TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የባህር ዳር ከተማን ግቦች ሀብታሙ ታደሰ እና አደም አባስ ከመረብ ሲያሳርፉ ለኢትዮጵያ መድን ሳይመን ፒተር እና ሀቢብ ከማል ማስቆጠር ችለዋል።

- የኢትዮጵያ መድኑ ተጨዋች ሀቢብ ከማል በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ ግቡን ሲያስቆጥር ሌላኛው ተጨዋች ሳይመን ፒተር ስድስተኛ ጎሉን ከመረብ አሳርፏል።

- የባህርዳር ከተማው ተጨዋች ሀብታሙ ታደሰ በውድድር አመቱ ሰባተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

- ባህርዳር ከተማ በአርባ ሶስት ነጥቦች #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ መድን በሰላሳ ስምንት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የባህርዳር ከተማን ግቦች ፍራኦል መንግሥቱ እና ፉዐድ ፈረጃ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለአርባምንጭ ከተማ እንዳልካቸው መስፍን እና አህመድ ሁሴን አስቆጥረዋል።

- ባህርዳር ከተማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ አራት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ ሶስት ነጥብ አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የኢትዮጵያ ቡናን ሁለት ግቦች መሐመድ ኑር ናስር ሲያስቆጥር ለአዳማ ከተማ አድናን ረሻድ እና ደስታ ዮሀንስ ከመረብ አሳርፈዋል።

- የኢትዮጵያ ቡናው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ኑር ናስር በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል

- ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አዳማ ከተማ በተመሳሳይ ሰላሳ አንድ ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአዳማ ከተማን ግብ ዮሴፍ ታረቀኝ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለወላይታ ድቻ የአቻነቱን ጎል ቢንያም ፍቅሩ አስቆጥሯል።

የአዳማ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ዮሴፍ ታረቀኝ በውድድር አመቱ ሰባት ግቦችን አስቆጥሯል።

አዳማ ከተማ በሰላሳ ሁለት ነጥቦች አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ድቻ በሰላሳ አንድ ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ አርባምንጭ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአርባምንጭ ከተማን ግብ ተመስገን ደረሰ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለፋሲል ከነማ የአቻነቱን ጎል በዛብህ መለዮ አስቆጥሯል።

የአርባምንጭ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ተመስገን ደረሰ በውድድር አመቱ ዘጠነኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ፋሲል ከነማ በሰላሳ አራት ነጥቦች አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ አራት ነጥብ አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ሀይቆቹ በተከታታይ ያደረጓቸውን #አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም በሶስቱ ሲሸነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና በዚህ አመት በተመሳሳይ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው ስምንት አሸንፈው ሰባት ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀድያ ሆሳዕና በሰላሳ ሁለት ነጥቦች #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ በተመሳሳይ ሰላሳ ሁለት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

አርባምንጭ ከተማ በተከታታይ ያደረጓቸውን ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ወላይታ ድቻ በሰላሳ ሁለት ነጥቦች #አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ አምስት ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀድያ ሆሳዕና በሰላሳ ሶስት ነጥቦች #ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልቂጤ ከተማ በሀያ ዘጠኝ ነጥብ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- አዳማ ከተማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከተማ በሀያ ስድስት ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ቡናን ግብ መሐመድ ናስር ሲያስቆጥር ለለገጣፎ ለገዳዲ አማኑኤል አረቦ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ቡናው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ናስር በውድድር አመቱ አስረኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቦቹን ሰላሳ አምስት በማድረስ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ለገጣፎ ለገዳዲ በአስራ ሁለት ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ለገጣፎ ለገዳዲ ከ አዳማ ከተማ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe