TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ግብር

🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች

🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር እየጠየቃቸው መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።

" በ2015 ዓ/ም ነበር ጥናቱ የተጠናው ፤ ከዛ 'ተግባራዊ አይሁን፣ ትክክል አይደለም' ተብሎ የተቀመጠ ጥናት ነው አሁን መመሪያ ተደርጎ በትዕዛዝ የወረደው " ሲሉ ነው የተናገሩት።

አስመጪዎቹ ስለዝርዝር ቅሬታቸው ምን አሉ ?

" አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን አላስፈላጊ ግብር እየጠየቀን ነው። ይሄን የሚያደገው 'ሲስተም አዘጋጅቻለሁ' በሚል ነው።

አዲሱ ሲስተም የስሪት፣ የተመረተበትና የመጣበት አገር ይጠይቃል፣ በጥናት መልክ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን ብሎ በአዲስ አበባ በሁሉም ቅርንጫፎች ኤክስኤል ሰርቶ አውርዶ ሥሩ ብሏል።

'ከጉምሩክ ዴክላራሲዮን ላይ ሒሳቡ ሲሰላ ከ45 በመቶ በላይ የሆነ ትርፍ እያተረፋችሁ ነው’ በሚል ነው አዲስ አሰራር ያመጣው።

ይህ መመሪያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተለዬ፣ ፌደራልና ክልል ላይ የሌለ፣ በአዲስ አበባ ብቻ፣ የመኪና አስመጪዎችን ብቻ በተመለከተ የተዘጋጀ መመሪያ ነው።

በዚህ መመሪያ መሠረት የተጠየቅነው ግብር አላስፈላጊ፣ ከህግ አግባብ ውጪ የሆነ ነው። ምክንያቱም ግብር በህግ ነው እንጂ በጥናት አይደለም የሚከፈለው። 

ግብር ሲከፈል ህግ ተረቆ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ነው። ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የግብር መመሪያ የሚያወጣው  ደግሞ ገቢዎች ሚኒስቴር ነው።

ይሄን አዲስ መመሪያ ግን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በራሱ በደብዳቤ መልኩ ነው ወደታች ያወረደው ከአሰራር ውጪ በሆነ መልኩ


እስከዛሬ ጉምሩክ ባስቀመጠው መሠረት ከፍተኛው ጣራ 9% ተደርጎ እኛም 4ም፣ 5ም% አተረፍን ብለን አቅርበን ነበር የምንፈፍለው።

አሁን ግን ቢሮው ሌላ የራሱን ሰንጠረዥ አዘጋጅቶ ለ11ዱም ክፍለ ከተሞች ይህንን መመሪያ አወረደ በትዕዛዝ መልክ። መመሪያው የወረደው ‘ከ45 በመቶ በላይ እያተረፋችሁ ነው የዚህን ግብር ክፈሉ’ በሚል ነው።

ከዚህ ቀደሙ ግብር ጋር ሲነጻጸር 5% አትርፌአለሁ ብለሸ አሳውቆ ግብር ሲከፍል የነበረን ሰው ‘45% ታተርፋለህ’ ማለት በጣም ብዙ እጥፍ ነው። የህግ አግባብ የለውም አሰራሩ። 

በፌደራል ደረጃ ንግድ ፈቃድ አስመጪዎች ያላቸው መኪና መሸጫ አላቸው። የእነርሱ በኖርማሉ ነው፣ እነርሱን አይመለከትም መመሪያው። ክልል ያሉትንም በተመሳሳይ አይመለከትም። 

አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው ክፍለ ሀገርም ሆነው የክፍለ ሀገር ፈቃድ አውጥተው (ለምሳሌ የክልል፣ የፌደራል ፈቃድ ያላቸው) ከኛ ጋር ተመሳሳይ መኪና የሚሸጡ አሉ።

እነርሱን ግን ይሄ አዲሱ የግብር መመሪያ አይመለከትም። አንድ ከተማ ውስጥ ተመሳሳይ አይነት መኪና እየሸጡ እያሉ
ይሄ ትልቅ ልዩነት ነው የሚያመጣው።

የፌደራል ገቢዎች የማያውቀውን ተመን እንዴት አንድ የከተማ አስተዳደር በራሱ ያወጣል? ይሄ አሰራር የህግ ግራውንድ የለውም። ቅሬታችን ይሰማልንና ትግበራው ይስተካከልልን”
ብለዋል።

አዲስ አበባ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጭዎች ከዚህ ቀደም ያልነበረ አሰራር ወርዶ ከመጠን ያለፈ ግብር ተጠየቅን ለሚለው ቅሬታቸው ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል ለአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጥያቄ አቅርበናል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ምን ምላሽ ሰጡ?

" በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡ ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው።

የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።

ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለውም። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። ዋናው ዓላማ ግን ከፍተኛ የሆነ የታክስ ስወራ ስላለ ያን ለማስቀረት ነው።

ከተማው ማንኛውም መኪና የሚገዛ ሰው ስንት ብር ነው የገዛው? በትክክል በገዛውና በከፈለው ገንዘብ ልክ ደረሰኝ ተሰጥቶታል ወይ? በስት አካውንት ነው ገንዘብ እንዲያስገባ የሚጠየቀው? የሚለው የአደባባይ ምስጢር ነው። 

ስለዚህ የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።

እዚህ ላይ ልዩነት አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው መጥቶ ልንወያይ እንችላለን በራችን ክፍት ነው "
ብለዋል።

(ኃላፊው፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ላቀረብንላቸው ጥያቄዎች የሰጡን ሙሉ ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ግብር 🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች 🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ…
#ግብር #ተሽከርካሪዎች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከተሽከርካሪ አስመጪዎች ለቀረበበት ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ሙሉ ምላሽ ምንድን ነው?

" አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ያሉ ዋና ዋና የሚባሉ የታክስ ስወራ አለባቸው የሚባሉ ዘርፎች ተለይተው ጥናት ተደርጓል፡፡

አንዱ ከቋሚ ንብረት፣ ከቤት፣ ከሪልስቴት ጋር ሽያጭ ጋር፣ ሌላው ደግሞ ከመኪና ጋር የተገናኘ ጥናት ነው፡፡ 

እነዚህ ጥናቶች 2015 ዓ/ም ተጠንተው ተጠናቀው 2016 ዓ/ም ሚያዝያ ጀምረው ተግባራዊ እንዲደረጉ በከተማ አስተዳደሩ ተወስኖ ሰርኩላር ተላልፏል፡፡ 

የቤትና መኪና ሻጮችን በተመለከተ ማለት ነው፡፡ የቤት ወዲያውኑ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ከመኪናም ሽያጭ ጋር በተገናኘ የመኪና ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ ሁለት ቢሮዎች ናቸው በዋናነት ግብር የሚሰበስቡት፡፡ 

አንዱ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በትራንስፖርት ቢሮ ውስጥ ያለው የከተማው የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ነው፡፡ 

በጥናት እንዲጠና የተደረገው  ከተማው የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች የሚሸጡበት ዋጋና ተሸጠዋል ተብሎ ለገቢወዎች ቢሮ በሚቀርበው የገንዘብ መጠን መካከል በጣም ሰፊ የዋጋ ልዩነት በመኖሩ ነው።

ጥናቱን ከፌደራልም ከአዲስ አበባም የተለያዩ ባለሙያዎች ናቸው ያጠኑት፡፡ በገበያው ዋጋና ለገቢዎች ቢሮ በሚቀርበው ሪፖርት መካከል በጣም ሰፊ ሆነ የዋጋ ልዩነት እንዳለው ጥናቱ አሳይቷል።

10 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መኪና በ3 ሚሊዮን ብር፣ በ6 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መኪና በ1 ሚሊየን ብር እየሆነ ያለው፡፡ በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡  

ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው። ጥናቱ በወቅቱ የነበረውንም የዋጋ ግሽበት ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተያያዘውንም ጉዳይ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። 

ስለዚህ ተግባራዊ መደረግ የነበረበት አምና ነው፡፡ 2016 ዓ/ም በዚሁ ነው መሰራት የነበረበት፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት 2016 ዓ/ም ሳይተገበር ቆይቷል፡፡ 

ከተማ አስተዳደሩ ‘2016 አለመተግበሩ ትክክል አይደለም፡፡ በ2016 ዓ/ም የግብር ዘመን ላይ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ አሁን ግን የ2017 ዓ/ም ግብር በሚከፈልበት ጊዜ ህጉ መከበር አለበት’ የሚል አሰራር ስለተቀመጠ ያንን አሰራር ነው የተገበርነው፡፡ 

በተከታታይ አስመጭዎቹ ሰዎችን ወክለው የሂሳብ ባለሙያዎቹ ጭምር መጥተው በተሰራው ፎርሙላ ላይ ቁጭ ብለን አንድ በአንድ ተወያይተናል፡፡ ተግባብተናል ብዙ ልዩነት አልነበረም።

በውይይታችን በተለይ ቴክኒካል የሆነውን ነገር የሒሳብ ባለሙያዎቻቸው ባሉበት ተወያይተን እነሱን የሚያከስር እንዳልሆነ ነገር ግን የግብር ስወራውን ለመከላከል የተዘጋጀ ፎርሙላ እንደሆነ ከውጭ ምንዛሬ ጋር ያለውንም ችግር ግምት ውስጥ እንዳስገባ በመድረኩ ላይ ተግባብተናል፡፡ 

አንድ ሰው መኪና ሲገዛ ደረሰኙን ይዞ ታርጋ ለመውሰድ ወይም ለማዞር በሚሄድበት ጊዜ አምና ጭምር መኪና ሻጮቹ የሰጡትን ደረሰኝ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን ‘አልቀበልም’ እያለ በፎርሙላው መሰረት እየሰራ ትክክለኛውን እያሰላ ከመኪና ገዥዎቹ አስፈላጊውን ክፍያ ሲቀበል ነው የነበረው፡፡ 

ሻጮቹ የሸጡት የገንዘብ መጠን ገዢው ታርጋ ለመሸጥ በሚሄድበት ጊዜ ተቀባይነት እንዳላገኘ እዛ በትክክለኛው ዋጋ የስም ዝውውር እንደፈጸመ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ አምናም እነሱ ላይ አለመተግበሩ ካልሆነ በስተቀር አዲስ የመጣ ነገር አይደለም፡፡  

ምንም አስመጪዎቹን የሚጎዳ፣ የሚያከስር ነገር የለውም፡፡ በጣም መሠረታዊ ሚባሉ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ ያስገባ አሰራር ነው፡፡

እንደ ጉዳት እየወሰዱት ያለው አምና ስንከፍል በነበረው አይነት ብቻ እንክፈል ለምን ተጨማሪ ክፍያ እንከፍላለን? ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ጥያቄ ነው፡፡ 
ይሄ ደግሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ የታክስ ስወራን መከላከል ያስፈልጋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በከተማው የሚሰራውን ይህን ሁሉ ልማትና ህዝብ ጥያቄ የሚመልሰው ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ ነው፡፡ 

እዚህ ገቢ ውስጥ የግብር ስወራውን የመከላከል የገቢዎች ቢሮ ኃላፊነት አለበት፡፡ የዋጋ ጥናትን በተመለከተ በግልጽ በታክስ አስዳደር አዋጁ ላይ ስልጣን ለገቢዎች ቢሮ ተሰጥቷል፡፡ ግልጽ ነው፡፡

አዋጁም ይሄ በዋናው የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ የሚባል አለ በሱ አዋጅ ላይ በግልጽ የተቀመጠ፣ አንቀጽ 3 ላይ ለገቢዎች ቢሮ ተሰጠ ስልጣን አለ "
ብሏል።

አንዱ የአስመጪዎቹ ቅሬታ መመሪያውን ማውረድ ያለበት የገቢዎች ሚኒስቴር ነው እንጂ ቢሮው አይደለም የሚል ነውና የቢሮው ምላሽ ምንድን ነው ? ሲንል ለቢሮ ኃላፊው ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

ምን ምንላሽ ተሰጠ ?

" አይ አይልም። የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የተሰጠ ስልጣን በታክስ አስተዳደር ተቀምጧል። የፌደራል ግብር ከፋይ የሚባሉ አሉ። አዲስ አበባ ላይ ደግሞ የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ አለ። 

በአዲስ አበባም ሆነ በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ላይ PLC የሆኑ ግብር ከፋዮች ለፌዴራል መንግስት ነው ግብር የሚከፍሉት። እነሱን የተመለከተ አሰራር ሊያወርድ ይችላል ፌደራል መንግስት። 

የአዲስ አበባ ከተማ ግብር ከፋዮችን በተመለከተ አሰራር መዘርጋት፣ ዋጋ ማጥናት፣ በዋጋ ጥናቱ መሰረት ግብር እንዲሰበስቡ የማድረግ ስልጣን ደግሞ ለከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ መሆኑ በአዋጁ በግልጽ ተቀምጧል። "

" ግብር የሚከፈለው ህግ ወጥቶ በህግ ደረጃ ነው እንጂ ጥናት ተጠንቶ አይደለም፣ ይሄ ጥናት ደግሞ 2015 ዓ/ም ላይ ‘ተጠንቶ አይሆንም ትክክል አይደለም’ በሚል ነበር ቆይቶ የነበረው፣ አሁን ለአዲስ አበባ መኪና አስመጪዎች ብቻ በሚል ጥናትን መሰረት ተድርጎ የወጣ፣ ህግን መሰረት ያላደረገ ነው " የሚል ቅሬታም ቀርቧል። የቢሮው ምላሽ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ትጥቷል።

ቢሮው በምላሹ ምን አለ ?

" በታክስ አስተዳደር አዋጁ ላይ በግልጽ የተቀመጠው በማንኛውም ምርት፣ አገልግሎት፣ ሽያጭ በሚከናወንበት በማንኛውም እቃ ላይ የገቢዎች ቢሮ ዋጋ ማጥናት፣ ዋጋን Set የማድረግ፣ በዚህ ዋጋን በመቀነስ የሚመጣን የግብር ስወራ ለመከላከል ዋጋ መተመን እና በዚያ መሰረት ግብር ማስከፈል እንደሚችል ተቀምጧል።  

ስለዚህ መመሪያም፣ ሌላ አዋጅም አያስፈልገውም አሰራር ብቻ ነው መዘርጋት የሚያስፈልገው። ይጠናል ያ የተጠናው ጥናት ወደ አሰራር ይቀየርና ተግባራዊ ይደረግ ተብሎ ለየቅርንጫፍ ይወርድና ነው ተግባራዊ የሚደረገው።  

ይሄ ነው አሰራሩ። ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለው። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። "

(ገቢዎች ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሐኪሞቹ ' መግቧቸው፤ የምግብ እጥረት ነው ' ይላሉ። እኛ ደግሞ ከየት እናመጣዋለን ? ጊዜው ከፋብን " - እናት በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ድርቅ እና የምግብ እጥረት ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ጨምሮ 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን ወረዳው አስታውቋል። በክልሉ ባለው ግጭት እና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅ እና የምግብ እጥረት መጋለጡን የቡግና…
🚨 “ የሚላስ የሚቀመስ የለም ” - የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

🔴 “ ችግር እንዳለ ይታወቃል ” - የአማራ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተጎዱ፣ በተለይ ጨቅላ ህፃናት የከፋ ስቃይ ላይ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ ጉዳዩ በጣም አሳዛኝ ነው። በእኛ ቦታው ያልሆነ ሰው አይገባውም ” ሲሉም የሁነቱን አስከፊነት አስረድተዋል።

ስሜ ከመነገር ይቆይ ያሉ የመረጃ ምንጭ በበኩላቸው፣ “ በቡግና ወረዳ ጉልሃ ቀበሌ አንድ ህፃን በምግብ እጥረት ሞቷል ” ብለዋል።

የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል አለሙ በበኩላቸው፣ በክልሉ ባለው ግጭትና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅና ለምግብ እጥረት በመጋለጡ ህፃናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን ሰሞኑንን ለቢቢሲ አማርኛ መናገራቸው አይዘነጋም።

በወረዳው በተከሰተ የምግብ እጥረት በተለይ ጨቅላ ህፃናት ስለተጎዱ ነዋሪዎቹ የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውን በመግለጽ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት፣ “ እኛ ጋር ስራ የለም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።

ጽሕፈት ቤቱ፣ “ እውቅናው የለኝም ” ያለ ሲሆን፣ ጉዳዩን እንደሚያውቁት ነዋሪዎች መናገራቸውን ብንገልጽለትም፣ “ እስካሁም ምንም አይነት በሪፓርትም የመጣ ነገር የለም ” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቡግና ወረዳ በተጨማሪም ለአማራ ክልል ስጋት አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ችግሩ መኖሩን አምኗል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌ በሰጡን ቃል፣ “ ጉዳዩ በኛ ቁጥጥር ውስጥ ነው። ከእኛ አቅም ውጪ የሆነ ነገር የለም ” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፣ “ ችግር እንዳለ ይታወቃል። ድጋፍ እየቀረበ ነው። ምንም የተለዬ ነገር የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ የአምናውን ድርቅ ችግር ተቋቁመናል አሁን እንዲያውም ጥሩ ነው ምርት አምርተዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ድጋፍ እየተደረገላቸው ከሆነ ምን ያክል ድጋፍ ተደርጓል ? ሰሞኑን ያደረጋችሁት ድጋፍ ነበር ? በተለይ ሰሞኑን ህፃናቱን የሚመግቡት እንደተቸገሩ ነዋሪዎቹ እየገለጹ ነው፣ ስንል ለወ/ሮ ፍቅሬ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

እሳቸውም በምላሻቸው፣ “ በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው በተለመደው አግባብ (ድጋፉ የሚሰጥበት ቀመር አለው) ድጋፍ እየደረሳቸው ነው ” ከማለት ውጪ የችግሩን አስከፊነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ነዋሪዎቹ የላኳቸው ፎቶዎች ህፃናቱ በምግብ እጥረት እንደተጎዱ የሚመሰክሩ እንደሆኑ ገልጸን፣ ድጋፍ ካለ ጉዳዩ እንዴት በዚህ ልክ ጉዳት እንዳደረሰ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኃላፊዋን ጠይቋል።

በዚህም፣ “ ይለካል እኮ ማልኑውትሬሽን፣ ሞዴሬት የሆኑት እየተለካ ምግብ ሁሉ ይሰጣቸዋል ለእናቶች፣ ለህፃናት ” የሚል ምላሽ ሰጠተዋል።

“ ለዩኒሴፍም ይቀርባል። ለአዋቂዎች ደግሞ እህል ይቀርባል። የገንዘብ ደጋፍም ይሰጣልና ክትልትል እየተደረገ ነው ” ያሉት ወ/ሮ ፍቅሬ፣ “ በመሀል ደግሞ በህመምም በምንም ጉዳት ሊያጋጥም ይችላል ” ነው ያሉት።

የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽንና ኮሚሽኑ ይህን ይበሉ እንጂ የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ግን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጠው ቃል፣ “ ማህበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን ባግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው አድርጓል ” ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል " አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመሆኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም " ብለዋል።

የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም አሁን ላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መሆኑን አስታውቀዋል።

የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበርኩ ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው " በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው እየገቡ ነው " ብለዋል።

የኤሪካ ኤምባሲ ደግሞ ፤ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ እንደሆነ አመልክቷል።

ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል።

ኤምባሲው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአሁኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውን አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትኩረት መነፈጋችን እጅጉን አሳዝኖናል " - የሽርካ ወረዳ ነዋሪዎች በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳ ቤተ ክህነቱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ግድያና እገታ እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎቹን ዋቢ በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከታገቱት ውስጥ የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች 8 ሰዎች ገንዘብ…
#Update

“ 11 ሰዎች አሁንም ያሉበት አልታወቀም። አንድ ሰው መገደሉ ተረጋግጧል ” -የሽርካ ወረዳ ቤተ ክኀነት

በአርሲ ዞን፤ ሽርካ ወረዳ በታጣቂዎች ታገቱ የተባሉ በርካታ ነዋሪዎች ያሉበት እንደማይታወቅ የወረዳው ቤተ ክኀነትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የአካቢው ነዋሪዎች፣ “ ታጣቂዎቹ እገታውን የፈጸሙት ታኃሳስ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ/ም ነው። ከ20 በላይ ሰዎች ናቸው በታጣቂዎች የተወሰዱት ” ብለዋል።

የታገቱት የወረዳው ቤተ ክኀነት ስራ አስኪያጅ ጭምር መሆኑን ተናግረው፣ ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ገንዘብ ከፍለው እንደተለለቁም ሰሞኑን ገልጸውልን ነበር።

ቁጥራቸው በትክክል ባይታወቅም ከታጋቾቹ ውስጥ የተገደሉ ሳይኖሩ እንዳልቀረ፣ ቀሪዎቹ ታጋቾች ከእገታ እንዳልተመለሱ፣ ጭራሹንም ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

“ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በየጊዜው የሸኔ ታጣቂዎች በሚፈጽሙት እገታ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ እድለኛ የሆኑት በ100 ሺዎች ገንዘብ እየከፈሉ የተለቀቁ አሉ ” ሲሉ አስታውሰዋል።

“ እስከመቼ ድረስ ነው ህዝቡ በተወለደበት አገር በእንዲህ አይነት ሰቀቀን የሚኖረው ? የፍርድ ቀን እስኪመጣ ጮኸታችንን አሰሙልን ” ሲሉ ተማጽነዋል።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የወረዳው ቤተ ክኀነት ሥራ አስኪያጅ ከቀናት በፊት በሰጡን ቃል፣ “ አሁን እቤቴ ገባሁ። ከእኔ ጋር ተይዘው የነበሩ ስምንት ሰዎች ጋር በአጠቃላይ ዘጠኝ ሰዎች ተለቀዋል ” ብለዋል።

የወረዳው ቤተ ክኀነት በዛሬው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ደግሞ፣ “ 11 ሰዎች ያሉበት አይታወቅም። አንድ ሰው መሞቱ ተረጋግጧል ” ብሎ የሁነቱን አሳሳቢት አስረድቷል።

የተለቀቁት ሰዎች ምን ያህል ገንዘብ በመክፈል እንደተለቀቁ ላቀረብነው ጥያቄ ሥራ አስኪያጁ በሰጡት ማብራሪያ፣ የገንዘቡ ጉዳይ ለመናገር እንኳ የሚመር መሆኑን ገልጸው፣ ብቻ የተለቀቁት ገንዘብ ከፍለው መሆኑ እንዲታወቅ ገልጸዋል።

“ የተወሰድንበት አቅጣጫው ስለሚለያይ፣ እኔም ሰሞኑን ችግር ላይ ስለከረምኩ መረጃውን ገና በደንብ ሰብስቤ ተጨማሪ ማብሪራያ እሰጣለሁ ” ሲሉ ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

“ ባለስልጣናቱ  ህገ ወጥ ስራ ሲሰራ ለማስቆም ምንም አይነት ፍላጎት የላቸውም ” - ነዋሪዎች

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ልዩ ስሙ ‘ሰፈረ ገነት’ በተባለ ቦታ የሚገኙ ነዋሪዎች ካሳና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው የመስሪያ ቦታቸው ለባለሃብት ተላልፎ በመሰጠቱ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አሰሙ።

ቦታቸው ጋራዥ፣ ላቢያጆ የመሳሰሉት ስራዎች የሚሰሩበትና በቤተሰብ ደረጃ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች የሚተዳደሩበት 12 ሺሕ ካሬ መሆኑን ገልጸው፣ ቦታው ከህግ ባፈነገጠ አሰራር ለአንድ ባለሃብት ስለተሰጠባቸው መብታቸው ተከብሮ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ መጀመሪያ ወረዳው ጠራንና ‘ቦታችሁ ለባለሃብት ተሰጥቷል። የተወሰነው በካቤኔ ነው’ አለን። ከዛ ክፍለ ከተማ ሄደን የካቢኔው ውሳኔ ነው ወይ? አሳዩን አልናቸው። 
‘ይህንን የመጠየቅ መብት የላችሁም። ጥቅማችሁን ነው ፕሮሰስ ማድረግ ያለባችሁ እንጂ ይሄ የኛ ጉዳይ ነው’ አለን። እሺ ብለን የሚያስፈልጉ ዶክሜንቶችን አቅርበን ፕሮሰስ ማድረግ ጀመሩ ክፍለ ከተማውና ወረዳው።

በመካከል የወረዳው ሥራ አስፈጻሚና የመሬት ልማት ማኔጅመንትን ሰብስበውን ‘የምትለቁ ከሆነ በፍጥነት ልቀቁ አለበለዚያ ልክ እንደ ህገ ወጥ ግንባታ በጫጭቄ እጥለዋለሁ’ አለ።

በዚህም ምትክ ቦታ ሳይሰጥ፣ የካሳ ክፍያ ሳይኖረው በሚል ሰው ተደናገጠ። ክፍለ ከተማ ሄደን ስናናግር ‘ማን ሰብስብ አለው?’ የሚል ጥያቄ አዘል ምላሽ ነው የሰጠን።

ከንቲባ ጽህፈት ቤትም ሄደን ቅሬታ አቀረብን ዓባይነህ ለሚባል ሰው፣ የካቢኔው ውሳኔ መሆኑን ማረጋገጥ እንፈልጋለን ስንለው ጌታቸው ለሚባል መራን። ጌታቸውን ስናናግራቸው ‘አረጋግጨ ይነገራችኋል እሱ የኛ ጉዳይ ነው’ አሉን።

በዚሁ ሁኔታ ቀጥለን በኋላ ስንጠይቅ ‘የካቢኔ ውሳኔ የተሰጠው ባለሃብቱ ወረዳ 10 ነው እንጂ ወረዳ አምስት ላይ አይደለም’ ተባልን።

በኋላም የወረዳ ዘጠኝ እንደሆነ ቀሪ ወረቀት ላይ አገኘን። ሄደን ቀጥታ ዓባይነህን ስናናግራቸው ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደውለው ሲያናግሩ ‘በካቢኔ ውሳኔ ነው  ፕሮሰስ የተደረገው ገንዘብ እየገባላቸው ነው’ አላቸው።

ከዛ ወረቀቱን ለዓባይነህ ስናቀርብ ለክፍለ ከተማው ‘አይ የካቢኔ ውሳኔ አይደለም፣ ከኛ መዝገብ ቤት ያለውንና ይሄንን አያይዤ እልክልሃለሁ ቼክ አድርገው’ አሉት። ከዚያ በኋላ ግን ማንም ምላሽ የሚሰጠን የለም። ባለሃብቱ የኛን ቦታ ሙሉ ለሙሉ አጥሮታል።

የኛ ቅሬታ ውሳኔው የካቢኔ ውሳኔ አይደለም ባለን ማስረጃ። ሲቀጥል የካቢኔው ውሳኔ ቢሆን እንኳ መጀመሪያ ካሳና ምትክ ቦታ ሊሰጠን ይገባል።

ባለስልጣናቱ ‘ይሄኮ ያስጠይቀናል። የእናንተ ጉዳይ እንዲፋጠን 22 ነው ግፊት ማድረግ ያለባችሁ’ የሚል አስተያዬት ነው የሚሰጧቸው እንጂ ህገ ወጥ ስራ ሲሰራ ለማስቆም ፍላጎት የላቸውም። ፍ/ቤት ሂደን እግድ ስናወጣ መደናገጥ ጀመሩ”
  ብለዋል።

NB. " 22 " ተብሎ የተገለጸው እዛ ያለውዥ የመሬት አስተዳደር ጉዳዩን እንደያዘ ለመግለጽ ሲሆን እነርሱ ባለወቁት መልኩ እዛ እንዲታይ መደረጉ አሻጥር እንደሆነ ገልጸዋል።

ለቅሬታው ምላሽ ለማግኘት ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሙከራ ያደረግን ሲሆን፣ ለጊዜው የስልክም ሆነ የፅሑፍ ምላሽ አልሰጡም።

ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ጉዳዩ እንደሚመለከታቸው በቅሬታ አቅራቢዎቹ የተነገረላቸው አቶ ግታቸው የተባሉ አካል፣ በስልክ ማብራሪያ እንደማይሰጡ ለቲክቫህ ገልጸዋል። በአካል ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ ይቀርባል።

(ነዋሪዎች ህዝቡ ይወቅልን ብለው አጠቃላይ ቦታውን የተመለከተ ዶክመንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መሰረት ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ

🚨“ የሐምሌ 2016 ዓ/ም ደመወዝና፣ የ23 ወራት የዱቲ ክፍያ ስላልተከፈለን የዱቲ ሥራ ለማቆም ተገደናል” - የሀላለ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች

🔴 “ የ23 ወራት ባይሆንም የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈላቸውም ” - ሆስፒታሉ

🔵 “ የአንድ ወይም ሁለት ወራት እንጂ የዚህን ያክል የተወዘፈ ክፍያ የለም ” - የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ

በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሀላለ ሆስፒታል የሚገኙ 78 ጤና ባለሞያዎችና ሌሎች ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዝና የ3 ዓመት የዱቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው የትርፍ ሰዓቱን ሥራ ለማቆም መገደዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ጤና ባለሞያዎቹ በሰጡን ቃል ምን አሉ?

“መንግስት ከሚመድበው በጀት ክፈሉ ብለን በደብዳቤ ብንጠይቅም ‘እንከፍላለን አሁን ግን የካሽ እጥረት አለብን’ አሉን። ከዚህ ባለፈ ማስፈራሪያ፣ እስራት፣ ድብደባ ይደርስብናል።

የመጀመሪያ የስምነት ወራት የዱቲ ክፍያ በተመለከተ ተካስሰን ፍርድ ቤት እንዲከፈለን ውሳኔ ቢሰጠንም በፖለቲካ ሰዎች ጣልቃ ገብነት ውሳኔ ባለመከበሩ አልተከፈለንም።
 
ከዚያ ወዲህ የሰራነውን የ15 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያንም ቢሆን ባለመክፈላቸው፣ ለመክፈልም ፍላጎት የሌላቸው በመሆኑ ከሆስፒታሉ ሠራተኞች ኃላፊ ውጪ በአጠቃላይ ተፈራሪመን የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማቆም ተገደናል።

በደላችንን፣ ድምፃችንን ለህዝብ እና ለመንግስት አሰሙልን። ጤና ሚንስቴር በህይወት ካለ መብታችንን ያስከብርልን” ሲሉ አሳስበዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የአንድ ወር ደመወዝና የ23 ወራት ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ያልተፈጸመበት ምክንያት ምንድን ነው? ሲል ለሆስፒታሉ ጥያቄ አቅርቧል።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ በረከት ሌራ ምን ምላሽ ሰጡ?

“የኛ ተቋም የሚያስተዳድረው ገንዘብ የለም ስራዎች ከተሰሩ በኋላ ለወረዳ ፋይናንስ ሪፓርት ቀርቦ ያንን መሠረት በማድረግ ነው ክፍያ የሚፈጸመው። 

የ2016 ዓ/ም የሐምሌ ደመወዝ 13% ብቻ ነው የሚቀረው 87% ተከፍሏል። የ23 ወራት ባይሆንም የ20 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ሰፊ ነው ችግሩ። የካሽ እጥረት በሚል ብዙ ነገር እየተባለ ነበር።

የዱቲ ክፍያ በተመለከተ ፍርድ ቤት ክፍያ እንዲፈጸም የሚል ውሳኔ ሰጥቷል። የወረዳው መንግስት ከክስ ሂደቱ በኋላ መክፈል ከጀመረ በኋላ ነው የቆመው።

‘በንግግር ችግሮችን እየፈታን እንመጣለን’ በሚል ቃል ከተገባልን በኋላ ነው በመካከል ክፍያው የቆመው።  የሚያዚያ ወር በከፊል መከፈል ከተጀመረ በኋላ ነው ቆመ”
ብለዋል።

የዱቲ ሥራ በመቆሙ በማታ የሚመጡ ወላድ እናቶችን ብቻቸውን እያከሙ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፣ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ባለሙያዎቹ የ23 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ቅሬታ አቅርበዋል፣ ሆስፒታሉም የ20 ወራት የዱቲ፣ የሐምሌ ደመወዝ 13 በመቶ ክፍያ አለመፈጸሙን ገልጿል፣ ይህ ለምን ሆነ? ጉዳዩን ተመልክታችሁት ነበር? ስንል ለወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ጥያቄ አቅርበናል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ምን አለ?

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ፣ “የ23 ወራት እንዳልተከፈለ መረጃው የለኝም። ተከፍሎ ነው እየተሰራ ያለው። ትክክል ነው ለማለት እቸገራለሁ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥተዋል።

የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ሆስፒታሉም እንዳረጋገጠ ስንገልጽላቸውም፣ “20 ወራት አይደርስም እኔ እንደማውቀው። ማጣራት ይጠይቃል” ነው ያሉት።

“የአንድ ወይም ሁለት ወራት እንጂ የዚህን ያክል የተወዘፈ ክፍያ የለም” ያሉት ኃላፊው፣ ጉዳዩን አጣርተው ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ሆስፒታሉ ያልተከፈላችሁ የ20 ወራት የዱቲ ክፍያ መሆኑን ገልጿል፣ እናንተ ደግሞ ያልተከፈላችሁ የ23 ወራት እንደሆነ ገልጻችኋል ፣ የትኛው ነው ትክክል ? ስንል የጠየቅናቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ከ23 ወራት የዱቲ የ3 ወሯን ለተወሰኑ ሰዎች ነበር የከፈሉት። በትምህርት፣ በዝውዝውር፣ ሥራ በመልቀቅ ሄዱት ሳይከፊሉ ነው ‘ከፍለናል’ የሚሉት ነገር ግን እነዚህ ባለሙያዎች ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ህብረተሰቡን እንዳገለገሉ መረሳት አልነበረበትም ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የሹፌሮችድምጽ

" ከታህሳስ 2 እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ብቻ 6 ሹፌሮች ከነረዳታቸው በታጣቂዎች ተገድለዋል " - ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር

🚨 " ሹፌርን ማገት የስራ ዘርፍ ሆኖ እየተኖረበት ነው !! "

የከባድ መኪና ሹፌሮች በሃገር አቋራጭ እና ከተማ አቋራጭ ጉዞዎቻቸው ወቅት በታጣቂዎች የሚደርስባቸው እገታ እና ግድያ ተባብሶ መቀጠሉን ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ባለፉት 5 አመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተገደሉ ሹፌሮች ቁጥርም 230 መሻገሩን ስሜ አይጠቀስ ያሉ የማህበሩ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከታህሳስ 2 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ/ም ብቻ ስድስት ሹፌሮች ከነረዳታቸው በታጣቂዎች ተገድለዋል ብለዋል።

አራቱ ሹፌሬች የተገደሉት በመተማ ጎንደር መንገድ ጭልጋ አካባቢ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ከጎንደር ሳንጃ መንገድ ፈረስ መግሪያ አካባቢ ነው።

ፈረስ መግሪያ አካባቢ የተገደሉት ሹፌርና ረዳት ሲሆኑ ከታህሳስ 2 ጀምሮ አግተው ገንዘብ እንዲሰጣቸው ሲደራደሩ ቆይተው ታህሳስ 5/2017 ዓ/ም 120 ሺ ብር ከተቀበሉ በኋላ ገድለው እንደጧላቸው ሃላፊው አስረድተዋል።

የችግሩን ክብደት ሲያስረዱም " አንዳንድ ቦታዎች ላይ መኪና ሲበላሽ የመጀመሪያ ስራ ወርዶ ዝቅ ብሎ ማየት አልሆነም የመጀመሪያ ስራ ወርዶ መሮጥ ነው ምክንያቱም እንደቆምክ አንድ ታጣቂ መጥቶ ሊያግትህ ወይም ሊገድልህ ይችላል ምን ተበላሸ ብለህ የምታየው አንድ ሚሊሻ ይዘህ ተመልሰህ መጥተህ ነው " ብለዋክ።

ማዕከላዊ ጎንደር ታች አርማጭሆ ከሶረቃ እስከ ሳንጃ፣ ፈረስ መግሪያ ፣ ' ኢትዮጵያ ካርታ ' የሚባለው አካባቢ ድረስ ለሹፌሮች አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን ገልጸው ሳንጃ እና አሽሬ ባለው የመንገድ ክፍል ከህዳር 25 እስከ አሁን ድረስ 5 ሹፌሬች እንደታገቱ ተናግረዋል።

ሃላፊው ፤  " ሰው የሹፌሮችን እገታ እና ግድያ አሁን በክልሉ ከሚታየው የጸጥታ ችግር ጋር ያያይዘዋል ነገር ግን እገታ በጠቀስናቸው አካባቢዎች 7 እና 8 ዓመት አልፎታል ሹፌርን ማገት የስራ ዘርፍ ሆኖ እየተኖረበት ነው " ሲሉ አማረዋል።

" በብዛት የሹፌሮች እገታ ያለበት አካባቢ ግጭት ያለበት አካባቢ አይደለም " ያሉት አመራሩ " ታገትን ተገደልን ብለን ስንናገር : ግጭት ወዳለበት አካባቢ እያሽከረከራቹ በመሆኑ ነው ' እየተባለ ይደበሰበሳል እንባላለንም ነገር ግን ይህ ለወንበዴ ሽፋን መስጠት ነው " ብለዋል።

በመተማ እና ጎንደር መሃል ቦና ፣ መቃ እና ግንታ አካባቢ አንድ ሹፌር እስከ 40 እና 50 ሺ ብር እንዲከፍል እንደሚገደድ አንስተው በ05/04/17 ሳይከፍሉ ያለፉ ሹፌር እና ረዳት በዚሁ አካባቢ መገደላቸውን አስታውሰዋል።

ለምንድነው የምትሰበስቡት ? ስንልም " ከምናግታቹ ብለን ነው " የሚል መልስ ይሰጠናል ብለዋል።

እገታ የሚፈጸምባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ኃይል ካምፕ ያለበት ቢሆንም ለሹፌር ጥበቃ የሚያደርግ ሆነ ወንበዴዎችን የሚያጸዳ ሃይል እንደሌለ ተናግረዋል።

በዚህ ምክንያት በሳንጃ ሶረቃ መንገድ 2 ሺህ ብር በመክፈል በአጃቢ ሚሊሻ ለመንቀሳቀስ መገደዳቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአካባቢውን የጸጥታ አመራሮች ምላሽ እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኮሬ 🛑 " ከትላንትና በስቲያም ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ቆስለዋል። የአርሶ አደሩ ስጋት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው " - ኮሬ ዞን 🔵 " እዛ አካባቢ ያለውን ህዝብ በማጽዳት መሬቱን መውሰድ ነው የተፈለገው " - የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ዳኖ ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ሁለት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ጥቃት እንደቆሰሉ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።…
🔈#ኮሬ

“ ሰሞኑን በጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ ንጹሐን ዜጎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - የዞኑ አካል

🔴 “ እስካሁን ድረስ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዳንዱ ግድያ ይገለጻል ፤ የአንዳንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ ” - በሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት የዞኑ ህዝብ ተወካይ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮሬ ዞን የንጹሐን በታጣቂዎች ግድያ ባለመቆሙ ዞኑ እና በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የዞኑ ተወካይና በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ዛሬም ፍትህ ጠይቀዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በኃላፊነት ላይ የሚገኙ አንድ የዞኑ አካል፣ እሁድ ታኀሳስ 13 ቀን 2017 ዓ/ም 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ንጹሐን ዜጎች መገደላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እኝሁ አካል በሰጡት ቃል፣ “ ምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ዞኑ ጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ ገብተው ባደረሱት ጥቃት ሁለት አርሶ አደሮች ተገድለዋል ” ነው ያሉት።

ታጣቂዎቹ ከፈቱት ባሉት ተኩስ ዩኑሱ ኡሱማን ኃይሌ የተባለ ወጣት ወዲያው፣ ወጣት ቡቹቴ ማስረሻ ደግሞ ወደ ኬሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወታቸው ማለፉን ከቤተሰቦቻቸው እንዳረጋገጡ ገልጸዋል። 

በተለይ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ነቅተው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዞኑ በአጽንኦት አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ መንግስት በዞኑ የሚፈጸመውን ጥቃት እንዲያስቆም ከዚህ ቀደም ስለቀረቡት ጥያቄ ምን አዲስ ነገር አለ ? ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ ዞን ህዝብ ተወካይ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)ን ጠይቋል።

በፓርላማ የህዝብ ተወካዩ ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ በፓርላማ ባለፈው እኔ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኬዙን አንስቼ ነበር።  ሽማግሌዎችም በተደጋጋሚ እዛ ርዕሰ መስተዳድር ሄደው ነበር።

እስካሁን ድረስ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዳንዱ ግድያ ይገለጻል፤ የአንዳንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ። የተለዬ ምንም መፍትሄም የለም።

መንግስት ትኩረት ቢሰጥ ኖሮ ያ አካባቢ ይህን ያህል የሚያስቸግር አይደለም፣ ጠባብ ቦታ ነው ገላና ሸለቆና ነጭ ሳር ፓርክ የሚባለው እነዚህ ሽፍቶች የሚንቀሳቀሱበት። 

በቀላሉ ኦፕሬሽን አድርጎ ችግሩን መፍታት ይችላል በሚል በተደጋጋሚ እናቀርባለን፤ ከዛም የመንግስት ሰራዊት ይሄዳል። ትንሽ ቆይቶ በሌሎች አካባቢዎች የጸጥታው ችግር ሲብስ የሚመለስበት ሁኔታ ነው ያለው።

የተለዬ የተሰጠ ትኩረትም የለም። የተለዬ መፍትሄም የለም ”
ብለዋል።

በየጊዜው ጥቃት እንደሚፈጸም ቢገልጹም ጥቃቱ እስካሁን አለመቆሙን እየተገለጸ ነው፤ ችግሩ እንዲቆም ምን መደረግ አለበት ? እንደ ህዝብ ተወካይነትዎ ያለዎት መልዕክት ምንድን ነው? የሚል ጥያቄም አቅርበናል።

አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ምን መለሱ?

“ የምናስተላልፈው መልዕክት መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ነው። በተጨማሪም ህዝቡን ራሱን መጠበቅ መቻል አለበት።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተቻለው ጥረት እያደረገ ነው። በዬአካባቢዎቸለ የሚነሱ ግጭቶችን ኢንፍሎንስ ያደርጋል ኃይል በመላክና ትኩረት እንሰጥ በማድረግ። 

የፓሊስ አባላት፣ ሚሊሻም በደንብ ተመልምሎ ለህዝቡ ጥበቃ እንዲያደርጉ መንግስት ከሌላው አካባቢ በተለዬ ሁኔታ ይህን ያመቻች የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር ለክልሉም፤  አሁንም ይህ ጥበቃ ቢደረግ ነው የተሻለ የሚሆነው።

በዘላቂነት ግን ከአገራዊ ሁኔታው ጋር በተያያዘ ጀነራል ኦፕሬሽን ሰርቶ ብቻ ነው ችግሩን ማቃለል የሚቻለውና ለዛ ትኩረት ይሰጥ።"


በኮሬ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ከጉጂ በሚነሱ ታጣቂዎች ዘርፈ ብዙ ጥቃት እንደሚያርሱባቸው በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጭምር መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አሁንም ጥቃቱ ባለመቆሙ የመንግስትን ትኩረት እየተማጸኑ ይገኛሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ምሽት 4:41 ላይ ከመተሐራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አመልክቷል። መሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን አመልክቷል። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ነው የተሰማው። @tikvahethiopia
" ያለማቋረጥ እየመዘገብን ነው እስካሁን 4.9 ነው የተመዘገበው አሁንም ያለው ነገር ስናየው የሚቆም አይመስልም " - ፕ/ር አታላይ አየለ

በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ የሃገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ እየተሰማ ያለው ከዝቅተኛ መጠን እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ ያለው የማግማ እንቅስቃሴ ፈጣን (Active) በመሆኑ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል።

ይህ ፈጣን እንቅስቃሴ በመቀነሱ ምክንያት የመሬት መንቀጥቀጡ ረገብ ብሎ የነበረ ቢሆንም ካለፉት 6 ቀናት ወዲህ ይህ እንቅስቃሴ በድጋሚ መታየት መጀመሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም፤ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" መስከረም እና ጥቅምት ላይ ይታይ የነበረው እና ረግቦ የነበረው እንቅስቃሴ ከ6 ቀን በፊት ጀምሮ በድጋሚ መታየት ጀምሯል ያለማቋረጥ እየመዘገብን ነው እስካሁን 4.9 ነው የተመዘገበው አሁንም ያለው ነገር ስናየው የሚቆም አይመስልም " ብለዋል።

ትላንት ማታ 4:41 ላይ ከተመዘገበው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ሌላ ትንንሽ እንቅስቃሴዎች አሁንም በመኖራቸው ያለማቋረጥ የመመዝገብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

መንቀጥቀጡ እስካሁን ከመነሻው ቦታው አዋሽ ፈንታሌ ያደረገው ለውጥ እንደሌለ የተናገሩት ፕሮፌሰሩ ሌሎች አካባቢ እየተሰማ ያለው ድንጋይ ውሃ ውስጥ ስንወረውረው እንደሚፈጥረው አይነት ሞገድ መሆኑን ጠቁመዋል።

" አሁን ባለው ሁኔታ የከፋ ነገር ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት የለም " ያሉ ሲሆን በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ግን ሁለት አይነት መላምቶችን ሊታዩ እንደሚችሉ አስቀምጠዋል።

" አንደኛው ልክ እንደዚህ ቀደሙ ውስጥ ያለው ሃይል ሲጨርስ አስተንፍሶ ይቆማል ያ ካልሆነ ግን ሁለተኛው ምናልባት ገፍቶ የቅንጣሎች ፍሰት ሊያስከትል ይችል ይሆናል ምናልባትም ሃይል ያለው እና እንደጎርፍም ሊፈስ የሚችል ይሆናል " ነው ያሉት።

እንደዚህ አይነት ነገር የሚመጣ ከሆነ ቅድመ ሁኔታዎች የማስቀመጥ እና የማሸሽ ስራ የሚሰራ በመሆኑ በተዋረድ ያሉ የመንግስት አመራሮች ይህንን ሁኔታ ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🚨“ አቶ ክርስቲያን ታደለና ዮሐንስ ቧያለው ዛሬ የሐኪም ቀጠሮ ነበራቸው ማረሚያ ቤቱ አልወሰዳቸውም ” - ቤተሰቦቻቸው 🔴 “ በሕይወት የመኖር መብታቸውን ነው ያሳጧቸው። የእስረኛ ዝውውር ወይስ በሕይወት የመኖር መብት ነው የሚቀድመው ? ” - ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ አዋሽ አርባ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት ባደረባቸው የጤና እክል በወቅቱ ባለመታከማቸው ለአንጀት ድርቀት ህመም የተዳረጉት አቶ…
“ አቶ ዮሐንስን ቧያለውን ለይተው ‘ዞን አምስት’ የሚባል ቦታ አስገብተውታል። ያ ቦታ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሰው ከባድ ጥፋት ሲያጠፋ መቅጫ ነው ” - ጉዳዩን የሚከታተሉ አካል

ለ1 ዓመት ከ5 ወር በእስራት ላይ የሚገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው አብረዋቸው ከነበሩት 41 እስረኞች ተለይተው “ ለሕይወታቸው አስጊ ወደሆነ ቦታ ” ለማዘወር ተገደዋል ይህ ደግሞ ጭንቀት ፈጥሮብናል ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ሰኞ ታኀሳስ 14 ቀን 2017 ዓ/ም 41 እስረኞች ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ቂሊንጦ እንደተዘዋወሩ ገልጸው፣ አቶ ዮሐንስን ለይተው “ በ‘ሸኔ ተጠርጥረው’ ካሉ ሰዎች " ጋር ወስደዋቸዋል ሲሉ ጠቁመዋል።

በመሆኑም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ያሉበትን ቦታ ጎብኝተው የአቶ ዮሐንስን ሕይወት ደህንነት እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል።

ስለአቶ ዮሐንስ ቧያለው በዝርዝር የተባለው ምንድን ነው ?

“ ትላንት እስረኞቹን ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ቂሊንጦ አዘዋውረዋል። 41 እስረኞችን ነው ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የወሰዱት። 

ከዚያ በኋላ አቶ ዮሐንስን ቧያለውን ለይተው አስቀርተው ‘ዞን አምስት’ የሚባል ቦታ አስገብተውታል። ያ ቦታ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሰው ከባድ ጥፋት ሲያጠፋ መቅጫ ነው።

እዛ ውስጥ ያሉት በ'ሸኔ' ተጠርጥረው ያሉ ሰዎች ናቸው።  ለይተው ከእነርሱ ጋር ነው  ያስቀመጡት። ‘ሸኔ ናችሁ’ ተብለው የታሰሩ፣ ‘ሸኔ’ የተባሉ ልጆች ናቸው እዛ ያሉት።

ይሄ ሁኔታውን ያከብደዋል። በዛ ላይ ደግሞ ኦፕራሲዮን ከተሰራ ሁለት ሳምንቱ ነው። አሁን ካስገቡት ቦታ አልጋ የሚባል ነገር የለም። ባዶ መሬት ላይ ነው እየተኛ ያለው።

አቶ ዮሐንስ አሁን የገባበት ቦታ በጣም የሚያሰጋ፣ እንኳን ኦፕራሲዮን የተደረገ ጤነኛ ሰውም የሚታመምበት ክፍል ነው። ቤቱ በጣም ቅዝቃዜ ስላለው እያነከሰ ነው። ”
ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ዮሐንስ ከ41 እስረኞች ተለይተው የተወሰዱት ምክንያት በግልጽ ሳይታወቅና ከአቶ ክርስቲያን ታደለ ጋር ኦፕራሲዮን ተሰርተው የነበረ ቢሆንም በቀጠሯቸው ቀን ሀኪም ቤት ሳይሄዱ በቀሩበት ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል።

አሁንም የጤናቸው ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ፣ ለአቶ ዮሐንስ ማስታገሻ መድኃኒት እንኳ ለመውሰድ ፈቃድ እንዳልተገኘ፣ ቁስላቸውን መመርመር ባለመቻላቸው በጠና እየታመሙ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አካላት ጠቁመዋል።

አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና ክርስቲያን ታደለ በአዋሽ አርባ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት በጠና ታመው በጊዜው ባለመታከማቸው ለአንጀት ድርቀት በሽታ ተጋልጠው ከቆዩ በኋላ ከሳምንታት በፊት ቀዶ ጥገና ቢደረግላቸውም በቀጠሯቸው ቀን ወደ ህክምና ለመሄድ መከልከላቸውን መነገሩ ይታወሳል።

(የአቶ ዮሐንስን የቦታ ለውጥ እንዲገመግሙ መልክዕት የተላለፈላቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ድርጊቱን ገምግመው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ ማብራሪያቸው በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ተመን ወጪ 100 በሆነበት ማግስት አንድ ዳቦ ለቁርስ ማቅረብ ማሻሻል አይደለም " -የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከተሻሻለው የምግብ ሜኑ ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው የተፈጠረ ግርግር ለተማሪዎች መጎዳት እና ለንብረት ውድመት ምክንያት መሆኑ ተሰምቷል። ለአለመግባባቱ መነሻ የሆነው በትምህርት ሚኒስቴር በተሻሻለው እና በሁሉም የዩኒቨርሲቲዎች…
#Update

“ መቐለ ብቻ አይደለም። ትላንት ደብረ ብርሃንም ፣ ደባርቅም ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተነስቷል ቅሬታው ” - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት

🚨 " የታሰሩ ተማሪዎች ተፈተዋል !! "

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የምግብ በጀት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

በዚህም ትምህርት ሚኒስቴር አጠናሁት ባለው ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ጥናት መሠረት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የምግብ በጀት ከታኀሳስ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በቀን 100 ብር እንዲሆን መወሰኑ አይዘነጋም።

ውሳኔው ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአዲሱ የምግብ ሜኑ ቅሬታ እንዳላቸው እየገለጹ ይገኛሉ።

በመቐለ ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደባርቅና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ትላንት ቅሬታቸውን በአደባባይ መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በነበረው በዚሁ ሂደት በተማሪዎቹ ድብደባ እስራት እንደደረሰ፣ ንብረት እንወደመም ተመልክቷል።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትላንት በተፈጠረው ግርግር የታሰሩ ተማሪዎች ተፈቱ ? ምን ያህል ተማሪዎች ናቸው የታሰሩት ? ስንል የጠየቅነው ኀብረቱ፣ “ 27 አካባቢ ተማሪዎች ነበሩ የታሰሩት ” ሲል መልሷል።

ኀብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣“ ታስረው የነበሩት ሁሉም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተፈተትተዋል። አሁን እዛ እየወጣን ነው ” ሲል አረጋግጧል።

“ ሁሉም ነገር ተረጋግቷል። ተቋሙ የራሳቸው በመሆኑ ተማሪዎች መጠበቅ እንዳለባቸው፣ የወደመው ንብረትም በጋራ መስተካከል ያለበት እንዲስተካከል ማሰሰቢያ ተሰጥቶ ሁሉንም አስፈትተናቸዋል ” ነው ያለው።

“ ተማሪዎቹ ታስረው የነበረው ቀዳማዊ ወያኔ እና ኣደ ሓቂ ነበር። ግማሾቹ ከቁኑ ስምንት ሰዓት ገደማ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል ነው የፈቱት ” ብሏል።

በተማሪዎች ላይ ድብደባ ደርሷል የተባለውን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀነው በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ “ ተማሪ ላይ ድብደባ ደርሷል። ጉዳትም ደርሷል ” ነው ያለው።

የአዲሱ የምግብ ሜኑ ውሳኔ ቅሬታ ያሳደረው በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚገኙ ተማሪዎች ብቻ እንዳልሆነ ኅብረቱ ገልጿል።

ኅብረቱ “ መቐለ ብቻ አይደለም። ትላንት ደብረ ብርሃን፣ ደባርቅም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተነስቷል ” ሲል ነው ያስረዳው።

“ በይበልጥ የመቐለው ፓለቲሳይዝ ስለሆነ ነው እንጂ በሌሎችም እኮ አለ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡበት በዚሁ በሜኑ ጉዳይ። ጉዳዩ አገራዊ ነው እየሆነ ያለው ” ሲልም አክሏል።

የሰላማዊ ሰልፉን ምክንያት በተመለከተ በሰጠን ማብራሪያ ኀብረቱ፣ “ አዲስ የወጣውን የምግብ ፓሊሲ እንቀበላለን አንቀበልም በሚል ነው ” ብሏል።

ቅሬታ የተነሳበትን የምግብ ሜኑውን በተመለከተ ከትምህር ሚኒስቴር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ለመወያዬት ቀጠሮ እንደያዘም ኅብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

“ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲው፣ የመቐለው አሁን ተረጋግቷል። ኮንሰርኑ ግን የ100 ብሯ ጉዳይ  ነው ” ሲልም ገልጿል።

ቅሬታው በሌሎችም ዩኒቨርቲዎች መሆኑን ኀብረቱ በገለጸው መሠረት ቅሬታ አለበት የተባለውን ደባርቅ ዩኒቨርሲቲን የጠየቅን ሲሆን፣ የአዲሱ ሜኑ ጉዳይ ለእርሱም ጥያቄ  እንደሆነበት ገልጿል።

(አዱሱን የምግብ ሜኑ የተመለከተው የተማሪዎቹ ቅሬታና የደባርቅ ዩኒቨርሲቲዝርዝር ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia