TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🧕" የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ በመጣስ አሁንም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች / ልጆቻችን ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይገቡ ከልክሏል " - የተማሪዎች ቤተሰቦች 👉 " የተጣሰ የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የለም ፤ የትምህርት ህግ እና ደንብ ያከበሩ ተማሪዎች ወደ ክፍል ገብተው መማር ጀምረዋል ፤ ቀሪዎቹ እንዲመለሱ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ነን " - የአክሱም…
#ሂጃብ #ሰልፍ
በሂጃብ ጉዳይ ነገ መቐለ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው።
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሂጃብ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና የትምህርት ቢሮ ወሳኔና ትእዛዝ እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሄድ አስታውቋል።
ምክር ቤቱ ፥ የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ መደረጋቸውና ከትምህርት ገበታ መራቃቸው መግለጹ ይታወሳል።
በአክሱም የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሂጃብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ባለፉት ሁለት ወራት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለሦሥት ጊዜ ደብዳቤ የፃፈው እንዲሁም የፍርድ ቤት ትእዛዝ አልቀበልም በማለታቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ መገደዱን ገልጿል።
በዚህም ነገ ጥዋት 1 ሰዓት በመቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ አሳውቋል።
ሁሉም ፍትህ ፈላጊ የሰልፉ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርቧል።
ሰልፉ ከቀናት በፊት ዓርብ ጥር 9 ሊደረግ የነበረ ቢሆንም የጥምቀት በዓል ዋዜማ በመሆኑ ምክንያት ነው ለነገ የተዘዋወረው።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ ተከታታይ መረጃዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል ፤ ነገ ማክሰኞ ጥር 13/2017 በመቐለ ከተማ የሚካሄደውን ስልፍም ተከታትሎ ያቀርባል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

የትግራይ ጉዳይ ወዴት ? በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች እንደሆኑ የገለጹ መኮንኖች ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ' የተዳከመ ' ያሉት በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተነስቶ በሌላ እንዲዋቀር መወሰናቸውን ገልጸዋል። " የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ውሳኔ አሳልፈናል " ብለዋል። " በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ…
🚨#Alert
" የወጣው መግለጫ ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው ! " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
" ህጋዊ ያልሆነ ቡድን ደግፎ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማፍረስ ፤ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን እና ሰራዊቱን ለመበተን መንቀሳቀስ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ ጥር 15/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ስም የወጣው መግለጫ አላማውን የሳተ እና ሰራዊቱ ከተሰጠው ተልእኮ ውጭ ነው ብሏል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ " በሰራዊት ከፍተኛ አዣዦች ስም የወጣው መግለጫ እንደማያውቀው በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ያልተለመደ ተግባር ነው " ብሎታል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ " ያልተለመደ ተግባር " ሲል የገለፀውን ውሳኔ አስመልክቶ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን እና ሁኔታውን መርምሮ ዝርዝር ማብራርያ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
" በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ስም የወጣው መግለጫ ግልፅ የሆነ መፈንቀለ መንግስት ያወጀ እና የፕሪቶሪያውን ውል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው " ብሏል ጊዚያዊ አስተዳደሩ።
" ሃላፊነት የጎደለውን ውሳኔው ወደ ታች ለማውረድ ጥድፍያ የተሞላበት እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑ ደርሼቤታለሁ " ያለው የጊዚያዊ አስተዳደሩ " የሚያስከትለው አደጋው እጅግ ከፍተኛ መሆኑ በመረዳት ተግባሩ በአስቸኳይ መቆም አለበት " ሲል አስጠንቅቋል።
" መላው የፀጥታ አካላት ህገ-ወጥ ውሳኔው የህዝቡን ችግር የሚያባብስ የጦርነት አዋጅ እና ስርዓት አልበኝነት የሚያስከትል መሆኑ በመገንዘብ በፅናት እንድትቃወሙት ትእዛዙን ተግባራዊ እንዳታደርጉ አስታውቃለሁ " ሲልም አክሏል።

Photo
#Update
" ህዝቡ በመረጣችሁት መንገድ ይታገላችኋል " - በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት
በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ፤ ትናንት ጥር 15/2017 ዓ.ም " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠውን መግለጫ የሚቃወም መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም መግለጫው ፥ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራውን ህወሓት" የነሃሴው " ብሎ ሲጠራው ራሱን ደግሞ " ነባር " በማለት ገልጿል።
" የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ያወጡት መግለጫ የ " ነሃሴው ህወሓት ህዝቡን እና ሰራዊቱ ለመበታተነ የሰራው ክፋት ውጤት ነው " በማለት ገልፆታል።
" የነሃሴው ህወሓት ህዝብን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያልተቀበለው ጉባኤ በማካሄድ ነባሩን ህወሓት እንዲዳከም ሰርቷል " ሲል በአቶ ጌታቸው የሚመራው ህወሓት ፤ " ወታደራዊ አምባገንነት ታግሎ ዴሞክራሲያዊ እና ህዝባዊ መንግስት የጨበጠ ህዝብ ወደ ኋላ አይመለስም " ብሏል።
" የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ስም የወጣውን መግለጫ " የጦርነት አዋጅ ነው ፤ በህዝብ ላይ አፋኝ አስተዳደር የሚጭን ተቀባይነት የሌለውና የውድቀት ጥሪ " ሲል ገልጾታል።
" ህዝቡ በመረጣችሁት መንገድ ይታገላቹሃል " ያለው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " የጦርነት አዋጃችሁ የፕሪቶሪያ ስምምነት አፍርሶ ፤ ትግራይ ለአህጉራዊ ዓለምአቀፋዊ ተነጥሎ እና ውግዘት የሚዳርግ ህዝቡን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው " ሲል አክሏል።
የአነ አቶ ጌታቸው ቡድን መግለጫውን መላ የትግራይ ኃይል አባላት እንዲያወግዙት ጠይቆ " ህዝብን እና መንግስታችሁ በሚስጡዋችሁ አቅጣጫ ብቻ እንድትንቀሳቀሱ ጥሪያችን እናቀርባለን " ሲል አሳስቧል።
ህዝቡ እና ወጣቱ በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ገልጾ ይህንኑ በመገንዘብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትግሉ በማጠናከር ለመብቱ ለአንድነቱ እና ለህልውናው በመታገል የተደቀነበት አደጋ እንዲመከት ጥሪ አቅርቧል።
ለህዝቡ ፣ ለዳያስፓራ ፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ስም የወጣው መግለጫ እንዲያወግዙት ጠይቀዋል።
መግለጫውን ያወጡት አመራሮች ያለፈ ታሪካቸው ከሚያጎድፍ ተግባር በመውጣት አሁን የፈፀሙት ስህተት በአስቸኳይ እንዲያርሙ እና ታሪካቸው እንዲያድሱ ጥሪ አቅርቧል።

" ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል የተሰጠው መግለጫ የሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃሳብ እና ውሳኔ እንዳልሆነ ለኢትዮጵያ መንግስት እናሳውቃለን " - የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መግለጫ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው (null and void እንዲሆን) ወስኗል።
" በሰራዊቱ የኮር አመራር የሚል አደረጃጀት እውቅና የለውም " ሲል የወሰነው ካቢነኔው " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ጥር 14/2017 ዓ.ም የተሰጠውን መግለጫ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል።
ካቢኔው ዛሬ ቅዳሜ ጥር 17/2017 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ፤ "የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መግለጫ ፦
- ለአንድ ቡድን የወገነ
- መንግስት የሚፈርስ
- ሰራዊት የሚበትን
- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚያፈርስ እና መሰረታዊ ችግር ያለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲታረም እና ታች ወርዶ እንዳይተገበር ወስኗል።
" የተሰጠው መግለጫ ከሰራዊት ተልእኮ ያፈነገጠ ፣ ተቋማዊ አሰራር የጣሰ " ነው "ሲል የገለፀው ካቢኔው ፥ " ' አመራር ነኝ ' በሚል በዚህ ሁኔታ ተሰብስቦ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል ስልጣን የለውም " ብሏል።
" ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል በተሰጠው መግለጫ መንግስታዊ ማስተካከያ እንዲደረግ አስመልክቶ የቀረበው አቋም የአንዱ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት ሲባል የፕሪቶሪያ ውል የሚያፈርስ ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው " አደገኛ ነው ' ሲል ገልጾ በአስቸኳይ የሚታረምበት አቅጣጫ ማስቀመጡን አሳውቋል።
ካቢኔው ባወጣው የውሳኔ መግለጫ ለኢትዮጵያ መንግስት ባስተላለፈው መልእክት " ' የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን ' በሚል በተሰጠው መግለጫ የሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃሳብ እና ውሳኔ አይደለም በመሆኑም ወድቅ አድርጎታል ፤ ሰራዊቱ እና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አሁንም ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተገዢ በመሆን ጅምር ሰላሙ እንዲጎለብት የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ተከብሮ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል " ብሏል።
" የትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፍላጎት ሰላም ነው " ሲል ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ መልእክት ያስተላለፈው ካቢኔው ፤ " የፕሪቶሪያ የሰላም ውል በአፈፃፀም ብዙ ችግሮች ቢኖሩትም በስምምነቱ አፈፃፀም የሚነሱ ችግሮች በሰላማዊ እና ፓለቲካዊ ትግል እንዲመለሱ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ የተሟላ ድጋፍ እንዲያደርግ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

#Tigray ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል። በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች…
" መንግስታችን እንዳይፈርስ እስከ ሞት ድረስ እንታገላለን ፤የጦርነት ነጋዴዎች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " - አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ
ዛሬ በመቐለ " እምቢ ለጦርነት እምቢ ለመፈንቅለ መንግስት !! " በሚል መሪ ቃል የሰሞኑን የወታደራዊ አመራሮች መግለጫ የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዶ ነበር።
በሰልፉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተው ነበር።
በጊዚያዊ ኣስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ በሰልፉ ላይ ተገኝተው " የሰላም ዋስ የሆነው ሰራዊት የቡድኖች መጫወቻ አይሆንም ፥ የጦርነት ነጋዴዎች ይብቃችሁ " ብለዋል።
" የሻዕብያ ተላላኪዎች አቁሙ !" ሲሉ በምሬት የተናገሩት ከንቲባው " መንግስት ለማፍረስ የተሄደው ርቀት አይሳካም ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ ህዝቡም እንዲከበሩ ያግዝ " ብለዋል።
" የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉነት እንዲተገበር ፣ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዲከበር እና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ቁርጠኛ መሆን አለበት " ያሉት ከንቲባው " የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላም ብቻ መሆኑን በማመን ወጣቱ ትግሉ አጠናክሮ ይቀጥል " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
ዛሬ ከመቐለ በተጨማሪ በሌሎችም ከተሞች ጊዚያዊ አስተዳደሩን ለመደገፍ እና " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው መገለጫ እና ውሳኔና በመቃወም ወጣቶች በበዙባቸው ሰልፎች ተካሂደው ነበር።
በዚህም ፦
- መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- የትግራይ ህዝብ ጥቅም በሰላም ብቻ ነው የሚረጋገጠው !
- ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንደግፋለን !
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ይከበሩ !
- የፕሪቶሪያ ስምምነት ይከበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች ተደምጠዋል።
ትላንትና ዛሬ መቐለ ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የትግራይ ኃይል መኮንኖችን የሚደግፉና የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ የሚገኝ ሲሆን ሰልፎቹ የፖሊስን ክልከላ በጣሰ መንገድ ነው እየተካሄዱ ያሉት።
በህወሓት የፖለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና መከፋፈል ወደ ፀጥታ ኃይል አመራሮች መዛመቱ ህዝቡን ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏል።
ትግራይ ከአስከፊው እና አውዳሚው ጦርነት ገና በቅጡ ሳታገግምና ችግሮች ሳይፈቱ ወደ ሌላ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባ የሚችል ሁኔታ እየታየ መሆኑ በርካቶችን አሳስቧል።