TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
290 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
Download Telegram
#HAWASSA_UNIVERSITY

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የሚቀበላቸውን አዳዲስ ተማሪዎች በፍኖተ ካርታው መሰረት የፍሬሽ ማን ኮርሶችን ለማስተማር መዘጋጀቱን ገለፀ። ዩኒቨርሲቲው በተያዘው የትምህርት ዘመን አዳዲስ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ለመጀመርም ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል። ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ሰዓት ሰባት ካምፓሶች፣ ስምንት ኮሌጆችና ሁለት ኢንስቲትዩቶች በስሩ አሉት። ዩኒቨርሲቲው በ94 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 107 የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም በ 22 የፒ.ኤች.ዲ የትምህርት መርሃ ግብሮችና በ6 የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና እየሰጠ ሲሆን፤ ከ42 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝም ታውቋል።

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ኢንጂነር ፍስሃ ጌታቸው ለኢዜአ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ለበርካታ አመታት የመማር ማስተማር ተግባርን ሲከውን የነበረ ሲሆን በተለይም በ2012 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን እየሰራ ነው።

ተጨማሪ ለማንበብ 👇https://telegra.ph/የሀዋሳ-ዩኒቨርሲቲ-09-18

(ENA)

#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ
@tikavhethmagazine @emush21
⬆️#HAWASSA

የሀዋሳ ታቦር ሕይወት ብርሃን ወጣቶች በTIKVAH-ETH 5ኛው አመት የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ላይ በመሳተፍ ያሰባሰቡትን መፅሃፍት ለግሰዋል።

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethmagazine
#HAWASSA

እሁድ ጥቅምት 30 በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ አንድ ብር የበጎ አድራጎት ማህበር እና የኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማህበር ያዘጋጁት "ለሰብዓዊነት እንገናኝ" በሚል ሀሳብ ትልቅ ዝግጅት አዘጋጅተዋል፡፡ በመድረኩም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ እና አርቲስት ሰርፀ ፍሬ ስብሃት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፕሮግራሙ ጥቅምት 30 በአፍሪካ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

#ቲክቫህ_ኢቨንት
@tikvahethmagazine @emush21
#Hawassa_Industrial_Park

በ22 ባላሃበብቶችየተመሰረተው የሀዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ባለሀብቶች ማህበር በኢንደስትሪያል ፓርኩ ለሚሰሩ ለሃያ ሁለቱም ኩባንያ ሰራተኞች ለእያንዳንዳቸው የሚውል 35ሺ የንጽሕና መጠበቂያ (አንቲ ባክቴሪያል) ማከፋፈሉን ገልጿል፡፡

የሀዋሳ ኢንዲሰትሪያል ፓርክ  ባለሀብቶች ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ካሚላ ሐምዛ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮቪድ-19  ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል በማህበሩ 250 በላይ የፕላስቲክ በርሜሎችን የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫ በራሪ ወረቀቶችን እንዲሁም የባለሞያ ሥልጠናዎችን እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸውልናል፡፡

@tikvahmagbot @tikvahethmagazine
#HAWASSA

ዓመታዊውን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ በይፋ ለማስጀመር የኢፊድሪ ጠ/ሚንስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ሀዋሳ ገብተዋል፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀዋሳ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሲዳማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ፣የክልል መሪዎች እና ሚንስትሮች እንዲሁም የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@tikvahmagbot @tikvahethmagazine
#Hawassa

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) እንዲሁም አስተዳደራቸውን የሚደግፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በሰልፉ ከሲዳማ ክልል ወረዳዎች እና ከሀዋሳ ከተማ የተውጣጡ በርካታ ዜጎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የዘገበው ደሬቴድ ነው።

PHOTO : SRTA & ELIAS DUKAMO
@tikvahethmagazine @tikvahmagBOT
#Hawassa : ለ2 ቀናት ኃይል ይቋረጣል።

በሐዋሳ ከተማ እና አካባቢዋ ለሁለት ቀናት የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ እንደሚኖር ተገልጿል።

መቼ ?

ነገ በ08/01/2014 እና በ09/01/2014 ዓ.ም ጥዋት ከ4:00-600 እንዲሁም ምሽት ከ12:00 - 2:00 ሰዓት ላይ የሀይል መቋረጥ ይከሰታል።

ይህን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደቡብ ሪጅን ነው።

ደንበኞቹ ከወዲሁ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

የሚቋረጥበት ምክንያት ?

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ደቡብ ሪጅን እንዳስታወቀው በሐዋሳና አካባቢዋ የሀይል መቋረጥ የሚከሰተው በስራ ጉዳይ ነው ብሏል።

Credit : Hawssa City Communication

@tikvahethiopia
#Hawassa 📍

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ከነዳጅ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር እንግልትን መቀነስ የሚያስችል አሰራር ይፋ ማድረጉን ገልጿል።

ከዛሬ 5/7/2014 ጀምሮ እስከ 10/7/2014 ተሽከርካሪዎች በሐዋሳ ከተማ ነዳጅ መቅዳት የሚቻለው በፈረቃ እና በተፈቀደላቸው የነዳጅ ማደያ ነው ሲሉ አክለዋል።

በዚህም መሰረት የነዳጅ አገልግሎት የሚሰጠው፦

1/ ባጃጅና የግል ሞተር ነዳጅ የሚቀዱት ከያንጠራ ገመጦ( ግሪን)፤

2/ የመንግስት ሞተርና ባጃጅ ከመናኸሪያ ቶታል፤

3/ የመንግስትና የቤት መኪና፣ዳማስ፣ ኩይትና ሱዙኪ ከኖክ ቁጥር 2፤

4/ ሚኒባሶች ከያንጠራ ጥቁር ውሃ(ግሪን) እንደሚቀዱ የሐዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።

በተጨማሪም በተርጋ ቁጥራቸው መሰረትም መርሐግብር ወጥቶላቸዋል።

1. ሰኞ፣ ዕሮብና አርብ ታርጋ ቁጥራቸው ሙሉ የሆኑት ብቻ ይቀዳሉ።

2. ማክሰኞ ፣ ሐሙስና ቅዳሜ ታርጋ ቁጥራቸው ጎዶሎ የሆኑት ብቻ ይቀዳሉ ።

3. ታርጋ የለሌው የግልም ሆነ የመንግስት ተሽከርካር መቅዳት አይችልም ሲልም ነው ያስታወቀው።

@tikvahethmagazine
#Hawassa 📍

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ410 ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው ስራ አጥ ለሆኑ ወጣቶች የማምረቻ ሼድ ማስረከቡን ገልጿል። 30 ሚሊዮን ብር ብድርም ተመቻችቶላቸዋል ነው የተባለው።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት በከተማዋ በ2014 በጀት አመት ከ25 ሺህ በላይ ስራ አጥ ወጣቶችን በመለየት የስራ እድል ለማመቻቸት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

@tikvahethmagazine
#Hawassa 📍

ከነገ ማለትም ሰኔ 8/2014 ጀምሮ በሐዋሳ ከተማ ለባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶችን ይፋ ማድረጉን በአስተዳደሩ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ አበራ አዴላ እንዳስታወቁት ከጨርቃጨርቅ በአላቲዮን ሆስፒታል አድርጎ በአቶቴ እስከ ትሩፋት እና በሎጊታ መስመር አድርጎ ሲዳማ ሱመዳ ድረስ ያለው ለባጃጅ የተከለከለ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ለህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት በሚከተሉት መስመሮች ብቻ አቋራጭ መንገድን መጠቀም እንደሚችሉም ነው አቶ አበራ የገለፁት።

እንደ ሀላፊው አቋራጭ መንገዶቹ፦

* የጨርቃ ጨርቅ መንገድ ይዞ ባለው የሲዳማ ክልል ፀረ ሙስና ኮምሽን ጎን መስቀለኛ አካባቢን በመጠቀም፣

* ሀዮሌ ትምህርት ቤት አጥር ጎን ያለው መስቀለኛ የትራፊክ መብራትን ይዞ ወደ ስታዲየም መሄጃ መንገድን በመጠቀም፣

* ታቦር መካነየሱስ አጥር ጎን ባለው ወደ አሊቶ ሄዋኖ ትምህርት ቤት መሄጃ መስቀለኛ መንገድን በመጠቀም፣

* የትሩፋት መንገድ ማቋረጫ ሆኖ ባለው የትራፊክ መብራት በሁለቱም አቅጣጫ ያለውን አካባቢ በመጠቀም፣

* ከሎጊታ ካፌና ሬስቶራንት ፊት ለፊት ያለውን እና የቲቲሲ መሄጃ መስቀለኛ መንገድን ይዞ ወደ ኮምቦኒ ትምህርት ቤት ባለው ኮብል ስቶን አካባቢን ያለውን አቅጣጫ በመጠቀም እና

* በናኦል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አድርጎ የዊነር ባርና ሬስቶራንት መሄጃ መንገድን እንደ አቋራጭ በመጠቀም አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ አቶ አበራ አስረድተዋል።

ከነገ ጀምሮ ይህንን በማያከብሩ የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

@tikvahethmagazine
#Hawassa : የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሲዳማን ሕዝብ ባህል የሚወክል እና ለሀዋሳ ከተማ ተጨማሪ ውበት የሚሆን የከተማ መግቢያ በር ግንባታ ፕሮጀክት አስጀምሯል። መግቢያ በሩ ጥቁር ውሃ በኩል የሚገነባ ሲሆን 8 ሜትር ከፍታ አለው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#HAWASSA

" ክለባችን ኩራታችን "

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከክልል ክለቦች ቀድሞ ያሸነፈው ሀዋሳ ከተማ ነሀሴ 29 " ክለባችን ኩራታችን " በሚል ደማቅ የሩጫ መርሐ-ግብር እንደሚያከናውን ገልጿል።

የክለቡን ደጋፊዎች " ለክለቤ እሮጣለሁ " በሚል ከክለቡ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ ቀርቧል።

ክለቡ የመሮጫ ቲሸርት የመሸጫ ቦታዎች
- ፒያሳ አሊያንስ ህንፃ
- ቄራ ሜዳ
- ጎድጓዳ አደባባይ
- አቶቴ ዋርካ
- ቲቲሲ ዋርካ
-05
- ፍቅር ሀይቅ
- ሪፈራል አደባባይ
- ሞቢል አካባቢ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Hawassa  📸

የመስቀል ደመራ በዓል በሀዋሳ ከተማ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዮሴፍ መሪነት እየተከበረ ይገኛል።

@tikvahethmagazine
#Bahirdar   #Hawassa

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር በባህር ዳር የሚገኘውን ጣና ሆቴል እና ሀዋሳ የሚገኘውን ፕሮግረስ ኢንተርናሽናል ሆቴልን ሁለቱንም በ“ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን” ብራንድ እንዲሁም የብሉ ናይል (አቫንቲ) ሪዞርትን በ“ፕሮቴያ ማሪዮት” ብራንድ ለመክፈት ስምምንት ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ወገኖች ባለፈው በፈረንጆቹ ህዳር 2021 በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት አጠገብ የሚገኘውን የዌስቲን ሆቴል ለማስተዳደር ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

@tikvahethmagazine
#Hawassa

በተለያዩ ጊዜያት በሀዋሳ ከተማ የሚስተዋለውን የነዳጅ (በተለይ ቤንዚን) ጥቁር ገበያን አስመልክቶ ተከታታይ ዘገባዎችን መስራታችን ይታወቃል። ይሁንና ችግሩ አሁንም መቀረፍ አለመቻሉን ተጠቃሚዎች ያስረዳሉ።

ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የከተማው ነዋሪ፦

"አሁን አሁንማ ቤንዚን ከተሽከርካሪ አውርዶ መሸጥ እንደ ቢዝነስ እየተቆጠረ መቷል" ይላል ቀመሩን ሲያስረዳም አሁን ላይ በጥቁር ገበያው ቤንዚን በሊትር ከ150 በላይ እንደጉድ እየተቸበቸበ ነው።

አስቡት ከሊትር 60 ብር ያተረፈ ሰው በሞተሩ እስከ 20 ሊትር ቢቀዳ እንኳን 1,200 ብር ያተርፋል ሁለት እና ሶስቴ ከቀዳ ደግሞ በእጥፉ ያገኛል ባለመኪኖች ደግሞ ምን ያህል እንደሚያተርፉ መገመት አያዳግትም።

ሌላኛው የባጃጅ ሹፌር ነገሩን ሲያስረዳ፦

አሁን ላይ እኮ ሱቆች ላይ ጭምር ቤንዚን እንደ ካርድ እየተጠየቀ ይሸጣል በየጎሚስታ ቤቶች ቤንዚን ይገኛል። አንዳንድ አሽከርካሪዎች ጭምር አውርደው ሲሸጡ እንታዘባለን የሚለው የባጃጅ ሹፌር ረጅም ሰልፍ ተሰልፈን በመሀል ገብቶ ሚቀዳም አይጠፋም ትስስሩ ከጥበቃ አንስቶ ነው በምን ሰዓት ተሰልፈን በምን ሰዓት ስራችንን እንደምንሰራ አይታወቅም ሲልም ያነሳል።

ሌሎችም በከተማው ያሉ ነዋሪዎች የጉዳዩን አሳሳቢነት በአፅንኦት ነግረውናል፣ ይህን ያህል ጊዜ እንዴት ቁጥጥር ተደርጎ መፍትሔ ሊበጅለት አልተቻለም የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

አሁን ላይ የነዳጅ ሰልፍ ልማድ የሆነባት ሀዋሳ የተወሰኑ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ለመታዘብ ቢቻልም አመርቂ ውጤት አለማስገኘቱ የብዙዎች ትዝብት ነው አሁንም ቁጥጥሩ በጥልቀት ይቀጥል ዘንድ የብዙዎች ጥሪ ነው።

በእናንተስ አከባቢ ይህ ችግር ይስተዋላል ? እንዴት ባለ መልኩ? ያካፍሉን!

@tikvahethmagazine
#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ የተጀመረዉ ተሽከሪካዎችን በአይነትና በታርጋ ለይቶ በተወሰኑ ማደያዎች የመደለደሉ ስራ መፍትሔ ከመሆን ይልቅ ለጥቁር ገበያ ወይንም ለሕገወጥ ግብይት ዳርጎናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል።

የሞተር ሳይክል እና የሚንባስ ታክሲ አሽከሪካሪ ቅሬታ አቅራቢዎች የተሽከርካሪ ምደባ ሥርዓቱ ችግር ፈቺ አለመሆኑን አስረድተዋል።

"ከማለዳ ጀምሮ ተሰልፈን ዉለን በተለያዩ ምክንቶች ሳንቀዳ የምንመለስበት አጋጣሚ ስላለ ተሰልፎ ከመዋል ይልቅ አዝማሚያዎችን አይተን በየመንገድ ዳሩ በዉሃ ሃይላዶች በ70እና 80ብር ልዩነት ለመግዛት እንገደዳለን" ሲሉ ነው የገለጹት።

አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎችና በየዕለቱ ከንግድና ገበያ ልማት መስሪ ቤቶች የሚመደቡ ባለመያዎች ጭምር የዚሁ ችግር ተባባሪዎች ናቸዉ ሲሉ አሽከሪካሪዎቹ ይናገራሉ።

በተጨማሪም ተራ ጠብቀዉ ከሚሰለፉት ባልተናነሰ በሰበብ አስባቡ ያለተራቸዉ እየገቡ የሚቀዱ ተሽከሪካሪዎች በህወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ለሚሸጡ ቤንዚኖች አቀባዮች ናቸዉ ብለዉ እንደሚያምኑም ተናግረዋል።

ስምንትና ሰባት ሊትር ለመቅዳት ብዙ ጊዜ ተሰልፈን እናድራለን የሚሉት የባጃጅ አሽከሪካሪዎች ይህ በመሸሽና ስራ ፈቶ ከመዋል አብዛኛው የባጃጅና ኪዩት አሽከርካሪ ከጥቁር ገበያ ከመደበኛው እጥፍ በሚባል ዋጋ በመገዛት በታሪፍ ላይ ያልተገባ ጭማሪ ለማድረግ እንደሚገደዱ ተናግረዋል።

በመንግስት ሞተር ሣይክልና መኪኖች ጭምር ለጥቁር ገበያዉ አሳላፊ ሆነዉ የሚሰሩ አካላት እንዳሉ በግልፅ እናያለን የሚሉት አሽከርካሪዎቹ  በየማደያዉ አከባቢ የሚስተዋሉ መረባበሾችን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ሄደዉ የሚቀዱባቸዉን ቦታዎች ጭምር እንደሚጠቁሙ ገልፀዋል።

በከተማዋ ረጃጅም የቤንዝን ሰልፎች እንዲስተዋሉና የጥቁር ገበያዉ እንዲስፋፋ #የአቅርቦት_እጥረት ዋነኛ ምክንያት ነዉ ሲል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ይገልጻል።

አክሎም ለመፍትሔ ተብለው በየጊዜዉ የሚወሰዱ እርምጃዎች እየተለመዱ ሲመጡ ሌላ ችግር ይዘዉ መምጣታቸዉን በማጠን በየጊዜው አዳዲስ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነዉ ሲል ገልጿል።

የምደባ ስርዓቱ በየማደያዉ የቀረበዉን ቤንዚን በአግባቡ ለመጠቀም እንጂ ለጥቁር ገበያው ምክንያት ሆኗል የሚል ቅሬታ ግን እስካሁን ቀርቦላቸዉ እንደማያውቅ መምሪያው ገልጿል።

በቀጣይ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ በማሰባሰብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት እንደሚጥርም አስታውቋል።

📌 ይህ ዘገባ ከመጠናቀሩ ሁለት ቀናት አስቀድሞ ህዳር የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ችሎት ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Hawassa በሀዋሳ ከተማ የተጀመረዉ ተሽከሪካዎችን በአይነትና በታርጋ ለይቶ በተወሰኑ ማደያዎች የመደለደሉ ስራ መፍትሔ ከመሆን ይልቅ ለጥቁር ገበያ ወይንም ለሕገወጥ ግብይት ዳርጎናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል። የሞተር ሳይክል እና የሚንባስ ታክሲ አሽከሪካሪ ቅሬታ አቅራቢዎች የተሽከርካሪ ምደባ ሥርዓቱ ችግር ፈቺ አለመሆኑን አስረድተዋል። "ከማለዳ ጀምሮ ተሰልፈን ዉለን በተለያዩ ምክንቶች ሳንቀዳ…
#Hawassa

በሲዳማ ክልል ያለውን የነዳጅ ግብይት ሁኔታ ገምግሞ መፍትሔ ለመስጠት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሚመለከታቸው የቢሮ ሃላፊዎችን በማወያየት አቅጣጫ አስቀምጠዋል ተብሏል።

በክልሉ በተለይ በሀዋሳ ከተማ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የነዳጅ እጥረት መከሠቱን በመግለጽም ችግሩ የአቅርቦትና የግብይት ስርዓቱ ላይ መሆኑ ተነስቷል።

የአቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ አቅራቢ ድርጅት ጋር እንደሚሰራ እና የግብይት ችግሩን ለመፍታት ደግሞ ጠንካራ ግብረሀይል ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አቅጣጫ አስቀምጠው ግብረሀይሉ ወደ ስራ ገብቷል ተብሏል።

በትላንትናው ዕለት በከተማው ሁሉም ማደያ የቤንዚን ስርጭት እንዳልነበር የቲክቫህ ቤተሰቦች ጥቆማ ሰጥተው ነበር።

@tikvahethmagazine
#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ታቦር ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በአንድ የገበያ ማዕከል ኮንቴነር ላይ የተነሳ የእሳት አደጋ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ መምሪያ አስታዉቋል።

የእሳት አደጋዉ የተከሰተው ጠዋት 1:30 አከባቢ ታቦር ክፍለ ከተማ ፋራ ቀበሌ በተለምዶ አዲሱ ገበያ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በአንድ የንግድ ሼድ ሱቅ ነው።

በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ነፃ የስልክ መስመር (7614) በደረሰ ጥቆማ የከተማ አስተዳደሩ እሳት አደጋ እንዲሁም የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እስት አደጋ መኪኖች ከፀጥታ አካላትና ከአከባቢው ሕብረተሰብ ጋር በመሆን የእሳት አደጋውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገልጿል።

"እንደ ወቅቱ ነፋሻማነትና ፀሐያማነት የእሳት አደጋዉን በቀላሉ መቆጣጠር አዳጋች ነበር"ያሉት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቶርባ በከተማ አስተዳደሩ የተዘረጋዉ ፈጣን የመረጃ ልዉዉጥ አደጋውን ለመቆጣጠር አግዟል ነው ያሉት።

አደጋዉ የከፋ ጉዳት እንዳያደር ላደረጉ የአከባቢው ነዋሪዎች፣ፈጣን ምላሽ ለሰጡ የሀዋሳ ከተማ እና ሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እንዲሁም የፀጥታ አካላት የከተማ አስተዳደሩ ሠላምና ፀጥታ ምስጋና አቅርበዋል።

የእሳት አደጋው ትክክለኛ መንስኤ እየተጣራ ነዉ ያሉት መምሪያ ኃላፊው ወቅቱ በጋ በመሆኑ ፀሐያማና ነፋሻማዉ  የአየር ፀባይ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ስለሚታሰብ ሕብረተሰቡ ተገቢዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

#TikvahFamilyHawassa

@tikvahethmagazine
#Hawassa

😀 "የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የመጨረሻዎቹን ፕሪሜር ሊግ ጫወታዎች እንዲያስተናግድ ጥያቄ ቀርቧል"

😀 "ለሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ማጠናቀቂያ መሸጥ ከታሰበው 1 ሚሊዮን ትኬት የተሸጠው ግማሹ ብቻ ነው" - የሀዋሳ ከተማ ልማት ፈንድ ምክር ቤት

የሀዋሳ ከተማ ልማት ፈንድ ምክር ቤት ጥር 20/2017 ዓ/ም ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረዉ የሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ማጠናቀቂያ የቶምቦላ ዕጣ ማዉጫ ቀን መራዘሙን አስታወቀ።

የሀዋሳ ከተማ የልማት ፈንድ ምክር ቤት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዘርሁን ቃሚሶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሳወቁት'' ለስታዲየሙን ማጠናቀቂያ መሸጥ ከታሰበዉ 1 ሚሊዮን ትኬት ግማሹ ብቻ መሸጡን ተከትሎ የዕጣ ማውጫውን ጊዜ ወደ ሚያዚያ 19/2017 ዓ/ም ማራዘሙን ገልፀዋል።

በ2005 ዓ/ም ተጀምሮ እስካሁን ያልተጠናቀቀዉን የሐዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም በማጠናቀቅ ለሀገራዊና አህጉራዊ ወድድሮች ክፍት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሀላፊው ገልፀዋል።

ነገር ግን በከተማዋ የተፈጠረውን የስታዲየም ክፍተት ለመሙላት በማሰብ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊግ ጫወታዎችን ማስተናገድ በሚችልበት ሁኔታ ነባር አፈርና ሳር ሙሉ በሙሉ ተነስቶ በስታንዳርዱ መሰረት በአዲስ ተተክቶ መታደሱን አስታውቀዋል።

በዚህም የእድሳት ሥራ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 3 ሚሊዮን ብር የሚሆነውን ወጪ የሸፈነ ሲሆኖን የልማት ፈንድ ምክር ቤት ደግሞ ቀሪዉን በመሸፈን እድሳቱ መሰራቱን ምክር ቤቱ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዘርሁን ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የመጨረሻዎቹን ፕሪሜር ሊግ ጫወታዎች እንዲያስተናግድ ጥያቄ ማቅረባቸውን ያነሱት አቶ ዘሪሁን ከኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ አዘጋጆችም ልዑካን መጥተው ምልከታ ማድረጋቸውንና የፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ ዙር ጫወታዎች ሀዋሳ እንዲደረግ እንደሚወስኑ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልፀዋል።

የሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም አሁን ካለበት ደረጃ አንስቶ ግንባታዉን ሙሉ በሙሉ  ለማጠናቀቅ ከ3.7ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያስፈልግም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM