#WANAW 🤝 #AFF
የዋናው የትጥቅ አምራች ድርጅት ከአዲስ አበባ ስፖርት ፌደሬሽን ጋር በዛሬው ዕለት በኔክሰስ ሆቴል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
ስምምነቱ ሦስት የተለያዩ ክፍሎች ሲኖሩት ለሦስት ዓመት የሚቆይና በየዓመቱ የሚታደስ የ3.4 ሚሊዮን ብር ስምምነት መሆኑንን በዕለቱ ተገልጿል።
#አንደኛው : የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሚያዘጋጀውን ከ17 ዓመት በታች የኳስ ውድድር ዋናው የስፖርት ትጥቅ አምራች የስያሜ መብት ከፌደሬሽኑ ተሰጥቶታል።
#ሁለተኛው: በአዲስ አበባ የሚገኙ የሰፈር ውስጥ የእግር ኳስ ግጥሚያዎችን ለመደገፍ ያለመ ሲሆን ፌደሬሽኑ በአዲስ መልክ ይህንን ውድድር ለማከናወን ከዋናው የስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
#ሦስተኛው: ፌደሬሽኑ "አንድ ሺ አስራ አንድ" በሚል አዲስ በቀረጸው ፕሮጀክት ከ13 ዓመት በታች በሆኑ ታዳጊዎችን (በወንድም በሴትም) በብቁ አሰልጣኞች በተመረጡ ማዕከላት ለመስጠት አቅዷል።
በዚህም ከዋናው የትጥቅ አቅራቢ ድርጅት ጋር ለታዳጊዎች በዝቅተኛ ዋጋ የስፖርት ትጥቅ ለማቅረብ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ስምምነቱ ፌደሬሽኑ በዚህ ዓመት ለማሳካት ያቀዳቸውን እቅዶች በብቃትና በተሻለ ሁኔታ ለመፈጸም ዛሬ ከዋናው የትጥቅ አቅራቢ ድርጅት ጋር የተደረገው ፊርማ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የፌደሬሽኑ ፕ/ት አቶ ደረጄ ገልጸዋል።
የዋናው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብተሥላሴ ገብረ ክርስቶስ በበኩላቸው ድርጅታቸው በዚህ ስምምነት ከሚያገኘው የማስታወቂያና የሽያጭ ሥራ በላይ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ትኩረት መስጠቱን አንስተዋል።
በቅርቡም የመሸጫ ማዕከል በጃን ሜዳ አከባቢ በመክፈት በዝቅተኛ ዋጋ የስፖርት ትጥቆችን ለስፖርቱ ቤተሰብ ለማድረስ ማቀዱን ገልጸዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe