TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia🇪🇹

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቱርክ አንካራ ፤ ከሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ጋር ያደረጉትን የፊት ለፊት ውይይትና ድርድር አጠናቀው ጥዋት አዲስ አበባ መግባታቸውን ከጠ/ሚ ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ምን ተስማሙ ? በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስምምነቱ " የአንካራ ስምምነት " ተብሏል። ይህ ተከትሎ በወጣው የስምምነት ሰነድ የተስማሙባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተቀምጠዋል። ምንድናቸው ? ➡️ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች አንዳቸው ለሌላኛቸውን…
ሶማሊያውያኑ ምን እያሉ ነው ?

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሶማሊያውያን በተለይም አክቲቪስቶች " ሀሰን ሼክ ሀገራችንን ሸጠብን ፤ በዲፕሎማሲ ተበልጦ አስበላን " ማለት ጀምረዋል።

ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉላዓዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት ባከበረ ሁኔታ ዘላቂነት ያለው አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ታገኛለች መባሉ የሶማሊያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አበሳጭቷቸዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ በX ቪላ ሶማሊያ ገጽ ስር ፤ ከወራት በፊት ሲያሞጋግሷቸው የነበሩትን ፕሬዜዳንታቸውን ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ላይ ውግዘት ማዝነብ ጀምረዋል።

እኚህ አስተያየት ሰጪዎች ምን እያሉ ነው ?

➡️ " ሀሰን ሼክ ባህራችንን ሸጠብን። ካደን ፤ ከሀዲ ነው "

➡️ " እንዴት በድርድሩ ላይ ሆነ በስምምነቱ ላይ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የባህር በር ለማግኘት የፈረመችው የመግባቢያ ስምምነት / MoU አልተነሳም ፤ በግልጽ ቀርቷል ለምን አልተባለም "

➡️ " አዋረደን ! ለሶማሊያ ጨለማ ቀን ነው "

➡️ " ስለ ኢትዮጵያ የቀጣይ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ (ሶማሊያ ውስጥ) ለምን አለተነሳም "

➡️ " ዘላቂነት እና አስተማማኝ የባህር በር ኢትዮጵያ ስታገኝ ሶማሊያ በምላሹ ምን ታገኛለች ? "

➡️ " ሁሉንም ኢትዮጵያ የፈለገችውን ነው የተቀበልነው፤ ኢትዮጵያ በመረጠችው መንገድ ሄዳ ፤ በዚህም በዚያ ብላ ባህር በር ስታገኝ እኛ ምን አገኘን ? " 

➡️ " ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲው እና ድርድሩ በልጣ ባህር በር አሳካች " ... የሚሉ አስተያየቶችን በመስጠት ፕሬዜዳንታቸው ላይ ውግዘት እና የስድብ ናዳ እያወረዱ ነው።

አንዳንዶቹ ከቦታው ይነሳልን ወደማለትም ገብተዋል።

120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ " በፍጹም የማልተወው የህልውዬ ጉዳይ ነው " ብላ በይፋና በድፍረት አደባባይ ከወጣች በኃላ ጉዳዩ ከፍተኛ አጀንዳ ሆኖ ዓለም አቀፍ መወያያ መሆን ችሏል።

ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ከተፈራረመች በኃላ ሶማሊያ አኩርፋ ብዙ ስትል ከርማለች ፤ ከኢትዮጵያ ጋርም ተጎረባብጣለች።

ፕሬዜዳንቷ እና አስተዳደራቸው በየጊዜው ወደ ሚዲያ እየወጡ ፦
- ከኢትዮጵያ ጋር በፍጹም አንነጋገርም፤
- የኢትዮጵያ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ላይ አይሳተፉም፤
- እንድንነጋገር ከፈለገች MoU ቀዳ ጥላ በይፋ ይቅርታ ትጠይቅ ይህ ካልሆነ ኢትዮጵያን አንሰማትም፤
- በኢትዮጵያ ያሉ ታጣቂዎችን እንደግፋቸዋለን / እናስታጥቃለን፤
- ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ደሟን እንዳልገበረችላት የኢትዮጵያ እድገት እንቅልፍ ከሚነሳቸው አካላት ጋር እየሄደ ጥምረት ሲፈጥር
- ከኢትዮጵያ ለመነጋገር ቅድመ ሁኔታዎችን ሲደረድር ... ሲዝት ፣ ሲፎክር ከርሟል።

በመጨረሻ በቱርክ አሸማጋይነት አንካር ሄደው ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በስምምነቱ ይፋዊ ሰነድ ላይ ሆነ በመሪዎች መግለጫ ምንም ቦታ ላይ ስለ ሶማሊለንዱ MoU አለመነሳቱ ፤ ማብራሪያ አለመሰጠቱ እንዲሁም በግልጽ ተሰርዟል አለመባሉን በማንሳት " ኢትዮጵያ የምትፈልገውን አገኘች " በማለት ሶማሊያውያን በፕሬዜዳንታቸው ላይ ተነስተዋል።

#TikvahEthiopia
#Ethiopia🇪🇹
#Seaaccess

@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #AddisAbaba

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መቼ ይካሄዳል ?

38ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት መጀመሪያ ሳምንት ይካሄዳል።

አዲስ አበባ የፊታችን የካቲት ወር መጀመሪያ ሳምንት የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ታስተናግዳለች።

ለዚህም ጉባኤ ሁሉን አቀፍ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች እንደሆነ ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባዔውን የኢትዮጵያን ገጽታና የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነት በሚያሳድግ መልኩ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጣጥና የሆቴል ፋሲሊቲዎች መሰረት በማድረግ 42 ሆቴሎች እንግዶቹን እንዲያስተናገዱ መመረጣቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር መረጃ ያሳያል።

ሆቴሎቹ በሕብረቱ ጉባዔ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል።

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሁም 46ኛው የህብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። #ENA

Photo Credit - Addis Ababa Mayor Office

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia #France

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ገቡ።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከደቂቃዎች በፊት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።

ማክሮን አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ቪድዮ ፦ ቢኤፍኤም ቲቪ

@tikvahethiopia