TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጣይስ ?

ማራኪ እግር ኳስ በማሳየት ምድባቸውን በ ዘጠኝ ነጥብ እና በ ሀያ አንድ የ ግብ ክፍያ ያጠናቀቁት የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ ግማሽ ፍፃሜው ከ ዩጋንዳው ቡድን ጋር ደርሷቸዋል ።

ንግድ ባንክ በቀጣይ ሰኞ ከ ዩጋንዳው ሌዲ ዶቭ ጋር ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰኞ ድል የሚቀናቸው ከሆነ ምስራቅ አፍሪካን በመወከል በ ግብፅ በ ህዳር ወር 2014 ላይ ለሚካሄደው አሁጉራዊ የ #መጨረሻ ውድድር ተሳታፊ ይሆናሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
1. በተጠናቀቀው የ ውድድር ዓመት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ #መጀመሪያ እና #መጨረሻ ግብ ያስቆጠሩት ተጫዋቾች ማናቸው ?

2. ዋልያዎቹ በ ካሜሩን የ አፍሪካ ዋንጫ የሚገጥሟቸውን #ሶስት ሀገራት እነማን ናቸው ?

3. በ ቶኪዮ ኦሎምፒክ ለ ኢትዮጵያ በ 10,000 ሜትር ወንዶች ወርቅ ያስገኘው አትሌት ማነው ?

ምላሽ መስጫ አድራሻ :- https://t.iss.one/joinchat/RyUJe4pwn1exkh-i

#ማስጠንቀቂያ !

1. ግማሽ መልስ አሸናፊ ወይም ተሸላሚ አያደርግም

2. " EDIT " የተደረጉ ምላሾች ተቀባይነት አይኖራቸውም

3. ሶስቱም ጥያቄዎች በአንድ ላይ መመለስ ሲኖርባቸው #በተናጥል የሚመጡ ምላሾች አሸናፊ አያደርግም !
የ ዋልያዎቹ ተጋጣሚ የ መጨረሻ ስብስቧን አሳወቀች !

ዋልያዎቹን ከ ሳምንታት በኋላ መስከረም 29 በ ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የምትገጥመው ደቡብ አፍሪካ የ #መጨረሻ 23 የ ቡድን ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል ።

የ ባፋና ባፋና ዋና አሰልጣኝ ሁጎ ብሮስ ያለ ተፅዕኖ ፈጣሪ አጥቂያቸው ፐርሲ ታው ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል ።

ሁጎ ብሮስ ጥሪ ካቀረቡት ሀያ ሶስት ተጫዋቾች መካከል እስራኤል ከሚጫወተው ተከላካያቸው ሲያንዳ ዡሉ ውጭ ለ ሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስቧን አሳወቀች !

ሊጀመር አሰራ ስምንት ቀናት ብቻ በቀሩት የ ካሜሩኑ የ አፍሪካ ዋንጫ ላይ አስተናጋጇ ካሜሮን በአፍሪካ ዋንጫ ላይ የምትጠቀማቸውን የ #መጨረሻ ሀያ ስምንት ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርጋለች ።

ካሜሩን በ ስብስቧ እንደ አንድሬ ኦናና ፣ ቹፖ ሞቲንግ ፣ ዛምቦ አንጉዊሳ እንዲሁም ቪንሰንት አቡበከር የመሳሰሉ ተጫዋቾችን በስብስቧ አካታለች ።

የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ ካሜሩን አቻቸው ጋር ጥር አምስት ከ ምሸቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe