TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
290 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
Download Telegram
Register at https://www.effsaa.org/short-term-training-program-registration-form/ after the settlement of the training fee.
Venue
At the training hall of Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) which is located at Kazanchis, Nigist Towers Hotel & Apartments 4th Floor (In front of Elilly International Hotel)
For More Information,
Call us at +251 115 589045 / +251 903 182525
OR
Visit our telegram channel
https://t.iss.one/EFFSAAOfficial
የሰኔ ወር የመጨረሻው ድንቅ ጉዞ ወደ አዋሽ ብሔራዊ ፖርክ እና ድሆ ሎጅ

የጉዞ ቀን:-ሰኔ 11 /2014 | መመለሻ :-ሰኔ 12 /2014
👉 ከሃገር ውጪ ያላችሁ ሃገር ቤት ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻችሁ ይህን ምርጥ ጉዞ በመጋበዝ ሰፕራይዝ ያድርጉ

የምንጎበኛቸው፦ |በተፈጥሮ የታደለውን የአዋሽ ፓርክ| አዋሽ ፏፏቴ| ተፈጥሯዊ ፍልውሃ ከ 40-50c በሚደርስ ውሃ መታጠብ| ዋና በድሆ ሎጅ|

ክፍያ የሚያጠቃልለው፦ | የድንኳን አዳር ፓርኩ ውስር | አንድ ምሽት ካምፕፋየር 🚎 ትራንስፖርት | 🍽 ምግብ,( ቁርስ ምሳ እራት ) ሻይ ቡና | 💧 የታሸገ ዉሃ |🚶አስጎብኚ ስካውት | የፓርክ መግቢያ | ፎቶ ያጠቃልላል|

መነሻ ቦታ ሜክሲኮ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት መገኛ ሰዓት 11:30 መነሻ 12:00 ሰዓት

ዋጋ በአንድ በሰው :- 3500
ለበለጠ መረጃ 👉 የቴሌግራም ግሩፖችንን ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/mirt_haikinhg
📞0962 26 78 20 or @yeneneh
አዘጋጅ፦ የኔነህ ፊልም ፕሮዳክሽን
#አፋልጉኝ

ንብረትነቱ የሀብታሙ ታረቀኝ የሆነ 3L ሚኒባስ መኪና በቀን 6/17/14 በትላንትናው እለት ከይርጋለም ከተማ 05 ቀበሌ ከመኖሪያ ቤት የተሰረቀ ስለሆነ እባካችሁን በያላችሁበት አካባቢ ክትትል እንድታደርጉ እና የሚኖረውን መረጃ በሚከተሉት ስልኮች እንድትሰደጡን በፈጣሪ ስም እንማጸናለን።

የሰሌዳ ቁጥር SD 02582
ባለ 5 ኮለኔት
3L ሚኒባስ

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩ
ስልክ ቁጥር
0911729084
0926040906
092 708 6768

Via መላኩ ዘፍኔ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
TIKVAH-MAGAZINE
#Update: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በናይጄሪያ ያደረጉኑትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ተከትሎ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የተገለጸው የሚኒስቴሮች የጋራ ስብሰባ ዛሬ ጀምሯል። ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የሁለቱ ሀገራት የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይም ቀደም ሲል በማዕድ እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የተስሟሙባቸውን ነጥቦች ጨምሮ አብሮ መስራት የሚችሉባቸው ሌሎች ጉዳዮች…
#Update : ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ በፖለቲካ ፣መከላከያ፣ በባህልና በቱሪዝም፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የተፈረመው ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ በቆየው 3ኛው የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ ነው።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ ኩል በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍሰሃ ሻዉል እና በናይጄሪያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሁመር ዘናባ ፈርመውታል።

ሀገራቱ በመገናኛ ብዙሃን አስተዳደር እና አመራር በተለይም ፣የወጣቶች ተሳትፎ በማሳደግ እና የፖን-አፍሪካዊነትን የሚዘክሩ ይዘቶችን ለማበልፀግ በሚቻሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መካከል ያለውን ፀጋ በመጠቀም ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ተጠቃሚነት እንዲዉል ያስችላል ተብሏል።

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በአፍሪካ ያለዉን እምቅ የሰዉ ሀብት እና ገበያ በጋራ ማልማት እና መጠቀም በስምምነቱ ዉስጥ የተካተቱ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

የ4ተኛ የሁለቱ አገሮች የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ እ.ኤ.አ.2024 አቡጃ ከተማ- ናይጄሪያ እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#Hawassa 📍

ከነገ ማለትም ሰኔ 8/2014 ጀምሮ በሐዋሳ ከተማ ለባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶችን ይፋ ማድረጉን በአስተዳደሩ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ አበራ አዴላ እንዳስታወቁት ከጨርቃጨርቅ በአላቲዮን ሆስፒታል አድርጎ በአቶቴ እስከ ትሩፋት እና በሎጊታ መስመር አድርጎ ሲዳማ ሱመዳ ድረስ ያለው ለባጃጅ የተከለከለ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ለህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት በሚከተሉት መስመሮች ብቻ አቋራጭ መንገድን መጠቀም እንደሚችሉም ነው አቶ አበራ የገለፁት።

እንደ ሀላፊው አቋራጭ መንገዶቹ፦

* የጨርቃ ጨርቅ መንገድ ይዞ ባለው የሲዳማ ክልል ፀረ ሙስና ኮምሽን ጎን መስቀለኛ አካባቢን በመጠቀም፣

* ሀዮሌ ትምህርት ቤት አጥር ጎን ያለው መስቀለኛ የትራፊክ መብራትን ይዞ ወደ ስታዲየም መሄጃ መንገድን በመጠቀም፣

* ታቦር መካነየሱስ አጥር ጎን ባለው ወደ አሊቶ ሄዋኖ ትምህርት ቤት መሄጃ መስቀለኛ መንገድን በመጠቀም፣

* የትሩፋት መንገድ ማቋረጫ ሆኖ ባለው የትራፊክ መብራት በሁለቱም አቅጣጫ ያለውን አካባቢ በመጠቀም፣

* ከሎጊታ ካፌና ሬስቶራንት ፊት ለፊት ያለውን እና የቲቲሲ መሄጃ መስቀለኛ መንገድን ይዞ ወደ ኮምቦኒ ትምህርት ቤት ባለው ኮብል ስቶን አካባቢን ያለውን አቅጣጫ በመጠቀም እና

* በናኦል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አድርጎ የዊነር ባርና ሬስቶራንት መሄጃ መንገድን እንደ አቋራጭ በመጠቀም አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ አቶ አበራ አስረድተዋል።

ከነገ ጀምሮ ይህንን በማያከብሩ የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

@tikvahethmagazine
ትላንት ጥዋት አንድ የአዲስ አበባ ቤተሰባችን አባል ያጋጠመውን አጋርቶናል።

ከ24 ወጥቶ ወደ ኢምፔሪያል በሚወስደው መንገድ አንድ እግረኛ ላይ በ " ኮድ 2 AA 16429 " ታርጋ የነበሩ 4 ሰዎች አንቀውት መሬት አስተኝተው ሲፈትሹት መመልከቱን ገልጿል።

በወቅቱ ይኸው እግረኛ ላይ ይህ ድርጊት ከፈፀሙ ግለሰቦች አንዱ አካባቢውን ሲቃኝ የነበረ ሲሆን መሳሪያ አውጥቶ እንዳሳየውና በኃላ ሊከተላቸው ቢሞክርም በፍጥነት በመንዳታቸው እንዲሁም አካባቢውም የሚመች ስላልሆነ መጨረሻቸውን ሳያይ ቀርቷል።

በአራቱ ሰዎች ተይዞ የነበረው ግለሰብ ነቅቶ ሲንቀሳቀስ በስፖኪዮ መመልከቱን የገለፀልን ይኸው ቤተሰባችን ምናልባት ታርጋውን ካላገኘው ኮድ 2 AA 16429 መሆኑን ጠቁሟል።

ጉዳዩን ለፖሊስም እንዲያውቀው አድርጓል።

ይህ የተፈፀመው ጥዋት ላይ ነውና ጥንቃቄም ማድረግ አይለያችሁ ብሏል።

ለቤተሰባችን ይጠቅማሉ የምትሉትን ጥቆማ፣ አስተያየትና የጥንቃቄ መልዕክት @tikvahmagbot ላይ ይጻፉልን።

@tikvahethmagazine
#የዛሬ ( ሠኔ 7/2014 )

💥 ዛሬ በጋምቤላ ክልል የተፈጠረው የተኩስ ልውውጥና የወጡ መረጃዎች በአጭሩ፦

- በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ " ጋምቤላ " ዛሬ መንግስት አሸባሪ ያለው የሸኔ ወታደሮች (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው) እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የነበር ሲሆን የመንግስት ኃይሎች ወስደውታል በተባለው እርምጃ ለሰዓታት የዘለቀው የተኩስ ልውውጥ ጋብ ብሏል።

- ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ያለማቋረጥ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ከ20 ሲካሄድ ቆይቶ መጠነኛ መረጋጋት በከተማው ተፈጥሯል ነው የተባለው።

- የክልሉ መንግስት ቀየት ብሎ በሰጠው መግለጫ ''በተወሰደዉ እርምጃ በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል" ሲል አመልክቷል። እስካሉን የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ የተጣራ መረጃ አልተገለጸም።

💥 ተመሳሳይ የተኩስ ልውውጥ በጊምቢና በደምቢዶሎ፦

- በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ከተማ ከማለዳ 12:30 ጀምሮ በጣም የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልጸውልናል።

- በሌላ ደምቢዶሎ ከተማ ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ ከባድ የተባለ ተኩስ ልውውጥ እንደነበር የቲክቫህ ደምቢ ዶሎ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል።

- የተኩስ ልውውጡ መንግስት ሽብርተኛ ብሎ በህ/ተ/ም/ቤት የፈረጀው ሸኔ (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ነው የሚጠራው) እና በመንግስት ሀይል መካከል ነውም ብለዋል።

- በተኩስ ልውውጡ ጉዳት ስለ መድረሱ እንደሰሙ ያመለከቱት የቤተሰብ አባሎቻችን ከቤት መውጣት እንዳልቻሉና የኤሌክትሪክ አገልግሎትም እንደተቋረጠባቸውም ጠቁመዋል። በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ያለው ነገር የለም።

👉 የጠ/ሚ/ሩ ምላሾች

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት እየተነሳላቸው ላለው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ያነሷቸውን ጉዳዮች እና ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡባቸውን በዚህ ተያይዟል : https://telegra.ph/የጠሚሩምላሾች-06-14

ችሎት

- በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ቻሎት ዛሬ ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አቃቤ ህግ ቀርቦ ተጨማሪ 15 የክስ መመሥረቻ ቀን ጠይቆ ተፈቅዶለታል ስለሆነም ለሰኔ 22/2014ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ተቀጥሯል።

- በተመሳሳይ ጋዜጠኛ መዓዛ እንዲሁም ጋዜጠኛ ሰለሞን ላይ የተጠየቀው 14 ቀን ቀጠሮ ውድቅ አድርጎ 5ቀን ተቀጥረዋል።
ረጅም ሰአትዎን ተቀምጠው ወይም መኪና እየነዱ ያሳልፋሉ ?
ስልክ ፦  0911284606
አንግዲያዉ Memory Foam Seat Cushion አስመጥተንሎታል።
-ቢሮ ተቀምጠው ለሚሰሩ
-ለሹፌሮች በጣም አስፈላጊ
- የወገብ የጀርባ እና የዳሌ ህመምን የሚቀርፍ ፣
-የኩላሊት ህመም ላለባቸው ምቾት የሚሰጥ
-ለኪንታሮ ህመምተኞች
መቀመጫው 650 ብር 
የጀርባው  550ብር
ያሉበት ድረስ በነፃ እናደርሳለን።
(አድራሻ ፡ ቦሌ ወሎ ሰፈር
Register at https://www.effsaa.org/short-term-training-program-registration-form/ after the settlement of the training fee.
Venue
At the training hall of Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) which is located at Kazanchis, Nigist Towers Hotel & Apartments 4th Floor (In front of Elilly International Hotel)
For More Information,
Call us at +251 115 589045 / +251 903 182525
OR
Visit our telegram channel
https://t.iss.one/EFFSAAOfficial
TIKVAH-MAGAZINE
#ጤናረቡዕ : ኩላሊት እና አንጀት ምን ያገናኛቸዋል? ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ ያለን ትርፍ ውሃን፣ጨውንና በደማችን ውስጥ ያለን ቆሻሻ በማጣራት ሽንትን ያመርታል፡፡ የኩላሊት ህመም ማለት ኩላሊታችን መጎዳቱን እና በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ተግባር በአግባቡ ማከናወን አለመቻሉን የሚገልፅ ነው፡፡ አንጀት እና ኩላሊት በጥምረት ሰውነታችን ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ያስወግዳሉ። በጤነኛ የሰውነት ሁኔታ ውስጥ…
#ጤናረቡዕ : ጤናማ አንጀት፣ ጤናማ ኩላሊት ክፍል ፪

ኤሌክትሮላይቶች ምንድን ናቸው?

ኤሌክትሮላይት በሰውነታችን ፈሳሽ ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኙ ኬሚካሎች ናቸው፡፡እነዚህም ክሎራይድ፣ ሶድየም እና ካልሺየምን ያካትታሉ፡፡

ኤሌክትሮላይቶች ለጤነኛ እና ለተመጣጠነ የሰውነት ተግባር አስፈላጊ ሲሆኑ በተመጣጠነ እና ለሰውነት በሚያስፈልገው ልክ መገኘት አለባቸው፡፡

ብዙ ሰዎች ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑትን ኤሌክትሮላይቶች ከምግባቸው ውስጥ ያገኛሉ፤ሆኖም በሰውነት ውስጥ በሚካሄዱ አንዳንድ ሂደቶች ምክንያት በእነዚህ ኤሌክትሮላይቶች መጠን ላይ መዛባት ይከሰታል፡፡

መንስኤው ምንድን ነው?

የኤሌክትሮላይቶች አለመመጣጠን ከሚከሰትባቸው ምክንያቶች አንዱ ብዙ የሰውነት ፈሳሽን በአንድ ጊዜ ስናጣ ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙ የሰውነት ላብ እና ማስመለስ ሲኖረን በሰውነታችን ውስጥ ያለ የኤሌክትሮላይቶች መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የኤሌክትሮላይቶች መጠን መዛባት ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ከኤሌክትሮላይቶች መጠን መዛባት ምልክቶች ውስጥ የተወሰኑት፡-

· ቁርጠት

· የማዞር ስሜት

· ከመደበኛው የተለየ የልብ ምት

· ድካም

በአንጀት ቁስለት ህመም ምክንያት የሚከሰት የሰውነት ፈሳሽና ኤሌክትሮላይት መጠን መዛባትና የኩላሊት ህመም
በርከት ያሉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአልሰሬቲቭ ኮላይተስና በክሮንስ ህመም ታካሚዎች ላይ የሚከሰት የኤሌክትሮላይቶች እጥረት አነስ ያለ ጉዳትን ከማስከተል ጀምሮ ለህይወት እስከሚያሰጋ ደረጃ ድረስ ሊደርስ እንደሚችል ነው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት በተለይም በአንጀት ቁስለት ህመም ንቁ የህመሙ ደረጃ ላይ በአንጀት ግድግዳ ንጣፍ ቁስለት ምክንያት የሚከሰት የአንጀት መዋቅር ለውጥ የሰውነታችን ኤሌክትሮላይቶች በአስፈላጊው መጠን እንዳይመረቱና ወደ ሰውነታችንም እንዳይመጠጡ በማድረግ የኤሌክትሮላይቶችን መጠን መዛባት ያስከትላል፡፡

የኤሌክትሮላይቶች መጠን መዛባት እንዳይከሰት ምን ማድረግ እንችላለን?

1. ዉሃን መጠጣት ፡- ዉሃን መጠጣት ቀላሉና ወሳኙ በኤሌክትሮላይቶች መጠን መዛባት ምክንያት የሚከሰቱ ውስብስብ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ልንከላከልበት የምንችለው መንገድ ነው፡፡

2. በኤሌክትሮላይት የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ፡- እንደ ካሮት፣አቮካዶ፣ብርቱካን፣ሙዝ፣እንጆሪና ሰላጣ ያሉ ምግቦችን መመገብ

በሰፊው ለማንበብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ⬇️⬇️

https://telegra.ph/Healthy-Gut-Healthy-Kidney-06-14

በቀጣይ ሳምንት የኩላሊት ስፔሻሊስት በቀጥታ ስርጭት ይዘን የምን ቅርብ ሲሆን ያሎትን ጥያቄዎች በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ወይንም በግል በ @IBDETHIOPIA ማስተላለፍ ይችላሉ።

በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ

Tikvah Magazine

Crohn’s & Colitis Ethiopia
TIKVAH-MAGAZINE
ትላንት ጥዋት አንድ የአዲስ አበባ ቤተሰባችን አባል ያጋጠመውን አጋርቶናል። ከ24 ወጥቶ ወደ ኢምፔሪያል በሚወስደው መንገድ አንድ እግረኛ ላይ በ " ኮድ 2 AA 16429 " ታርጋ የነበሩ 4 ሰዎች አንቀውት መሬት አስተኝተው ሲፈትሹት መመልከቱን ገልጿል። በወቅቱ ይኸው እግረኛ ላይ ይህ ድርጊት ከፈፀሙ ግለሰቦች አንዱ አካባቢውን ሲቃኝ የነበረ ሲሆን መሳሪያ አውጥቶ እንዳሳየውና በኃላ ሊከተላቸው ቢሞክርም…
" አመሰግናለሁ "

ትላንት አንድ የአዲስ አበባ ቤተሰባችን አባል ከ24 ወጥቶ ወደ ኢምፔሪያል በሚወስደው መንገድ አንድ እግረኛን በመኪና የነበሩ 4 ሰዎች አንቀውት መሬት አስተኝተው ሲፈትሹት መመልከቱን ጥቆማ ሰጥቶ ነበር።

ምናልባት ይህ የዝርፊያ ተግባር የተፈፀመበት ወገናችን ታርጋውን ካላየው በሚልም ታርጋውን አጋርቶ ነበር።

ይህንንም ጥቆማ ተከትሎ አንድ የቤተሰባችን አባል ጥቃቱ የተፈጸመው በእርሱ ላይ መሆኑንና ዘራፊዎቹ ስልኩንና ዋሌት ቦርሳውን እንደወሰዱበት ገልጿል።

ይሄው የቤተሰባችን አባል ወንጀሉ የተፈጸመበትን የመኪና ተርጋ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጉን አስታውቋል።

ጥቆማውን ላደረሰው የቲክቫህ ቤተሰብ አባልም ምስጋና አቅርቧል።

መልዕክቶቻችን ማጋሪያ ፦ @tikvahethiopiaBOT

@tikvahethmagazine
ወልድያና አካባቢዋ በጭጋግ በታገዘ ለከፍተኛ አቧራ ብናኝ ተዳርጋለች፤ ከተማ አስተዳደሩ ማሰሰቢያ ሰጥቷል።

ወልድያ ከተማና አካባቢዋ በትላንትናው ዕለት በግምት ከቀኑ 10:00 ሰዓት በኋላ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የአቧራ ብናኝ መከሰቱን ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

ጫጋጋማው ብናኝ አዳሩንም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን፤ ክስተቱ ለጊዜው መነሻው በትክክል ባይታወቅም በአስፋልት ግንባታ ምክንያት ተቆፎሮ ሲነሳ የነበረው አቧራ ጋር ተዳምሮ አካባቢውን በከፍተኛ ሁኔታ በክሎታል።

ይኽ ከፍተኛ የአቧራ ብናኝ ለተለያዬ የጤና እክል የሚዳርግ በመሆኑ ሕዝቡ ማስክ በመልበስ የተለየ ጥንቃቄ በማድረግ የእራሱንም የአካባቢውንም ጤና በመከላከል የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📹 ጋዜጣዊ መግለጫ : ለአንድ ዓመት ጊዜ ዝግጅት ተደርጎበታል የተባለው የመጀመሪያው የሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ በሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን አዘጋጅነት ሰኔ 22 ይካሄዳል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE

በቻይና ሀገር ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ያቋረጡትን ትምህርት እንዲከታተሉ ተፈቅዷል።

ትምህርት ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ይሄንን ተከትሎ የቻይና መንግስት ባወጣው የኮቪድ- 19 ፕሮቶኮል ምክንያት በአጋጣሚ ወደሀገራቸው መጥተው መመለስ ያልቻሉ ተማሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት እና በቻይና ሀገር የሚገኘው ኤምባሲ ባደረጉት ጥረት የቻይና መንግስት ተማሪዎች ተመልሰው ያቋረጡትን ትምህርት እንዲከታተሉ መፍቀዱን አሳውቋል።

ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘው ፎርም መሰረት ተማሪዎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላት እጅግ ቢዘገይ እ.ኤ.አ. እስከ June 20/2022 ብቻ በሚከተለዉ ማስፈንጠሪያ በመግባት ፎርሙን ሞልተው በተከታዩ ኢሜይል አድራሻ እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

Link- https://moe.gov.et/AddReso

Email፡ [email protected],
[email protected]

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ግዙፍ የውጪ ድርጅቶች በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያሳደሩ ይገኛሉ። የተለያዩ ዘርፎች ላይ ብቁ የሰለጠነ የሰው ኃይልም በመፈለግ ላይ ይገኛሉ።

መልኅቅ ማርኬቲንግ እና ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩትም በሽያጭ እና ማርኬቲንግ፣ በዲጂታል ማርኬቲንግ እና በማይንሴት የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ ስለሚገኝ ከአስር ዓመታት በላይ ልምድ ባካበቱ አሰልጣኞች በተግባር ሰልጥነው ተፈላጊነትዎን ይጨምሩ!

አሁኑኑ በ0967280828 ይደውሉና ቦታዎን ያስይዙ! የተረጋገጠ የስራ ዕድል እና የምክክር (Mentorship) አገልግሎትም ያገኛሉ!

#MelhikMarketingandLeadershipInstitute #MMLI #Salesandmarketing #Digitalmarketing #Mindset #Training
የሰኔ ወር የመጨረሻው ድንቅ ጉዞ ወደ አዋሽ ብሔራዊ ፖርክ እና ድሆ ሎጅ

የጉዞ ቀን:-ሰኔ 11 /2014 | መመለሻ :-ሰኔ 12 /2014
👉 ከሃገር ውጪ ያላችሁ ሃገር ቤት ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻችሁ ይህን ምርጥ ጉዞ በመጋበዝ ሰፕራይዝ ያድርጉ

የምንጎበኛቸው፦ |በተፈጥሮ የታደለውን የአዋሽ ፓርክ| አዋሽ ፏፏቴ| ተፈጥሯዊ ፍልውሃ ከ 40-50c በሚደርስ ውሃ መታጠብ| ዋና በድሆ ሎጅ|

ክፍያ የሚያጠቃልለው፦ | የድንኳን አዳር ፓርኩ ውስር | አንድ ምሽት ካምፕፋየር 🚎 ትራንስፖርት | 🍽 ምግብ,( ቁርስ ምሳ እራት ) ሻይ ቡና | 💧 የታሸገ ዉሃ |🚶አስጎብኚ ስካውት | የፓርክ መግቢያ | ፎቶ ያጠቃልላል|

መነሻ ቦታ ሜክሲኮ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት መገኛ ሰዓት 11:30 መነሻ 12:00 ሰዓት

ዋጋ በአንድ በሰው :- 3500
ለበለጠ መረጃ 👉 የቴሌግራም ግሩፖችንን ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/mirt_haikinhg
📞0962 26 78 20 or @yeneneh
አዘጋጅ፦ የኔነህ ፊልም ፕሮዳክሽን
TIKVAH-MAGAZINE
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ''ፋይላችን ጠፋብን'' የሚለውን ቅሬታ ለመፍታት የፋይል ማደራጀት ዘመቻ እየተከናወነ ነው ተብሏል። በአዲስ አበባ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት ከግንቦት 18 ቀን/2014 ጀምሮ እስከ ሰኔ 08/2014 የሚሰጠውን መደበኛ አገልግሎት በጊዜያዊነት በማቆም ፋይሎቹን በተደራጀ እና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ኮድ ለመስጠት ሁሉንም የጽ/ቤቱን ሰራተኞች በማስተባበር በዘመቻ…
#UPDATE

በአዲስ አበባ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተደደር ጽ/ቤት ላለፉት 15 ቀናት መደበኛውን አገልግሎት በማቆም ፋይል የማደራጀት ሥራ አጠናቆ ዛሬ መደበኛ ሥራውን በአዲስ መልክ መጀመሩን የክፍለ ከተማው የመሬት ልማት እና አስተደዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ዑመር ገልጸዋል።

ቢሯቸው ዛሬ ተገልጋዮችን ተቀብሎ ማስተናገድ መጀመሩን አንስተው ''በቀን የምናስተናግደውን የተገልጋይ ቁጥር ስታንዳርድ አውጥተን እያስተናግድን እንገኛለን'' ብለዋል።

በተጨማሪም በክፍለ ከተማው ከ2000 በላይ የልማት ተነሺዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊዋ ይህን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ እንደሆነም ተናግረዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
እስካሁን 37,726 ኢትዮጵያውያንን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ኢትዮጵያ ሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩና ለችግር የተጋለጡ ዜጎቿ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራች ትገኛለች።

በዛሬው ዕለትም በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 17 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 37,726 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot