TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ በአጠቃላይ አቃቢ ህግ በእኔ ላይ መስርቶ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸውን ወንጀል አልፈጸምኩም” - አቶ ክርስቲያን ታደለ

እነአቶ ክርስቲያን ታደለ ዛሬ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ጉዳዩን ከሚከታተሉ ሰዎችና ቃላቸውን ካቀረበበት ሰነድ መረዳት ትችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው አቶ ክርስቲያን የእምነት ክህደት ቃል የሰጡበት ሰነድ፣ “በአጠቃላይ አቃቢ ህግ በእኔ ላይ መስርቶ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸውን ወንጀል አልፈጸምኩም። ጥፋተኛም አይደለሁም” ይላል።

አቶ ክርስቲያን በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ምን አሉ?

“ለ550 ቀናትም በግፍና ጭካኔ እገታ ውስጥ የምገኘው ለአንዲት ደቂቃ እንኳን በጥፋተኝነት የሚያስቀጣ አንዳችም የወንጀል ድርጊት የሚያቋቁም የህግ መተላለፍ ስለፈጸምኩ አይደለም። የአማራ ሕዝብ የሚያነሳቸውን የህልውና ጥያቄዎች በይፋ በማቅረቤ፣ በሕዝቤ የሚደርሰውን ግፍ፣ በደል በማስረጃ በመሞገቴ፣ የገዢውን ፓርቲ አፈናና የመንግስት አሰራሮችንና አመራሮችን ብልሹነትና ዘረፋ በመታገሌ ነው ” ብለዋል።

“ ተደጋጋሚ የአመራር ብልሹነት ባሳዩ አካላትም የወንጀልና የፍትሃብሔር ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ክስ እንዲመሰረት ፍትህ ሚኒስቴር አዝዥለው ” የሚሉና ሌሎች ድርጊቶችን በአደባባይ እንደታገሉ ገልጸዋል።

“ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በአሰራራቸው የፋይናንስ ገልጸኝነትና ህጋዊነት እንዲከተሉና እንዲረጋገጡ እንዲሁም ኦዲት ለመደረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቄከለሁ ” ነው ያሉት።

እነዚህን ጥያቄዎች እንዳልጠይቅ አንዳንድ አመራሮች ለማግባባት እንደሞከሩ ገልጸው፣ “ አንዳንዶቹም ሊገድሉኝ፣ ሊያስሩኝና አንዳች ነገር ሊያደርሱብኝ እንደሚችሉ ጭምር ነግረውኛል፤ መልዕክትም አድርሰውኛል ” ብለዋል።

“ አንዳች ወንጀል አልፈጸምኩም ” ያሉት ክርስቲያን፣ “ ይህን በተመለከተ ከክሱ ይዘት ብቻ ሳይሆን በራሴ መንገድ ይህን ክስ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብብኝ ካደረገው አካል ዘንድም አረጋግጫለሁ ” ሲሉ አስረድተዋል።

“ እኔ አማራ የሆንኩት አማራ ሆኘ ስለተወለድኩ ነው። የከማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ የሆንኩትም ፈቅጄ፣ መርጨና ወድጄ ነው። በየትኛውም ቦታና ሁኔታ ለአማራነቴ ጥብቅና መቆምም ተፈጥሯዊ ግዴታዬ ነው ” ብለዋል።

“ አማራዊ እሴቶታችን ለኛ ቅዱስ ነው ” ብለው፣ “ ይሁንና አቃቢ ህግ ባቀረበው የፓለቲካ ውንጀላ ሰነድ ላይ፣ ‘አማራ ርስቱን ተቀምቷል፤ አገሪቱ በአማራ እሴት መመራት አለባት’ የሚል የርዕዮተዓለማዊ አቋም መያዛችን ክስ ሆኖ ቀርቧል” ብለዋል።

“ ይህ የአቃቢ ህግ ክስ ግን መንግስት ከአማራና ከአማራነት የጸዳች ኢትዮጵያ ነው ወይ የሚፈልገው ? የሚል ሙግት ያስነሳል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከአማራና ከአማራነት በስተቀር እንዲሆኑ የሚደነግግ ህግስ አለ ወይ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል “ በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ‘ቋሪትና ደጋ ዳሞት ላሉ የሽብር ቡድን አስተባባዎች በስልክ ሐምሌ 25/2015 ዓ/ም በመደወል መከላከያን ማጥቃት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በማሳወቅ እንዲመቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል’ ” ማለቱን ጠቅሰል።

“ አቃቢ ህግ ለዚህ ክስ አስረጅ የሆነ አንዳችም ማስረጃ አላቀረበም ” ብለዋል።

(ሙሉ የእምነት ቃላቸውን የሰጡበት ሰነድ ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከግምገማ በኋላ በደረስንበት ውጤት ነዋሪዎቹ መቶ በመቶ ጥፋተኞች ናቸው " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ለኮንስትራክሽን ሥራ በገቡ እና እንዲነሱ ባልተደረጉ ቆጣሪዎች ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ከእነዚህ ቆጣሪዎች በህገወጥ መንገድ ሃይል እንዲጠቀሙ ምክንያት ሆኗል መባሉ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተመዘገቡት ቆጣሪዎች…
➡️ " ቆጣሪው መንገድ ላይ ያለ በመሆኑ ማንም ሰው እየቀጠለ ይጠቀማል ሌሎች በተጠቀሙት እኛ ልንጠየቅ አይገባም " -ነዋሪዎች

🔴 " ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን መረጃ ከእናንተ እንፈልጋለን " -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


በቦሌ አራብሳ ሳይት 3 ብሎክ 534 እና 535 ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር የገቡበትን ውዝግብ በሚመለከት የአገልግሎቱ የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ በአካባቢው በመገኘት እውነታውን መመልከት እንደሚቻል ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ያለውን እውነታ ለመመልከት እና ቅሬታውን ለመፍታት ከቀናት በፊት የአገልግሎቱ የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር ፣ የሪጅኑ የህግ ክፍል፣ የጸጥታ አካላት እና ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ምልከታ ተደርጓል።

በምልከታው ወቅትም የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብም በቦታው በመገኘት ከአገልግሎቱ ሃላፊዎች እና ነዋሪዎች እውነታውን ለመመልከት ጥረት አድርጓል።

አገልግሎቱ በአራብሳ የጋራ መኖሪያ መንደር ሳይት ሶስት ሃይልን ከቆጣሪ ላይ በህገወጥ መንገድ ቀጥለው ሲጠቀሙ እንደተደረሰባቸው በመግለጽ የቆጣሪውን እዳ እንዲከፍሉ በማሳወቅ ሃይል ያቋረጠባቸው ብሎኮች 534፣ 535፣ 550 እና 551 ናቸው።

የቲክቫህ አባል ቦታው ተገኝቶ እንደተመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት " በህገ-ወጥ መንገድ ቆጣሪን እንዳይቆጥር በማድረግ ሃይል ሲጠቀሙ እንደነበር ደርሼበታለሁ " በማለት ሃይል ካቋረጠባቸው አራት ብሎኮች ውስጥ ሁለቱ ማለትም ብሎክ 550 እና 551 ሃይል ተቀጥሎላቸው አገልግሎት እያገኙ ነበር።

የእነዚህ ቆጣሪዎች እዳ ባልተከፈለበት እና ከሌሎች ብሎኮች ጋር በጋራ ሃይል በተቋረጠበት ሁኔታ ለእነርሱ በማን እና በምን ሁኔታ ተቀጠለ ? የሚል ጥያቄ ለሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ዳይሬክተሩም ፤ የቆጣሪዎቹ እዳ ባልተከፈለበት ሁኔታ የእነሱ ሃይል መጠቀም ከእርሳቸው እውቅና ውጪ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተቋረጠ በኃላ በራሳቸው ሃይሉን ቀጥለው ይጠቀሙ ወይስ የአገልግሎቱ ሰው ቀጠለላቸው የሚለውን ጉዳይ ማጣራት በማድረግ " አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

በመቀጠለም ምልከታ የተደረገው ብሎክ 534 እና 535 ላይ ሲሆን እነዚህ ብሎኮች " ሃይል በህገ ወጥ መንገድ ቀጥለው ሲጠቀሙ በኢንስፔክሽን ወቅት ተገኝተዋል " በሚል ሃይል ከተቋረጠባቸው ወር እንዳለፋቸው ተናግረዋል።

አገልግሎት በበኩሉ " ሃይሉን ያቋረጥኩት ከጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች ለአንድ ዓመት ከአራት ወር በላይ ቀጥዬ ተጠቅሚያለው ያሉ እና የሚጠቀምም ስለመኖሩ በደረሰኝ ጥቆማ መሰረት ነው " ብሏል።

ነዋሪዎች ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ቀጥለው አለመጠቀማቸውን ተከራክረዋል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሞያዎች ግን የቆጣሪውን ሃይል ባቋረጡበት ወቅት እነዚህ ብሎኮች መጨለማቸውን እንደማስረጃ በመጥቀስ ሃይል በህገወጥ መንገድ እየተጠቀሙ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል።

" ሃይል የተቋረጠብን ለብሎካችን የገባው ስሪ ፌዝ ቆጣሪ በመቆረጡ እንጂ ከተጠቀሰው ቆጣሪ ላይ ሃይል አልቀጠልንም " ሲሉ የተከራከሩት ነዋሪዎች " ቆጣሪው መንገድ ላይ ያለ በመሆኑ ማንም ሰው እየቀጠለ ይጠቀማል ሌሎች በተጠቀሙት እኛ ልንጠየቅ አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።

" ከጋራ መኖሪያ ብሎኩም የተጠቀመ ቢኖር ለይቶ እነሱን ተጠያቂ ማድረግ የአገልግሎቱ ሃላፊነት ነው ሁሉም ባላጠፋው ለወር ያህል ነዋሪው ለምን ይቀጣል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

አገልግሎቱም በምላሹ " ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን መረጃ ከእናንተ እንፈልጋለን " ቢልም ነዋሪዎች ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ በመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሪጅኑ ዳይሬክተር በቦታው በተገኙበት ወቅት ለነዋሪዎች መፍትሔ ለመስጠት ሃይሉን እንዲቀጠልላቸው ያደረጉ ሲሆን ለህገ ወጥ ድርጊት ምክንያት የተባለውን ቆጣሪም ከቦታው እንዲነሳ አድርገዋል።

ዳይሬክተሩ አቶ ብርሃኑ ሲጠቀሙ የነበሩትን አካላት ማንነት ከነዋሪዎቹ ወይም ኮሚቴዎቹ ማግኘት እንደሚፈልጉ እና በጊዜ ሂደት ማንነታቸውን የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ ሃይሉ በድጋሚ እንዲቀጠል በተደረገበት ወቅት በብሎኩ ካሉ ሁለት ቆጣሪዎች ለመታዘብ እንደተቻለው 1,500 ብር የተሞላው በ19/02/17 ዓ/ም የነበረ ቢሆንም ሃይል እስከተቋረጠበት 15/04/17 ዓም ድረስ ባለው ሁለት ወር ውስጥ ከካርዱ ጥቃም ላይ የዋለው ከ 10 ብር በታች ሆኖ ተገኝቷል።

" ቆጣሪው ሲገናኝ ያሳየው የብር መጠን 1,492. 5  አና 1,455.32 ብር ነው ይህ ማለት በ2 ወር ጊዜ ውስጥ የተጠቀሙት ከ10 ብር በታች ነው ይህ ሁሉ ህብረተሰብ በ10 ብር 2 ወር ሊጠቀም አይችልም ያማለት ቀጥታ ሲጠቀሙ እንደነበር ተጨባጭ ማስረጃ ነው " ሲሉ አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።

በብሎኮች በመዟዟር በተደረገው ምልከታ በቀጥታ ያለቆጣሪ ከመስመር ላይ በመቀጠል ሃይል የሚጠቀሙ ሰዎች ስለመኖራቸው ለመታዘዘብ ተችሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia