽት ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ በውድድሩ በአትሌቲክስ ውድድር ሰባት የወርቅ ሜዳልያዎች ስታስመዘግብ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች የቦክስ ውድድር የወርቅ ሜዳልያም አግኝታለች።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በውድድሩ #በአትሌቲክስ

- ሰባት የወርቅ ፣

- ሰባት የብር እና

- አራት የነሀስ ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ የአትሌቲክስ የሜዳልያ ሰንጠረዡን ከናይጄሪያ በመቀጠል በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችላለች።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቦክስ ውድድር ሁለት የወርቅ እና አንድ የነሀስ ሜዳልያ እንዲሁም በብስክሌት ውድድር አንድ የብር ሜዳልያ መመዝገብ ተችሏል።

#አጠቃላይ የሜዳሊያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1ኛ ግብፅ ፡- 187 ሜዳሊያዎች
2ኛ ናይጄርያ ፡- 121 ሜዳሊያዎች
3ኛ ደቡብ አፍሪካ ፡- 106 ሜዳሊያዎች

8ኛ ኢትዮጵያ ፡- 22 ሜዳሊያዎች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

45ኛው የአለም አትሌቲክስ ሀገር አቋራጭ ውድድር በሰርቢያ ቤልግሬድ ሲካሄድ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ 20ዓመት በታች 6ኪ.ሜ ውድድርን ተከታትለው በመግባት #ማሸነፍ ችለዋል።

ከ 20ዓመት በታች በተደረገው የሴቶች ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገሯ #ወርቅ ማስገኘት ችላለች።

ሌሎች አትሌቶቻችን አሳየች አይቸው #ሁለተኛ እንዲሁም ሮቤ ዲዳ #ሶስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ ታሪካዊውን የአረንጓዴ ጎርፍ ድል አስመዝግበዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ሀገር አቋራጭ ውድድር ታሪክ ከ 20ዓመት በታች ሴቶች ውድድርን ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በ 8ኪ.ሜ ወንዶች በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት መዝገበ ስሜ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የብር ሚዳልያ አስገኝቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

ኢትዮጵያ የአለም እጅ ኳስ ፌዴሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ዞን አምስት የወጣቶች እና ታዳጊዎች ውድድርን እንድታዘጋጅ መመረጧን የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ውድድሩ የሀገራችን መልካም ገጽታ እና የቀጠናውን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ወዳጅነት ለማጠናከር እንዲሁም እጅ ኳስ ስፖርት እንዲያድግ የሚያግዝ በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል።

የአለም የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን እና የአፍሪካ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን በጥምረት የሚያዘጋጁት ውድድሩ “ የምስራቅ አፍሪካ የህዝብ ለህዝብ ወዳጅነትን እናጠናክራለን " በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት እነማን ናቸው ?

- ኢትዮጵያ          - ሶማሊያ           - ሩዋንዳ
- ቡሩንዲ           - ዩጋንዳ             - ታንዛኒያ
- ኬንያ               - ሱዳን              - ደቡብ ሱዳን
- ጁቡቲ

የሀገራት ልዑካን ብዛት ምን ይመስላል ?

- አንድ ሀገር ሁለት ቡድን ይኖረዋል ፣ አንድ ቡድን 17 ልኡካንን ይይዛል አጠቃላይ ወደ 350 የሚጠጋ ልዑካኖች ይኖራሉ።

ውድድሩ መቼ እና የት ይካሄዳል ?

- በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከግንቦት 4 - 9/2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

- አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እና በአራት ኪሎ ስፖርት እና ትምህርት ማዕከል እንደሚካሄድ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

ለቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት እና የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ክብር በሚዘጋጀው የቦክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በተለያየ ሚዛን ካካፈለፈለቻቸው አስራ ሶስት ቦክሰኞች ስድስት ሜዳልያዎች አገኘች።

ጋና በተደረገው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በቦክስ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ወርቅ ያስገኙልን ቤተልሄም ገዛሀኝ እና ቤቴልሄም ወልዴ እንዲሁም ነሀስ ያስገኘው ተመስገን ያሸንፋሉ ተብሎ ትልቅ ግምት የተሰጣቸው ቦክሰኞች ነበሩ።

በወንዶች ምክትል ሳጅን ተመስገን ምትኩ ማጣሪያዎቹን በዝረራ በመጨረስ ለፍጻሜ ደርሶ በሲሼልስ ተሸንፎ ብር ሜዳሊያ ያገኘ ሲሆን

- በሴቶች ቤተልሄም ገዛሀኝ በደረሰባት የእጅ ውልቃት ምክንያት ጨወታውን እየመራች ለማቋረጥ ተገዳ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

- እንዲሁም ሮማን አሰፋ ጥሩ ተፎካክራ የብር ሜድሊያ ተሸልማለች።

- በተጨማሪም በወንዶች ሱራፌል አላዩ እና ሚሊዮን ጬባ ነሀስ ሜዳልያ ለሀገራችን ያስገኙ አትሌቶች ናቸው።

ባሳለፍነው ሳምንት የጀመረው እና ለተከታታይ ቀናት ሲደረግ ቆይቶ ትላንት ፍፃሜውን ባገኘው ውድድር ላይ በመካፈል ዳጎስ ያለውን ሽልማት ለመውሰድ ሀምሳ አራት የአፍሪካ ሀገራት ደቡብ አፍሪካ ከትመው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የትግራይ ክልል ክለቦች ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት ዋናው ሊግ ከ 2017ዓ.ም የውድድር ዘመን ጀምሮ ተመልሰው እንዲወዳደሩ የኢፌዴሪ ባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር መወሰኑ ይፋ ተደርጓል።

የኢእፌ ከዚህ ቀደም አስተላልፎት የነበረውን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ በመሻር የትግራይ ክልል ክለቦች ከጦርነቱ በፊት ሲወዳደሩበት ወደነበረው ዋናው ሊግ ተመልሰው እንዲወዳደሩ ከመንግሥት የቀረበውን አቅጣጫ በመቀበል ውሳኔ አሳልፏል።

በ 2017ዓ.ም የውድድር ዘመንም :-

- 19 ቡድኖች ተሳታፊ ይሆናሉ
- 5 ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊግ ይወርዳሉ።

መቐለ 70 እንደርታ ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ስሑል ሽረ በቀጣዩ የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ይወዳደራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በ 2018ዓ.ም የውድድር ዘመን ሊጉ ከዚህ ቀደም ወደነበረበት 16 ክለቦች ተሳታፊ እንደሚሆኑበት የ ኢእፌ ገልጿል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ሴቶች ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ አቻው ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣርያ ሶስተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ብሔራዊ ቡድኑ የአለም ዋንጫ ማጣርያ ሶስተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ኬንያ ናይሮቢ ላይ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም የሚያደርግ ይሆናል።

የማጣሪያ ጨዋታውን በደርሶ መልስ ውጤት የሚያሸንፈው ቡድን በመጨረሻው የማጣሪያ ዙር ከጅቡቲ እና ብሩንዲ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

ለሀያ አራተኛ ጊዜ የሚደረገው የ 2017ዓ.ም የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ህዳር 8/2017ዓ.ም የተሳታፊ ቁጥሩን ከፍ በማድረግ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል።

ቀጣዩ የ 2017ዓ.ም የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የታሳታፊ ቁጥሩን ከዚህ በፊት ከነበረው 45,000 ወደ 50,000 ከፍ በማድረግ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዘንድሮው የ2017 የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሉሲ ( ድንቅነሽ ) የተገኘችበት 50ኛ አመት ክብረ በዓል ተያይዞ እንደሚከበር ተነግሯል።

የሩጫው 30,000 ማልያዎች ከወዲሁ ለድርጅቶች መሸጣቸውን እና ቀሪ 20,000 ቲሸርቶች ብቻ መቅረታቸውን አዘጋጆቹ በዛሬው ዕለት አሳውቀዋል።

ምዝገባ ከነገ ጀምሮ በቴሌ ብር እንዲሁም በዳሽን ባንክ ስድስት የተመረጡ ቅርንጫፎች በይፋ እንደሚጀመር ተያይዞ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia

በ3000 ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ወደ ማጠናቀቂያው በጥሩ ኃይል ወደፊት እየመጣ የነበረው እና ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ የተጠበቀው ለሜቻ ግርማ ወድቆ ውድድሩን ማጠናቀቅ አልቻለም።

ጉዳቱ የከፋ እንዳይሆንበትና ጤናው  ደህና እንዲሆን እንመኛለን።

ሳሙኤል ፍሬው 6ኛ ፤ ጌትነት ዋለ ደግሞ 9ኛ ሆነው ነው የጨረሱት።

ሞሮኮ፣ አሜሪካ እና ኬንያ ሜዳሊያዎቹን ወስደዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

"
በእግሩ እና በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት አልደረሰበትም " - የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን " አትሌት ለሜቻ ግርማ በተደረገለት የሲቲ ስካን ምርመራ በእግሩና በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት እንዳልደረሰት ከሆስፒታል የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል " ሲል በይፋ አሳውቋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe