TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
#DeadlineDay

- ኤቨርተን ቡድናቸውን በቀሪ የውድድር ዘመን ለማጠናከር የሳውዝሀምፕተኑን ቼ አዳምስ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

- ሀኪም ዚያሽ ወደ ፒኤስጂ እንደሚዘዋወር ሰፋ ያሉ መረጃዎች ቢወጡም በሁለቱ ክለቦች መካከል የተደረሰ ስምምነት #የለም

- አርሰናል ሞይሰስ ካይሴዶ ለማስፈረም ሶስተኛ የዝውውር ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ሲጠበቅ ለዝውውሩ 75 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

- ሊድስ ዩናይትድ ኒኮሎ ዛኒዮሎን በውሰት ከሴርያው ክለብ ሮማ ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል።

- የስፖርቲንግ ሊዝበኑ ፔድሮ ፖሮ ወደ ቶተንሀም የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ መዳረሻውን ለንደን ሲያደርግ በዛሬው ዕለት ፊርማውን እንደሚያኖር ይጠበቃል።

- ሊድስ ዩናይትድ ጃክ ሀሪሰን ለመሸጥ ዝግጁ መሆናቸው ሲገለፅ ሌስተር ሲቲ ተጫዋቹን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል።

- የቶተንሀሙ ተጫዋች ዴጃን ስፔንስ በቂ የመጫወት እድል ለማግኘት በውሰት የፈረንሳዩን ሬሚስ ክለብ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#DeadlineDay

- አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሞርጋን ሮጀርስ ከሚድልስብሮው 15 ሚልዮን ፓውንድ በማውጣት በአምስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

- አርጀንቲናዊው የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች አሌሆ ቪሊዝ የላሊጋውን ክለብ ሲቪያ በውሰት ውል ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሰዋል።

- በርንማውዝ ቱርካዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኢኔስ ኡናል ከላሊጋው ክለብ ሄታፌ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

- የማንችስተር ዩናይትዱ ወጣት ተጨዋች ኢሳክ ሀንሰን አሮን በቋሚነት የጀርመኑን ክለብ ዎርደር ብሬመን ለመቀላቀል መቃረቡ ተዘግቧል።

- አልጄሪያዊው ተጨዋች ሰይድ ቤንራህማ በውሰት ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ወደ ስፍራው ማምራቱ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#DeadlineDay - አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሞርጋን ሮጀርስ ከሚድልስብሮው 15 ሚልዮን ፓውንድ በማውጣት በአምስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል። - አርጀንቲናዊው የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች አሌሆ ቪሊዝ የላሊጋውን ክለብ ሲቪያ በውሰት ውል ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሰዋል። - በርንማውዝ ቱርካዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኢኔስ ኡናል ከላሊጋው ክለብ ሄታፌ…
#Update                    #DeadlineDay

- የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች አርማንዶ ብሮሀ ፉልሀምን እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ በውሰት ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል።

- የማንችስተር ዩናይትዱ ወጣት ተጨዋች ኢሳክ ሀንሰን አሮን በቋሚነት የጀርመኑን ክለብ ዎርደር ብሬመን በይፋ ተቀላቅሏል።

- አስቶን ቪላ ሊኖ ሱሳን ከሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በቋሚነት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

- በርንማውዝ ቱርካዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኢኔስ ኡናል ከላሊጋው ክለብ ሄታፌ አስፈርመዋል።

- ኖቲንግሀም ፎረስት ቤልጂየማዊውን የስትራስቡርግ ግብ ጠባቂ ማትዝ ሴልስ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።

- የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ብሪያን ዛራጎዛን ከላሊጋው ክለብ ግራናዳ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

- አልጄሪያዊው ተጨዋች ሰይድ ቤንራህማ ከዌስትሀም ዩናይትድ በውሰት ለፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ፈርሟል።

- የማንችስተር ሲቲው ተጨዋች አልፊ ሀሪሰን ኒውካስል ዩናይትድን በሁለት አመት ኮንትራት ተቀላቅሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አጫጭር የዝውውር መረጃዎች !

- የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በእንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ ዝውውር ዙሪያ በዛሬው ዕለት ለንግግር ተቀምጠው እንደነበር ተገልጿል።

- ራሂም ስተርሊንግ አርሰናልን ጨምሮ ለተለያዩ ክለቦች እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ በቼልሲ ከቆየ ምንም ጨዋታ የማድረግ እድል እንደሌለው ተነግሯል።

- ዌስትሀም ዩናይትድ ካርሎስ ሶለርን ከፒኤስጂ በውሰት ውል ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

- አል አህሊ ቪክተር ኦሲሜን እና ኢቫን ቶኒን ለማስፈረም ከክለቦቻቸው ጋር መስማማታቸው የሚታወቅ ሲሆን ማስፈረም የሚፈልጉት ከሁለቱ አንዱን መሆኑ ተዘግቧል።

- ዎልቭስ የክሪስታል ፓላሱን ግብ ጠባቂ ሳም ጆንስቶንን በ 10 ሚልዮን ፓውንድ በረጅም ጊዜ ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

- የኤቨርተኑ ተጨዋች ኔኡል ሙፓይ በረጅም ጊዜ የውሰት ውል የፈረንሳዩን ክለብ ማርሴይ በይፋ ተቀላቅሏል።

- ቼልሲ ናይጄሪያዊውን አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜንን ለማስፈረም አሁንም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

- ማኑኤል ኡጋርት የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች የሚያደርገውን ፊርማ ያኖረ ሲሆን ዝውውር በቀጣይ ሰዓታት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።

- የሊቨርፑሉ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ስቴፋን ባቼቲች በውሰት ውል ሳልዝበርግን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

የዝውውር መረጃዎቹ ከ ዘ አትሌቲክስ እና ፋብሪዝዮ ሮማኖ የተገኙ ናቸው።

#DeadlineDay

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አጫጭር የዝውውር መረጃዎች !

- ቼልሲ ጄደን ሳንቾን ከማንችስተር ዩናይትድ የሚያስፈርመው በሚቀጥለው አመት የመግዛት ግዴታ ባካተተ የውሰት ውል መሆኑ ተነግሯል።

- የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ግብ ጠባቂ ፒትሮቪች በውሰት ውል ስትራስቡርግን መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

- ቪያሪያል ስፔናዊውን የመስመር ተጨዋች ሁዋን በርናትን ከፒኤስጂ በውሰት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

- ዎልቭስ የአያክሱን የፊት መስመር ተጨዋች ካርሎስ ፎርብስን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

- በአርሰናል ለቁጥር ሶስት ግብ ጠባቂነት ሲፈለግ የነበረው የዎልቭስ ግብ ጠባቂ ዳን ቤንትሌይ በክለቡ እንደሚቆይ ተነግሯል።

- ቼልሲ ከናፖሊ ጋር የሚያደርጉትን ንግግር ለመቋጨት የቪክቶር ኦሲሜንን የመጨረሻ ውሳኔ በመጠበቅ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

- ኢፕስዊች ታውን አርማንዶ ብሮሀን ከቼልሲ በውሰት ለማስፈረም በድጋሜ ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

የዝውውር መረጃዎቹ ምንጭ ዘ አትሌቲክስ ነው።

#DeadlineDay

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አጫጭር የዝውውር መረጃዎች !

- የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ኦሬል ማንጋላን በውሰት ለአንድ አመት ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

- እንግሊዛዊው የፊት መስመር አጥቂ ኢቫን ቶኒ ከብሬንትፎርድ ወደ አል አህሊ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ የህክምና ምርመራውን አድርጓል።

- ስኮት ማክ ቶሚናይ ከማንችስተር ዩናይትድ ናፖሊን ለመቀላቀል የሚያስችለውን ፊርማ አኑሯል ክለቡ በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

- የሊቨርፑሉ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ስቴፋን ባቼቲች በውሰት ውል ሳልዝበርግን መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

- ኒውካስል ዩናይትድ ኢላንጋን ለማስፈረም ለኖቲንግሀም ፎረስት ያቀረበው የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበታል።

#DeadlineDay

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አጫጭር የዝውውር መረጃዎች !

- ኤሲ ሚላን እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ታሚ አብረሀም ከሮማ በውሰት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

- አርሰናል ራሂም ስተርሊንግን ከቼልሲ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

- ኢፕስዊች ታውን ሬስ ኔልሰንን ከአርሰናል በረጅም ጊዜ የውሰት ውል ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

- ክሪስታል ፓላስ ማክሴንስ ላክሮይክስን ከዎልፍስበርግ 21 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት በአምስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

#DeadlineDay

@tikvahethsport     @kidusyoftahe