TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
ፕርሚየር ሉጉ አዲስ ህግ ተግባራዊ ያደርጋል !

በመጪው አርብ በሚጀምረው አዲሱ የውድድር ዓመት የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ ጨዋታ #ዘጠኝ ተቀያሪ ተጨዋቾችን ማስመዝግብ እንደሚችሉ ተገልጿል ።

ይህ ህግ ተግባራዊ ሲሆን በ ጨዋታ ቀን አልጣኞች ሶስት ተጨዋቾችን ብቻ መቀየር የሚችሉ ሲሆን በ ጨዋታ ወቅት የ ጭንቅላት ጉዳት የሚያስተናግዱ ተጨዋቾች ካሉ #ሁለት ተጨማሪ ቅያሪ እንደሚፈቀድላቸው ተነግሯል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አጫጭር የመጀመሪያ አጋማሽ መረጃዎች !

ሌስተር ሲቲ 0 - 2 ቼልሲ

ሩዲገር
ካንቴ

• አንቶኒ ሩዲገር በ ሌስተር ሲቲ ላይ በአጠቃላይ አራት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል ።

• ቼልሲዎች በውድድር ዓመቱ በ ሊጉ ካስቆጠሯቸው ጎሎች 43% በተከላካዮች የተቆጠሩ ናቸው ።

• ሌስተር ሲቲ በዘንድሮ የውድድር አመት ከቆሙ ኳሶች ስምንት ግቦችን በማስተናገድ በሊጉ ላይ ቀዳሚው ክለብ ናቸው ።

• ሪስ ጄምስ በውድድር ዓመቱ በ ስምንት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ።

• ሩዲገር በ ፕርሚየር ሊጉ በድምሩ ስምንት ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል ።

• የ ቼልሲ የተከላካይ ክፍል በሊጉ አስራ ሶስት ጎሎችን በዘንድሮው የውድድር ዓመት አስቆጥረዋል ።

• ይህም በሊጉ ከሚገኙ #ዘጠኝ ክለቦች የተሻለው ሆኖ ይገኛል ።

• ቤን ቺል ዌል በሊጉ ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ላይ በአራት ጎሎች ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል ።

• ንጎሎ ካንቴ ከቀድሞ ክለቡ ሌስተር ሲቲ ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ሁለተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጦና ንቦቹ ድል ቀንቷቸዋል !

በ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች በ ስንታየሁ መንግስቱ ሁለት ግቦች እና ቃልኪዳን ዘላለም ግብ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፈዋል ።

• ታፈሰ ሰለሞን ኢትዮጵያ ቡናን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል ።

• የጦና ንቦቹ ከ ቡናማዎቹ ጋር ባደረጉት ያለፉት አምስት ጨዋታዎች በአራቱ አልተሸነፉም ።

• ቡናማዎቹ ባለፉት በሁሉም የውድድር መድረክ ባደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም ።

• አቡበከር ናስር በጨዋታው ታፈሰ ሰለሞን ላስቆጠራት ግብ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

• ቡናማዎቹ በሊጉ አንድም ጨዋታ ያላሸነፉ ሲሆን በደረጃ ሰንጠረዡ በወራጅ ቀጠናው አስራ አምስተኛ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል ።

• በተቃራኒው የ ጦና ንቦቹ በ #ዘጠኝ ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃን ከ ባህር ዳር ከተማ ተረክበዋል ።

#Betika
#CentralHotelHawassa

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አያክስ በአስደናቂ ጉዟቸው ቀጥለዋል !

በ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የሚመሩት የ ሆላንድ ሊግ መሪ አያክሶች አስደናቂ የሆነ ጉዟቸውን ቀጥለዋል ።

አያክስ በዘንድሮ የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጓቸው ሀያ አምስት ጨዋታዎች ሰባ አራት ጎሎችን በተጋጣሚዎቻቸው መረብ ላይ ሲያሳርፉ በተቃራኒው #ዘጠኝ ግቦች ብቻ ተቆጥሮባቸዋል ።

አያክስ ከተቀናቃኛቸው ፒኤስቪ በ #ሁለት ነጥቦች ርቀው ሊጉን በ #ስልሳ ነጥቦች እየመሩ ይገኛሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia🇪🇹

ለአራተኛ ጊዜ በታንዛኒያ ዳሬሰላም የሚካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ ከ20 እና ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን የሚወክለው ቡድን ዛሬ ማለዳ ላይ ከመክፈቻ መርኃ ግብሩ አስቀድሞ በተካሄዱ ውድድሮች #ዘጠኝ ወርቅ ፣ #አንድ ብር እና
#አንድ ነሃስ በማግኘት ውድድሩን በድል ጀምረውታል ።

መረጃው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የሌስተር ሲቲ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ?

ሌስተር ሲቲዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ምንም ተጫዋች #አለማስፈረማቸው እና ቡድኑን ሊለቁ የሚችሉ ተጫዋቾች መበራከታቸው ለክለቡ ስጋት እንደሆነ ተነግሯል ።

የቡድኑ ግብ ጠባቂ እና አምበል ካስፐር ሽማይክልን ለኒስ የሸጡት ቀበሮዎቹ ሌሎች #ዘጠኝ ተጫዋቾቻቸው በቀጣዩ ክረምት ኮንትራታቸው የሚጠናቀቅ ሲሆን እስካሁን የውል ማራዘሚያ ኮንትራት እንዳልቀረበላቸው ተገልጿል ።

ከዚህ በተጨማሪ የክለቡ ወሳኝ ተጫዋች የሆኑት ዌስሊ ፎፋና ፣ ማዲሰን እና ቴልሚናስ ከሌሎች ክለቦች ጋር ስማቸው እየተያያዘ ሲገኝ የቀኝ መስመር ተመላላሹ ሪካርዶ ፔሬራ በጉዳት ለመጪዎቹ ስድስት ወራት ግልጋሎትን አይሰጥም ።

እነዚህ ችግሮች የገጠሟቸው ሌስተሮች በአንፃሩ እስካሁን አንድም ተጫዋቾች አለማስፈረማቸው በአውሮፓ አምስት ታላላቅ ሊጎች ከሚወዳደሩ ክለቦች ብቸኛው ያደርጋቸዋል ።

ያለፈውን የውድድር ዘመን በስምንተኛ ደረጃ ያጠናቀቁት ቀበሮዎች በዘንድሮው የውድድር አመት ምን ይገጥማቸው ይሆን ?

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ንግድ ባንክ ተከታታይ ድላቸውን አስመዝግበዋል !

በሴካፋ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ እየተሳተፉ የሚገኙት ንግድ ባንኮች ተጋጣሚያቸውን ኤ ፒ አር ኪጋሊን 2 ለ 0 ረተዋል ።

√ መዲና አዎል እና ሎዛ አበራ የማሸነፊያዎቹን ግብ ከመረብ አሳርፈዋል ።

√ መዲና አዎል በሴካፋው ስድስተኛ ጎሏን ስታስቆጥር ሎዛ አበራ የውድድሩን የከፍተኛ ግብ አግቢነት እየመራች ስትገኝ ዘጠነኛ ጎሏ ሆኖ ተመዝግቧል ።

√ ሎዛ አበራ ካስቆጠረቻቸው #ዘጠኝ ግቦች ባለፈ በውድድሩ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችታ ማቀበል ችላለች ።

√ ንግድ ባንክ ምድባቸውን በአንደኝነት ሲያጠናቅቁ በቀጣይ ከ ዩጋንዳው ሺ ኮርፖሬት ጋር ለፍፃሜ ለማለፍ ይጫወታሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና ሊጉን መምራት ጀምረዋል !

በአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ የሚሰለጥኑት ባርሴሎናዎች በላሊጋው አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ካዲዝን 4ለ0 መርታት ችለዋል።

√ ፍራንክ ዲ ዮንግ ፣ አንሱ ፋቲ ፣ ኡስማን ዴምቤሌ እና ሮበርት ሊዋንዶውስኪ የባርሴሎና የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

√ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ በላሊጋው ለባርሴሎና ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ ስድስት ከፍ አድርጓል።

√ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ባርሴሎና ከተቀላቀለ በኋላ ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች #ዘጠኝ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

√ ባርሴሎና አስራ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #በጊዜያዊነት ሊጉን መምራት ጀምረዋል።

√ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባርሴሎና ከ ኤልቼ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኳታር ወይስ ኢኳዶር ?

የኳታሩ የዓለም ዋንጫ በይፋ ዛሬ መካሄዱን ሲጀምር አዘጋጇ ሀገር ኳታር የደቡብ አሜሪካዋን ኢኳዶር የምታስተናግድ ይሆናል።

√ አዘጋጇ ኳታር በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ተሳትፏዋን የምታደርግ ሲሆን ባለፉት ዓመታት የተሻለ ውጤቶችን በእግር ኳሱ እያስመዘገበች ትገኛለች።

√ ኳታር እ.ኤ.አ በ 2019 የኳታር እስያ ዋንጫ ሲያሸንፉ በ 2021 የአረብ ዋንጫ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።

√ ለኢኳዶር ፈታኝ ጨዋታ እንደሚሆን ሲጠበቅ በወንዶች የዓለም ዋንጫ ታሪክ አዘጋጅ ሀገር የመክፈቻ ጨዋታ #ተሸንፎ አያውቅም።

√ ኢኳዶር ከስምንት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫው ሲመለሱ ከምድባቸው ማለፍ የቻሉበት የ 2006 የዓለም ዋንጫ በበጎ መልኩ ይነሳላቸዋል።

√ ኢኳዶር በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ላይ ከጋና እና አሜሪካ በመቀጠል #ሶስተኛው ወጣት ስብስብ ያላት ሀገር ነች።

√ ኢኳዶር ለዓለም ዋንጫው ለማለፍ በማጣርያው #ከሜዳቸው_ውጪ ባደረጉት #ዘጠኝ ጨዋታዎች #ስምንት ነጥቦችን ብቻ ሰብስበዋል።

√ ኳታር ተከታታይ አምስት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ከ ኒካራጉኣ ፣ አልባኒያ ፣ ጓቲማላ ፣ ሁንዱራስ እና ፓናማ አድርጋ ሁሉንም በመርታት ለዛሬው ጨዋታ ተዘጋጅታለች።

√ አምበሉ እና የፊት መስመር ተጫዋቹ ሀሰን አልሀይዱስ እንዲሁም አል ሙአዝ አሊ በኳታር በኩል የሚጠበቁ ተጫዋቾች ናቸው።

√ ኢኳዶር በብራይተኖቹ ኢስቱፒናን እና ሞይሰስ ካይሴዶ ተስፋ በመጣል ቡድኗን አዋቅራለች።

√ ሁለቱ ሀገራት ከአራት ዓመታት በፊት ባደረጉት ጨዋታ ኳታር 4ለ3 በሆነ ውጤት በዘጠኝ ተጫዋቾች ጨዋታውን ለመጨረስ የተገደደችውን ኢኳዶር በሜዳዋ መርታት ችላለች።

√ ጣልያናዊው የመሐል ዳኛ ዳንኤል ኦርሳቶ ይህንን ተጠባቂ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

@tikvahethsport
#QatarWorldCup 🇶🇦

በ 2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ተደርገው ሲጠናቀቁ #ዘጠኝ አፍሪካዊያን ተጫዋቾች የጨዋታው ኮከብ ተሸላሚ መሆን ችለዋል።

በምድብ ጨዋታ #ሰባት_ድሎች በአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ሲመዘገቡ አዲስ ሪከርድ መሆኑም ተገልጿል።

በጥሎ ማለፉ የኳታር የዓለም ዋንጫ #ሞሮኮ እና #ሴኔጋል አፍሪካን በመወክል ብርቱ ፉክክር የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#QatarWorldCup 🇶🇦

የኳታር የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ሁለተኛ ጨዋታ በመደረግ ላይ ሲገኝ አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ ብቸኛ ግብ እየመራች ወደ መልበሻ ክፍል አቅንተዋል።

√ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ግብ ሲያስቆጥር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል።

√ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫው ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን በድምሩ #ዘጠኝ አድርሷል።

√ ሊዮኔል ሜሲ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን #በአምበልነት እየመራ 100ኛ ጨዋታውን በማድረግ ላይ ይገኛል።

√ ሊዮኔል ሜሲ ለብሔራዊ ቡድኑ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ዘጠና አራት ከፍ አድርጓል።

√ ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 1,000ኛ ጨዋታውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe