TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ብርሃኑ አዴሎ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ዕጩ ሆነው ቀረቡ። በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ዘመነ መንግስት የሚኒስትሮች ካቢኔ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ገብረማርያም ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነርነት ለመሰየም ዛሬ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ/ም ፓርላማ ቀርበዋል። ሌሎች አራት ዕጩዎችም መቅረባቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። አቶ…
#Update
አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።
ለሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮምሽነር በመሆን የተመረጡት አቶ ብርሃኑ በህዝብ ተወካዮሽ ምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
አቶ ብርሃኑ የቀድሞው የምክር ቤት አባል የነበሩ ሲሆን የአዕምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር፣ በኢህአዴግ ዘመን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
ላለፉት 10 ዓመታት ደግሞ በጥብቅና በህግ ማማከር ስራ ላይ ቆይተዋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር የነበሩት ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የስራ ዘመናቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ራኬብ መሰለ በተጠባባቂነት ተቋሙን ሲመሩ ነበር።
@tikvahethiopia

በመቐለ ኤፍ ኤም 104.4 ምንድነው የተፈጠረው ? " በመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ላይ የአፈና እና የስራ አመራር የማባረር ሙከራ " መደረጉን ጣቢያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል። ሙከራው በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የመቐለ ከንቲባ እንዲሆኑ በተሾመቱ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ያስተባበሩት ነው ተብሏል። ዛሬ ጥር 21/2017 ዓ.ም የተካሄደው የአፈናና አመራር የመቀየር…
#Update
🔴" በ104.4 የመቐለ ኤፍኤም ያጋጠመው ችግር በመግባባት እንዲፈታ አድርጊያለሁ ስልጣን መረከብ የሚፈልግ አካል እና ግለሰብ ህግ እና ስርዓት ያክብር " - የመቐለ ከተማ ፓሊስ
➡" ሬድዮ ጣቢያችን ለሁለት የተሰነጠቁ ቡድኖች መጫወቻ እንዲሆን አንፈቅድም " - የመቐለ FM አመራር
ጥሪ 21 / 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት 5 ታጣቂዎች አስከትሎ የመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠረ ሙከራ ያደረገው ሬድዮ ጣብያውን እንዲመራ የመቐለ አስተዳደር " ሹሞኛል " የሚል ግለሰብ እንደሆነ የሬድዮ ጣቢያው አመራሮች ተናግረዋል።
ታጣቂዎች አስከትሎ ሬድዮ ጣብያውን ለመረከብ ሲሞክር የተፃፈለት ደብዳቤ በቦታው ለነበሩ አመራሮች ማሳየት ባለመቻሉ ምክንያት ግርግር እንዲነሳ ምክንያት መሆኑ አመራሮቹ ያብራራሉ።
ዘግይቶ በተደረገው ማጣራት የሹመት ደብዳቤ ማቅረብ ያልቻለውና ሬድዮውን ለመምራት መመደቡ የጠቀሰው ግለሰብ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት የከተማዋ ከንቲባ እንዲሆኑ በተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) መመደቡ በቃል እንደጠቀሰላቸው አመራሮቹ ገልጸዋል።
ጉዳዩን ወደ መቐለ ፓሊስ በመውሰድ ጊዚያዊ መፍትሄ ማግኘት መቻላቸው ከምስጋና ጭምር አስታውቀዋል።
የጣቢያው አመራሮች " በደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት በተሾመ ከንቲባ ሬድዮ ጣብያውን ለማስተዳደር መመደቡን የሚናገረው ግለሰብ የአገሪቱዋ የሚድያ ህግ በሚጥስ አካሄድ ከአንድ ክፍለ ከተማ ያሰባሰባቸው ታጣቂዎች በማስከተል የአፈና ተግባር ለመፈፀም መመኮሩ የህወሓት በሁለት መሰንጠቅ በክልሉ እያደረሰ ያለው ዘርፈ በዙ ችግር አንዱ ማሳያ ነው " ሲሉ አክለዋል።
" ከ15 ዓመት በላይ ያስቆጠረ እና ከ60 በላይ ሰራተኞች ያሉት የመንግስት የኤፍኤም ሬድዮ ለሁለት የተሰነጠቁ ቡድኖች መጫወቻ አይሆንም " ያሉት አመራሮቹ በአገሪቱ የብሮድካስት ህግ የሚተዳደር ሚድያ መሆኑ በመግለፅ ተመሳሳይ አፈና እንዳይፈፀም በግለሰቡ እና በላከው አካል ላይ ክስ እና አገዳ እንዲጣል እንቅስቃሴ መጀመራቸው አስታውቀዋል።
የመቐለ ፓሊስ በፅሁፍ ባወጣው መግለጫ የአፈና ተግባሩን አውግዞ ፤ ችግሩ በመግባባት መፍታቱን እና ወደ ሃላፊነት መምጣት የሚፈልግ አካል እና ግለሰብ ህግ እና ስርዓት አክብሮ መሆን ይገባዋል ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo
#Update
" ወደ ቀን መርሃግብር ተቀይረን እንድንማር ከመግባባት ላይ ተደርሷል " - ተማሪዎች
ሰሞኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) መረሃግብር በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በግል ከፍለዉ መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት " ተመዝግበንና አስፈላጊውን ክፊያ አጠናቀን ትምህርት በመጀመር ሂደት ዉስጥ ባለንበት ዩኒቨርሲቲው ' አናስተምራችሁም ' ብሎናል " ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ዩኒቨርሲቲዉ በበኩሉ ጉዳዩን ከትምህርት ሚንስቴር ጋር በመነጋገር ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፆልን ነበር።
ቅሬታ አቅርበዉ የነበሩ ተማሪዎችና ወላጆች በዛሬው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳስታወቁት ዩኒቨርሲቲው የትምህርት መርሃግብሩን ከእረፍት ቀናት ወደ መደበኛ መርሃግብር በማዘዋወር ተማሪዎቹን ለማስተማር መወሰኑን አረጋግጠዋል።
" ዛሬ ተጠርተን ዉል ተፈራርመናል " ያሉት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) አመልካቾች " በዉሉ ላይ የተቀመጡ ጉዳዮች የመረሃግብሩ ከዕረፍት ቀናት (weekend) ወደ መደበኛ መቀየር ፣ አመልካቾች በግል ከፍለዉ የሚማሩ ስለመሆናቸው የሚገልፅ፣ ስለ ክፍያ አፈፃፀምና በዩኒቨርሲቲው እና በተማሪዎቹ መካከል ስለሚኖረዉ መብትና ግዴታ የሚደነግግ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
የተማሪ ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " ከከፍተኛ ጭንቅ ነዉ የገላገላችሁን፣ ምን እንደምናደርግ ጨንቆን ነበር ትምህርት ሚንስቴር እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲም ላሳያችሁን በጎ ምላሽ እናመሰግናለን " ብለዋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በግል ከፍሎ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ለሚወስዱ ተማሪዎች ያዘጋጀዉን ዉል በዚህ መረጃ ላይ ያካተትን ሲሆን የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አክበር ጩፎ ስለጉዳዩ ትክክለኛነት ከመግለፅ ባለፈ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW

Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update
" እስካሁን በህይወት የተገኘ የለም "
በአሜሪካ ፤ ዋሽንግቶን ዲሲ የመንገደኞች አውሮፕላን ከጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ በ " ፖቶማክ ወንዝ " ውስጥ ከተከሰከሰበት አደጋ የነፍስ አድን ሰራተኞች እስካሁን አንድም ሰው በህይወት አላገኙም።
የነፍስ አድን ስራው ግን መቀጠሉ ተነግሯል።
አውሮፕላኑ 60 መንገደኞችን እና 4 የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ነው 3 ሰው ከያዘው የጦር ሂሊኮፕተር ጋር ተላትሞ የተከሰከሰው።
@tikvahethiopia
" እስካሁን በህይወት የተገኘ የለም "
በአሜሪካ ፤ ዋሽንግቶን ዲሲ የመንገደኞች አውሮፕላን ከጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ በ " ፖቶማክ ወንዝ " ውስጥ ከተከሰከሰበት አደጋ የነፍስ አድን ሰራተኞች እስካሁን አንድም ሰው በህይወት አላገኙም።
የነፍስ አድን ስራው ግን መቀጠሉ ተነግሯል።
አውሮፕላኑ 60 መንገደኞችን እና 4 የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ነው 3 ሰው ከያዘው የጦር ሂሊኮፕተር ጋር ተላትሞ የተከሰከሰው።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በመቐለ ከተማ በከንቲባ ስም ማንኛውም ተግባር እንዳይፈፅም አስጠነቀቁ።
አቶ ጌታቸው በእፅንኦት ያስጠነቀቋቸው ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት እጩ አቅራቢነት ከንቲባ በመሆን የተሾሙትን ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ነው።
ፕሬዜዳንቱ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ፅፈውት ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች ይፋ በሆነው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ ፤ በከተማዋ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቅቡልነት ባጡ ከንቲባ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) በተፃፈ ደብዳቤ ማንኛውም ስራ መፈፀም የህግ ተጠያቂነት አንደሚያስከትልባቸው ያትታል።
ዶክተሩ ህገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲያቆሙ የሚያሳስበው እና የሚያስጠነቅቀው ደብዳቤው ጊዚያዊ አስተዳደሩ የሚፃረር አቋም በመያዝ ከተማዋ መምራት አግባብነት የለውም ይላል።
ስለሆነም በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቅቡልነት በሌላቸው ከንቲባ የሚሰጣቸው ማንኛውም ዓይነት ትእዛዝ እንዳይቀበሉ የፕሬዜዳንቱ ደብዳቤ አስጠንቅቋል።
ህወሓት ለሁለት በመሰንጠቁ ምክንያት የመቐለ ከተማ ላለፉት 60 ቀናት ቢሮ ገብቶ የሚደራ ከንቲባ የላትም።
ህዳር 23/2017 ዓ.ም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ደብዳቤ የተሾሙ ብርሃነ ገ/የሱስ አንድ ቀን ብቻ በአስተዳደሩ ግቢ ታይተው ለሁለተኛ ጊዙ አልተመለሱም።
በደብረፅዮኑ ህወሓት የተሾሙ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ከህዳር 23 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ቢሮ አልገቡም።
የመቐለ ከንቲባ ቢሮ አሁንም ታሽጎ በፓሊሶች ይጠበቃል፤ የከተማዋ ነዋሪ ደግሞ ከከንቲባ ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት አጥቶ አቤቱታውን ለማን ማቅረብ እንዳለበት ግራ ገብቶት ይገኛል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት በይፋ ተመሰረተ።
ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ የመረጠ ሲሆን የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ደጀን በርሀ (ዶ/ር) በከፍተኛ ድምፅ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል።
የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤት የማቋቋም ሃሳብ የክልሉ ምክር ቤት የሚያፈርሰው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተከትሎ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ማቋቋምያ ሰነድ ጥር 2015 ዓ.ም ሲፀድቅ የተነሳ ሃሳብ ነው።
ሃሳቡ በድጋፍ እና በተቃውሞ ለሁለት አመታት ያህል ሲናጥ ቆይቶ ዛሬ ጥር 25/2017 ዓ.ም በይፋ ተመስርቶ መሪዎቹ መርጠዋል።
በምስረታ ካውንስሉ መልእክት ያስተላለፉት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ የሚገኙ የኢሮብ እና ኩናማ ብሄረሰቦች የተወከሉበት ካውንስሉ ዘግይቶም ቢሆንም መመስረቱ መልካም ሆኖ አቃፊ ፣ አሳታፊ እና የሃሳብ ብዙህነት የሚንሸራሸሩበት መድረክ መሆን ይገባዋል ብለዋል።
የአማካሪ ካውንስል ምክር ቤቱ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተቀመጡት የትግራይ ህዝብ ጥቅሞች በተሻለ እና በአስተማማኝ እንዲመለሱ አጋዥ ሃይል ለማሰባሰብ አልሞ መቋቋሙን የጠቆሙት ፕሬዜዳንቱ " ልዩነቶቻችን በማጠበብ ለተሻለ ነገ በጋራ መስራት ወቅታዊ የትግራይ ጥያቄ ነው " ብለዋል።
የካውንስሉ እድሜ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የቆይታ ጊዜ መሆኑ ያስረዱት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ይህንን ታሳቢ በማድረግ የትግራይ ፓለቲካዊ ምህዳር ማስፋት እና ለነገ ማመቻቸት ዋነኛ ስራው መሆን እንደሚገባ አክለዋል።
ካውንስሉ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች መሬት ላይ እንዲወርዱ አጋዥ ሚና ከመጫወት በተጨማሪ የትግራይ ተደማጭነት እና የመደራደር አቅም የሚያጠናክር አቅጣጫ መከተል ይገባዋል ብለዋል ፕሬዜዳንቱ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት ለመምራት ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ቃለ ማህላ ፈፅሟል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አማካሪ ካውንስል ምክር ቤት መመስረት በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት እና ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ እና ሌሎች ተቃውሞውታል