TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia #SW ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ። የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ። ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው። በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን…
" አልሸባብ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት ተመልሷል " - ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው

የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት እርምጃ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በሶማሌ ክልል በ5 ትናንሽ የጠረፍ አካባቢዎች ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ሙከራ በጸጥታ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሉ ተቆርጠው የቀሩትን የሽብር ቡድኑ አባላትን የማጽዳት ዘመቻ ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ባለፉት ቀን ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡ በዚህም በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ጠቁመዋል፡፡

ነገር ግን የሽብር ቡድኑ #ዛሬ_ሌሊት ላይ የተበታተነ ኃይሉን በማሰባሰብ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት አካባቢ ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም መሞከሮ ነበር።

ሆኖም የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኑ ዳግም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራዎችን ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ነው ያብራሩት፡፡

እስካሁን ባለው መረጃም ከ150 በላይ የሽብር ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውንና የሽብር ቡድኑ ለአጥፍቶ መጥፋት ያዘጋጃቸው ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንደተማረኩ አመልክተዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
#China

ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ስለ ቻይና-ታይዋን ጉዳይ ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሞኑን የቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ለኢዜአ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኑን ተናግረዋል።

" የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት " አምባሳደር መለስ፤ " ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው " ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለ #አንድ_ቻይና ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉ ሲሆን ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት የሚያራምዱት አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

#ሱዳን

ሱዳን ለአንድ ቻይና መርህ ድጋፏን እንደምትሰጥ አሳውቃለች። ታይዋንም የቻይና ግዛት አካል መሆኗን ገልጻለች።

ሱዳን ፤ ቻይና ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነትዋን በመጠበቅ ረገድ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

#ኤርትራ

ኤርትራ የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነው ብላለች።

የአፈጉባኤዋ ድርጊት የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም " የአንድ-ቻይና " ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነው ስትል ገልፃለች።

ኤርትራ፤ አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች ነው ብላ ድርጊቱ አጸያፊ ነው ብላለች።

#CGTN #ENA #AlAIN #Shabait

@tikvahethiopia
#SNNPRS #SouthWestEthiopia

የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

👉 ለወንዶች 41፣
👉 ለሴቶች 40 እና
👉 ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

👉 ለወንዶች 39፣
👉 ለሴቶች 38 እና
👉 ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
"ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል"

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዳግም ያገረሸው ግጭት ተባብሶና ሰፍቶ እየቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት መሳሪያ ወርዶ ወደ ንግግር እንዲገባ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ቀጥለዋል።

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ" ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል" ሲል የሰላም ጥሪ አቅርቧል።

ጉኤው ምን አለ?

- ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊቆምና የሰላም ሂደቱ ሊቀጥል ይገባል።

- የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው።

- ከዚህ ቀደም የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል፤አሁንም የሰላም ጥሪ እናቀርባለን።

- የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሌሎችም ወገኖች ለዚህ ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል።

- የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል።

- ህፃናትን ለወታደራዊ ዘመቻ ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ ሊቆም ይገባል።

- በወቅታዊ ጉዳይ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል።

- ትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች መሪዎች የትግራይ ክልል ወደ ሰላማዊ ድርድሩ እንዲመለስ በመምከር አባታዊና መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

- የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡና የውጭ ሀገራት መንግሥታት፣አፍሪካ ሕብረት፣ ተመድና ሌሎች አካላት ሁሉ የሰላም ጥረቱ አጋዥ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።

- የጳጉሜን 5ቱን ቀናት ምእመናን በፆምና ፀሎት እንዲያሳልፉ ጥሪ እናቀርባለን።

(የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ)

#ENA

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ያለውን ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

- በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት " #አንፈተንም " በሚል ለቀው ወጥተዋል፤ ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለፃል።

- በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል።

- ከተጠቀሱት (#ሀዋሳ እና #መቅደላ_አምባ) አካባቢዎች #በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ ነው።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
#Update

ዛሬ " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " አባላት ፤ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አጠቃላይ ሂደት እና ቀጣይ ስራዎችን በሚመለከት ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ለሁለቱ ም/ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች ፣ ለክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች ፣ ለከፍተኛ ባለስልጣናት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሀሴን የተናገሩት ፦

- ስምምነቱ በዋናነት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነትን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝቦችን የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቋል።

- በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችልና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- ከህገ-መንግስት ውጪ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቆመው በትግራይ ክልል በህገ-መንግስቱ መሰረት ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ #ጊዜያዊ_አስተዳደር ይቋቋማል።

- ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ቀደመው ማህበራዊ ትስስር እንዲመለሱ በጋራ ይሰራል።

- የወደሙ ተቋማትን ጨምሮ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በጋራ ርብርብ ሊከናወኑ ይገባል። የትስስርና የተግባቦት ስራዎች የህዝቦችን መጻኢ የጋራ ጉዞ ታሳቢ ያደረጉ ሊሆኑ ይገባል።

- በግጭቱ ምክንያት በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እንዲሁም በሌሎች መስኮች የደረሰውን ጫና በማስተካካል ረገድ በትብብር መስራት ይጠበቃል።

- የመገናኛ ብዙሃን #ቁርሾዎችን ማባባስ ሳይሆን ዜጎች ከችግሩ ተምረው በቀጣይ አብሮነታቸውን አጠናክረው የሚሄዱበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ሊሰሩ ይገባል።

- #በማወቅም ሆነ #ባለማወቅ የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሰሩ ኣካላትን በጋራ ማስቆም ይገባል።

- ሁሉም ዜጋ ለሰላም ስምምነቱ #ተግባራዊነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ  ይገባል።

#ENA

@tikvahethiopia
#Update

" ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየር እና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል " - የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

ዛሬ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ፤ ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ #ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብአዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን አስታውቋል።

የሰብአዊ ድጋፍ ተቋማት በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል።

ይህ የተገለፀው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለተለያዩ #ዓለም_አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

አምባሳደር ሽፈራው ፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ ተቋማት የየብስም ሆነ የአየር ትራንስፖርት ክፍት ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።

በአፋር ክልል ከአብዓላ መቐለ ፣ በሁመራ በኩል ሽራሮ ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ፤ በጎንደር አዲ አርቃይ ማይጸምሪ ሽሬ እንዲሁም የወልዲያ አላማጣ መስመሮች ሁሉም ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት እንደሆኑ ተናግረዋል።

በአፋር ክልል ከአብዓላ መቐለ መስመር የሙከራ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፤ በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ በኩል ከገቡ 16 ከባድ መኪናዎች መካከል 3ቱ የሕክምና ቁሳቁስ ይዘው መግባታቸውን አመልክተዋል።

" ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየር እና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል " ብለዋል ኮሚሽነሩ።

#ENA

@tikvahethiopia
#መልዕክት

የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፦

" የገና በዓል ሲከበር ህብረተሰቡ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።

በበዓሉ ወቅት ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በፍጥነት ለመቆጣጠር ከተለያዩ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር ተዘርግቷል።

እሳትና ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በነጻ የስልክ መስመር 939 ፤ በቀጥታ የስልክ መስመሮች 011 155 53 00 ወይም በ 011 156 86 01 ደውሎ ማሳወቅ ይቻላል። "

#ENA

@tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣ የምግብ ደኅንነት ኢንስፔክተር መሀመድ ሁሴን ፦

" ሕብረተሰቡ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦችን የመጠቀሚያ ጊዜያቸውን እያስተዋለ መግዛት አለበት።

በተለይ መጪዎቹን የበዓል ወቅቶችን አስታኮ በርካታ ጊዜያቸው ያለፋባቸው ምግቦችና መጠጦች በቅናሽ ዋጋ ወደ ገበያ ሊወጡ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።

ከምግብ ጋር  የተለያዩ ባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል አላስፈላጊ ትርፍ ለማጋበስ ከሚጥሩ ሕገ-ወጦችም ራስን መጠበቅ ይገባል።

ሕብረተሰቡ የሚገዛቸውን የምግብና የመጠጥ ምርቶች በጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ምርቶቹን ከመግዛቱ በፊት ማን እንዳመረታቸው ? መቼ እንደተመረቱና ? የመጠቀሚያ ጊዜያቸው መቼ እንደሚያልቅ? በአግባቡ ማየት አለበት።

ከእነዚህ ምግቦችና መጠጦች መካከል #ጁሶች ፣  የተለያዩ የታሸጉ #ብስኩቶችና ሌሎች #መጠጦች ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል።

በተለይ ሕገ-ወጥ የሆኑና ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ወይም በክልል ጤና ቢሮዎች ሥር ባሉ ተቆጣጣሪ የፈቃድ ማረጋገጫ ሳይወስዱ የምግብ ንግድ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሕገ-ወጦች አሉ።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ የራሱን መቆጣጠሪያ ስልቶችን ነድፎ ቁጥጥር ያደርጋል ፤ ሕብረተሰቡ ለዚህ ሥራ የሚሰጠው መረጃ ቀላል ባለመሆኑ የተለመደ ትብብሩን ሊያደርግ ይገባል። "

#ENA

@TIKVAHETHIOPIA
#Mettu

1.3 ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረግበታል የተባለው የመቱ-ጎሬ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።

በ166 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በሶስት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።

ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች በተለያዩ መስኮች የስራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር የተገለፀ ሲሆን የመንግስት አካላት እና ሕብረተሰቡ ለስራው ስኬታማነት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የሚከበሩት እና የሚታወቁት የአካባቢ ጉዳይ ሳይንቲስት ዶክተር ተወልደብርሃን ገብረ እግዚአብሔር የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ተፈፅሟል።

ስርዓተ ቀብራቸው በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ነው የተፈፀመው።

ዶ/ር ተወልደብርሃን ገ/እግዚአብሔር ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ/ም ሕይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

#ENA

@tikvahethiopia
#Update

ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ፍቃድ ሊሰጥ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ፍቃድ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ባለሥልጣኑ ከህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት ማቆሙ ይታወቃል።

ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የተሻሻሉት መመሪያዎቹ ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ፈቃድ የነበራቸውን ጨምሮ ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ እንደ አዲስ ምዝገባ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ምዝገባው በዘንድሮ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን በ2016 ዓ.ም አዲስ ፍቃድና የእድሳት አገልግሎት መስጠት ሊጀመር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ 360 የሚጠጉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን መረጃ ያሳያል። #ENA

MORE : @tikvahuniversity
ጠቅላይ ኢተማዦር ሹሙ ምንድነው ያሉት ?

የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ኢተማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፥ " ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም " ብለዋል።

ይህንን ያሉት የክልል ልዩ ሃይሎችን በፌዴራልና የክልል የጸጥታ ተቋማት መልሶ የማደራጀት ስራ የመከላከያ ጀነራሎች፣ ፌዴራል ፖሊስ እና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ሲገመገም ነው።

ፊልድ ማርሻሉ ምንድነው የተናገሩት ?

" የክልል ልዩ ሃይሎች እንደገና በመደራጀታቸው ህብረ ብሄራዊ ጠንካራ የጸጥታ ተቋም ይገነባል።

የክልል ልዩ ኃይሎች አደረጃጀት ህጋዊ አለመሆን፣ በክልሎች መካከል እንደ ስጋት መተያየት እንዲሁም ችግሮችን በሃይል ለመፍታት የሚደረገው እንቅስቃሴ አደረጃጀቱን ለመቀየር አስገድዷል።

በአሁኑ ወቅት በሁሉም ክልሎች መልሶ የማደራጀት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀትና መዋቅር የለም።

በመሆኑም የጸጥታ መዋቅሩ መከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ ሲሆን በክልል ልዩ ኃይሎች ስም ተልዕኮም ሆነ ግዳጅ የሚቀበል ኃይል አይኖርም።

ከዚህ በኋላ በመረጡት አደረጃጀት መሰረት ሁሉንም ወደ ተመደቡበት የማጓጓዝና ወደ ስልጠና የማስገባት ስራ ይከናወናል። "

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የ2016 ዓ/ም የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ እየተከበረ ይገኛል።

#TikvahFamilyBishoftu / #ENA

@tikvahethiopia
#Oromia

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትን በ20 በመቶ ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወንኩ ነው አለ።

ይህን ያለው የክልሉ የትምህርት ጥራት  ሽግግር የመጀመሪያው ጉባኤ በአዳማ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።

እንደ ቢሮው መረጃ ፦

- ባለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱት የክልሉ ተማሪዎች 1.8 በመቶ ብቻ ናቸው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡት።

- የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተኑት 518 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- የተመዘገበው የ12ኛ ክፍል ውጤት የትምህርት ጥራት ችግር እጅጉን አሳሳቢ መሆኑን ማሳያ ነው ብሏል። በዘንድሮው ፈተና ውጤቱን በ20 በመቶ ለማሻሻል እየተሰራ ነው ሲል አሳውቋል።

- የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 40 በመቶ ብቻ ወደ ዘጠነኛ ክፍል አልፈዋል።

- በክልሉ የ8ኛ ክፍል ካስፈተኑት 9 ሺህ 585 ትምህርት ቤቶች መካከል 971 የሚሆኑት አንድም ተማሪ አላሳለፉም።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመለየት ጥናት ማካሄዱን ገልጿል።

በዚህ ጥናት መሰረት ፦

* 47 በመቶ የሚሆኑት መምህራን የተሰጣቸው የትምህርት ክፍለ ጊዜ በአግባቡ ያለመጠቀማቸው አንዱ ችግር መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል።

* በትምህርት ዘርፉ የአመራር ሰጪነት ብቃት ማነስና የፖለቲካ አመራር አባላቱ ለዘርፉ ትኩረት ማጣት እንዲሁም የሱፐርቫይዘሮች ድጋፍና ክትትል ማነስ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው ሲል ገልጿል።

ክልሉ የትምህርት ጥራት ችግሮቹን ለመፍታት 15 ሺህ 520 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ከመገንባት ባለፈ ከ140 በላይ የሁለተኛ፣ ልዩና አዳሪ ትምህርት ቤቶች መገንባቱን ቢሮ አሳውቋል።

በተጨማሪ ብቁ መምህራን ለማፍራትና የመማር ማስተማር ስነ ዘዴን ለማሻሻል የሙያ ምዘና፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራ፣ የአይሲቲ ልማትና የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል ላይም እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

በዘንድሮው የ6ኛ፣ የ8ኛና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እየተሰራ ነው ብሏል።

🔵 በኦሮሚያ ክልል ከ11 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ አሉ።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የአከራይ እና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁ ይታወቃል፡፡

በዚህም አስተዳደሩ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቶቹን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ይዘው በመቅረብ ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ቤት አከራዮች ፦

➡️ ህጋዊ የምዝገባ ውል ለመፈጸም ወደ ወረዳ ጽ/ቤቶች በሚሄዱበት ወቅት ቤቱ የራሳቸው ስለመሆኑ ወይንም ህጋዊ ተወካይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተከራዮች ፦

➡️ ማንነታቸውን የሚገልጽ #መታወቂያ ወይም ሌላ ህጋዊ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

በስራ ሰዓት መመዘግብ የማይችሉ አከራይና ተከራዮች ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በስራ ቀን ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ ህጋዊ የውል ምዝገባውን መፈጸም ይችላሉ።

#ENA
#Ethiopia
#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የገበያ ስርዓቱ ችግር ካጋጠው ብሔራዊ ባንክ ጣልቃ ይገባል " - የብሔራዊ ባንክ ገዥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥው ማሞ ምሕረቱ ዛሬ ለኢዜአ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህም ማብራሪያ ስለ ውጭ ምንዛሬ ስርዓቱ መቀየር አንስተዋል። " ይፋ የተደረገው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ሕግ ማዕቀፍ በርካታ ለውጦች ይዞ ያመጣል " ሲሉ ገልጸውታል። በብሔራዊ ባንክ ብቻ ይተመን የነበረው ስርዓት በመደበኛውና…
" 2.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ሆኗል " - የብሔራዊ ባንክ ገዥ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ፥ እስካሁን ባለው ከዓለም አቀፉ የገንዘብ  ተቋም (IMF) እና ዓለም ባንክ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ ከውጭ ከሚገቡ የፍጆታ ዕቃዎች 18 በመቶ ብቻ በውጭ ምንዛሬ እንደሚመጡ ገልፀዋል።

ሌሎቹ በአብዛኛው በኢ-መደበኛ ወይም በትይዩ ገበያ ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ እንደነበር ጠቁመዋል።

በዚህም " የምንዛሬ ተመኑ ወደ ገበያ መር መለወጡ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ ሊፈጥር አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።

ባንኩ ህገ-ወጥነትና አሉታዊ ጫና የሚፈጥሩ ጉዳዮች ከተከሰቱ ህጋዊ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚከሰትን ህገወጥ አሰራር ለመቆጣጠር ጥብቅ የፊሲካል እና የገንዘብ ፖሊሲ ገቢራዊ ይደረጋል ሲሉ አውጀዋል።

በዚህም " ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ በቂ ዝግጅት አድርገናል " ብለዋል።

#NationalBankofEthiopia #ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሹመት : የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። @tikvahethiopia
#Update

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።

የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሕዳር 23/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳዳር ሆነው መሾማቸውን ገልጿል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። #ENA

@tikvahethiopia