TIKVAH-ETHIOPIA
በተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ዙሪያ የአሶሳ ፖሊስ ምን አለ ? የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው " ሰላም ሰፈር " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ረቡዕ ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ እንደሆነ አመልክቷል።…
#Update
የተማሪ ደራርቱ ገዳይ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል።
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ ላይ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ አስታውቋል።
ረቡዕ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አቶ ዩሀንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰብ የሴት ጓደኛው የሆነችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የግድያ ወንጀል በመፈፀሙ ተከሳሽ በፈፀመው ሰው በመግደል ወንጀል ተከሷል።
መርማሪ ፖሊስና ዐቃቢ ህግ በጋራ ተጠርጣሪው ላይ ክስ መስርተው ምርመራ በማጣራት የወንጀል ድርጊቱን የሚያስረዱ የሰው ማስረጃና የህክምና ማስረጃ በማስደገፍ ለሚመለከተው ፍ/ቤት ልከዋል።
የክስ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በቀን 15/9/2016 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት #በ18_ዓመት_ጽኑ_እስራት እንዲቀጣ ውስኗል።
መረጃው የአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።
#AssosaUniversity
@tikvahethiopia