TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥንቃቄ

በጥንቃቄ ጉድለት ሊደርሱ የሚችሉ የተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲል የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መልዕክት አስተላልፏል።

ኮሚሽኑ ፤ በሰው ልጅ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ድንገተኛ አደጋዎች መካከል አብዛኞቹ በጥንቃቄ ጉድለትና በመዘናጋት የሚከሰቱ ናቸው ብሏል።

በመሆኑም ለአደጋ መንስኤ የሚሆኑ የአሰራርና የአጠቃቀም ግድፈቶችን በማስወገድ ህይወትንና ንብረትን ከጉዳት ለመታደግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ማከናወን እንደሚገባ ገልጿል።

➡️ በምግብ ማብሰያ /ማዕድቤት/ አካባቢ የኤሌክትሪክ፣ የቡታ ጋዝ፣ የጧፍና የከሰል ምድጃዎችን በአግባቡና በጥንቃቄ ይጠቀሙ።

➡️ በገበያ ማእከላት የገበያተኛውን ቀልብ ለመሳብ የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ ዲኮሬሽኖች ቃጠሎ እንዳያስነሱ ይጠንቀቁ።

➡️ ሻማና ጧፍ በሚጠቀሙበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገር ያርቁት።

➡️ ካም ፋየር የሚያዘጋጁ ከሆነ ከአካባቢው ከመራቅዎ በፊት በደንብ መጥፋቱን ያረጋግጡ።

➡️ በኤሌክትሪክ እሳት የተነሳ እሳትን ሃይሉን ከምንጩ ሳያቋርጡ በወሃ ለማጥፋት አይሞክሩ።

➡️ ርችቶችን ሲተኩሱ በነዳጅ ማደያ ፣ በሳር ቤቶችና በሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ላይ እንዳያርፍ ይጠንቀቁ።

➡️ ጠጥተው አያሽከርክሩ ለመዝናናትዎ በገደብ ይስጡ።

➡️ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ የተለያዩ መሳሪያዎች በአንድ ሶኬት ላይ ደራርበው አይጠቀሙ።

➡️ ለአደጋ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድ/በመፍታት የሰው ህይዎትን እና ንብረትን መታደግ ያስፈልጋል።

ኮሚሽኑ ከአቅም በላይ ለሆነ ማንኛውም የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም የአምቡላንስ አገልግሎትን በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ሳምንቱን ሙሉ 24 ሰዓት በመደወል ማግኘት እንደሚቻል አሳውቋል።

° ነፃ የስልክ መስመር 👉 939
° ማዕከል 0111568601/0111555300

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የጤናባለሙያዎችድምፅ " ከ15 ወራት በላይ የዱቲ ገንዘብ አልተከፈለንም በዚህ ኑሮ ውድነት በብድር በዬ ወሩ ተሰቃየን " - ጤና ባለሙያዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ15 ቀናት የዘመቻ አበልና ከአንድ አመት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመፈጸሙ ችግር ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የጤና ባለሙያዎቹ ዝርዝር ቅሬታ ምንድን ነው…
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

🔵 " ቸግሮናልጠምቶናል፣ ርቦናል፣ ሰልችቶናል፣ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ የዱቲ ሳይከፈለን ለ17 ወራት ስንሰራ ከመንግስት አካል ማንም ያሰበን የለም " - ጤና ባለሞያዎች

🔴 " ምንም ምላሽ የለንም። ቢሮ መጥተው ይጠይቁን " - ወናጎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት

በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ያሉ ጤና ባለሙያዎች የወራት ያልተከፈለ የዱቲ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው በመጠየቃቸው ከደመወዛቸው እንዲቆረጥባቸው መወሰኑን በመግለጽ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

" ዱቲ ስላልከፈሉን የሰራነውን ገንዘብ ስለጠየቅን ብቻ ከሦስት ወራት በላይ ደሞዛችን ከ960 ብር ጀምሮ በስኬል  እየተቆረጠ ይገኛል " ብለው፣ ደመወዛቸው እንዲቆረጥ የተወሰነው የዱቲ ሥራ በማቆማቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የዱቲ ሥራ በመቆሙ ህዝቡም ችግር ላይ ስለሆነ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀው፣ " ካልሆነ ለሚፈጠር ችግር ተጠያቂ አንሆንም " ሲሉ አስጠይቅቀዋል።

በዞኑ ዲላ ዙሪያ ወረዳ ጪጩ ጤና ጣቢያ ያሉ ባለሙያዎቹ በበኩላቸው፣ የ17 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ያማረራቸውን ቅሬታ በተመለከተ በዝርዝር ምን አሉ ?

" በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የ17 ወራት የዱቲ ክፍያ ባለመከፈሉ የጪጩ ጤና ጣቢያ ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የዱቲ ሥራ በማቆም ሕዝቡ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል።

በተደጋጋሚ ለዞኑና ለወረዳው ቅሬታ ብናቀርብም ምላሽ በመስጠት ፈንታ ባለሞያዎችን ለእስር ሲዳርግ ቆይቷል። ለሦስት ዓመት ያክል በዱቲ ክፍያ እየተከራተተ የሚገኝ የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሞያ እስከ ዛሬ ተገቢ ምላሽ አላገኘም።

በጌዴኦ ዞን በወናጎ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሞያዎች የዱቲ ጥያቄ አቅርበው ተገቢ ምላሽ ባለማግኘታቸው መብታቸው ለማስከበር የዱቲ ሥራ በማቆማቸው በየወሩ ከደሞዛዝ እንዲቆረጥ ተወስኗል።

ዱቲ ስላልከፈሉን የሰራነውን ገንዘብ ስለጠየቅን ብቻ ከሦስት ወር በላይ ደሞዛችን ከ960 ብር ጀምሮ በየወሩ እየተቆረጠ ይገኛል። መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን።

ቸግሮናል፣ ጠምቶናል፣ ርቦናል ሰልችቶናል ሞራላችን ተነክቷል መውጫ ቀዳዳ አሳጥቶናል ከኑሮ ውድነት ጋር የዱቲ ሳይከፈለን ለ17 ወራት ስንሰራ ከመንግስት አካል ማንም ያሰበን የለም " ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቀው የወናጎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ቀጥተኛ ማብራሪያ በመስጠት ፋንታ፣ " ምንም ምላሽ የለንም። ቢሮ መጥተው ይጠይቁን " ብሏል።

ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስልክ ለማሳት ፈቃደኛ ባይሆኑም የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ ከዚህ ቀደም ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡትን ምላሽ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸውልን ነበር።

"ጉዳዩ በእርግጥ ያለ ነው። መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው። ያን ለመፍታት በጋራ እየሰራን ነው" የሚል ቃል ነበር የሰጡን።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

" ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል " - ተገልጋይ

በትግራይ ክልል ፣ መቐለ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ የሉም ፤ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፀጥታ ሃይሎች ጥበቃ ስር ይገኛል።

ተገልጋዮች ከከንቲባ ማግኘት ያለባቸው አገልግሎት ለማግኘት ቢመላለሱም የሚያስተናግዳቸው የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ጠዋት መቐለ አስተዳደር ፅህፈት ቅጥር ግቢ ድረስ ተጉዞ አጭር ምልከታ አደርጓል።

በአስተዳደሩ ዋና በር በቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተገለግጋሎች ሲገቡ ሲወጡ ይታዩሉ ፤ ፍትሻ በሚካሄድበት ቦታ ከተለመደው በተለየ ብዛት ያላቸው የፀጥታ አካላት ይስተዋላሉ።

5ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው የዋና ከንቲባ ፅህፈት ቢሮ  (ከህዳር 22/2017 ዓ.ም ) እንደታሸገ ሆኖ ግራና ቀኝ የፓሊስ ደንብ ልብስ በለበሱ የፀጥታ አካላት ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከከንቲባ የሚሰጥ አገልግሎት ለማግኘት ከአንድ ወር በላይ የተመላለሰ ተገልጋይ አግኝቶ አስተያየቱ ተቀብሏል።

ተልጋዩ ፀጋዛኣብ ርእሰደብሪ ይባላል የመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ነው።

ያለውን የመሬት ጉዳይ አስመልክቶ ከንቲባ አግኝቶ ለማነጋገር ቢመላለስም እስካሁን እንዳልተሳከለት ገልጿል።

" በሁለቱም በኩል ያሉ የህወሓት አመራሮች ማሰብ ተሰኗቸዋል ? ፤ ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል " ሲል በምሬት ተናግሯል።

ካለፈው ወርሀ ነሃሴ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ወደ ሁለት ቡድን መሰንጠቃቸው ያወጁት የደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን በየፊናቸው በየቦታው አመራር በመመደብና በመገለጫዎች መወራረፍ ቀጥለውበታል።

ባለፈው ወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የቀድሞ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ ተክቶ በደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እጩ አቅራቢነት በከተማው ምክር ቤት ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ረዳአ በርሀ (ዶ/ር) በጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ወድያውኑ ተቀባይነት ማጣታቸው ተከትሎ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ብርሃነ ገ/የሱስ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተሹመዋል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሸሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም በፅህፈት ቤቱና በክፍለ ከተሞች አመራሮች በቅጥር ግቢው በሚገኘው የመሰብሰብያ አዳራሽ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጨምሮ ሚድያዎች በተገኙበት አቀባበል ቢደረግላቸውም ከነጋታው ጀምሮ ይህ ዜና አስከተጠናቀረበት ሰዓት ተመልሰው ቢሮ አልገቡም።

በወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) እንዲሁም ቢሮ ላይ የሉም።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክር ቤቶች በመጠቀም ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ " በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት " በማለት መቐለ ጨምሮ በትግራይ ስድስት ዞኖች የየራሳቸው አስተዳዳሪዎች በመሾም ህዝቡን ግራ አጋብተውታል።

ይህንን መሰል ግራ የገባው የሁለቱ የህወሓት ቡድኖች አካሄድ ማብቅያው መቼ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
#AAiT

Call for Applications in MSc and PhD Programs 2024/25 Second Semester

1. Computer Engineering - MSc and PhD
2. Communication Engineering - MSc and PhD
3. Control Engineering - MSc and PhD
4. Electrical Power Engineering - MSc and PhD

School of Electrical & Computer Engineering, Addis Ababa University,

Application Deadline for GAT: Friday December 20, 2024

More information, see our channel https://t.iss.one/TrainingAAiT or check application procedure here.

Email: [email protected]
" የሚሠሩበት ቦታ የት እንደሆነ በግልጽ የማይታወቅ በመሆኑ፣ ዕርምጃ ለመውሰድ ተቸግረናል " - ባለስልጣን መ/ቤቱ

" ዘመናዊና ባህላዊ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን " ብለው በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ማስታወቂያ የሚያስነግሩ የተደራጁ ሕገወጥ ግለሰቦች መበራከታቸውንና ለቁጥጥር ፈታኝ እንደሆኑበት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል።

መ/ቤቱ ፤ የዘመናዊና ባህላዊ ሕክምና አገልግሎት በተመለከተ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንና የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ፈቃድ ሳይሰጡ ማስታወቂያ ማስተላለፍ እንደማይቻል በሕግ ተቀምጧል ብሏል።

በርካታ የተደራጁ ቡድኖች ግን ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግና ከሌሎች የሕክምና ተቋማት የበለጠ የተሻለ መሆናቸውን ለማሳየት በጣም የተጋነነ ማስታወቂያ እንደሚያስተላልፉ አሳውቋል።

ዘመናዊና ባህላዊ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን በሚል የተሳሳተ ማስታወቂያ ምክንያት፣ ሰዎች የሕክምና አገልግሎቱን እንሞክረው ብለው የተሳሳተ ነገር ውስጥ እንደሚገቡና ችግሩን ባለሥልጣኑ መቆጣጠር እንዳልቻለ አሳውቋል።

ችግሩ ትክክለኛ የሆነ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን እንዲመረዙ የሚያደርግ መሆኑን፣ እስካሁን የባህል ሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ 93 ተቋማት ባለሥልጣኑ መመዝገብ መቻሉን ጠቁሟል።

በሕገወጥ መንገድ ማስታወቂያ የሚያስተላልፉ የተደራጁ ቡድኖች የሚሠሩበት ቦታ የት እንደሆነ በግልጽ የማይታወቅ በመሆኑ፣ ዕርምጃ ለመውሰድ መቸገሩን መ/ቤቱ ገልጿል።

የባህል ሕክምና አዋቂዎች ማኅበር በበኩሉ ፤ የተለያዩ የሕክምና አገልግሎቶችን እንሰጣለን ብለው የተሳሳተ ማስታወቂያ የሚያስነግሩ ሰዎች አድራሻም ቢሮም እንደሌላቸው ገልጿል።

በማኅበር ሥር ሆነው የባህል ሕክምና አገልግሎት የሚሰጡት ግን፣ የተለያዩ ሥልጠናዎችን የሚወስዱና ባለሥልጣኑም ሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ያስቀመጡትን ሕግና ሥርዓት ተከትለው እንደሚሠሩ ገልጿል።

ዘመናዊና ባህላዊ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩ ግለሰቦች ማኅበሩን እንደማይወክሉ ለማሳወቅ፣ ማኅበሩ ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽንና ለሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤ ጽፎ ማስገባቱን አስታውቋል።

የባህል ሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ከበፊት ጀምሮ ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው ሲል የጠቆመው ማኅበሩ ፤ ከዚህ ቀደም የተሻለ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን ብለው ማስታወቂያ ባስነገሩ ሰዎች ገንዘባቸውን የተዘረፉ ሰዎች ለማኅበሩ ቅሬታ ማቅረባቸውን አስታውሷል።

አንድ የባህል ሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ የሕክምና ባለሙያ በማኅበራዊ ድረ ገጽም ሆነ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያ እንዲያስነግር ማኅበሩ ፈቃድ እንደማይሰጥ፣ የመስጠትም ሥልጣን እንደሌለው አክሏል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" አዲስ ሰላማዊና ፖለቲካዊ ትግል አካሂዳለሁ " - በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት

አዲስ ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግል ለማካሄድ ማቀዱን በደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት አስታወቀ።

ምን አይነት አዲስ ሰላማዊ የፓለቲካ ስልት ለማካሄድ እንዳቀደ ያላብራራው ደርጅቱ " ሰላማዊና ፓለቲካዊ ትግል ብቸኛ የችግሮች መፍትሄ ነው " ሲል አክለዋል

የደርጅቱ ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር ) ዛሬ በተጀመረ የክፍተኛ ካድሬዎች ውይይት ማስጀመሪያ የመክፈቻ ንግግራቸው ፤ " ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም አዲስ ሰላማዊ የፓለቲካ የትግል ስልት ህወሓት ቀይሷል " ያሉ ሲሆን " ስልቶቹ ከመተግበር በፊት ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለመግባባት ያለመ መድረክ መጥራት አስፈልጓል " ብለዋል።

" ህወሓት እንዳትበተን እና እንድትድን ከፍተኛ አመራሩ ተገቢ ትግል አካሂደዋል " ሲሉም ተደምጠዋል።

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችና ለውጦች የተለየ የትግል ስልት ፣ ለየት ያለ መመካከርና መደጋገፍ የሚጠይቁ ናቸው " በማለትም አክለዋል።

" ህዝቡ ተበትኗል ወደ ቄየው አልተመለሰም፤ ባለበት ቦታ ሆኖም ከፍቶታል ፤ በዚህ ላይ የአመራር ችግር ተጨምሮበት ህዝቡ እጅግ ከፍቶታል ፤ ስለሆነም ህዝብ ለማዳን የትግል ስልቶቻችን በማስተካከል ካለፈው የበለጠ ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግል ማካሄድ ይጠብቅብናል " ሲሉ ተደምጠዋል። 

በደብረፅዮን ገብረሚካኤል ( ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት የደርጅቱ  ማእከላዊ ኮሚቴ ያካሄዱትን ውይይት ተከትሎ የሚካሄድ የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ታህሳስ 9 እና 10 /2017 ለሁለት ቀናት በመቐለ የሰማእታት ሀውልት አዳራሽ እንደሚካሄድ የድርጅቱ ይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ላይ ሰፍሯል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

ዛሬውኑ የKimem Itel Pro ስልክ ከሳፋሪኮም ወስደው፣ ክፍያውን ቀስ እያሉ ይክፈሉ። እስከ 3000 ብር ቅድሚያ ክፍያ በመክፈል ቀሪዉን አመቺ በሆኑ የክፍያ አማራጮች እየከፈሉ በ10,447ብር ይግዙት። ለበለጠ መረጃ ወደ 700 ወይም *777*6# ይደዉሉ። እንዳያመልጥዎ!
  
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #1Wedefit #Furtheraheadtogether
ፎቶ ፦ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሕንፃ እድሳት ተጠናቆ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ እንደሚመለስ ተገልጿል።

ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል ተብሏል።

ካቴድራሉ እድሳት እየተደረገለት ከሁለት ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን ከ1 ወር በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል።

ለካቴድራሉ እድሳት እስካሁን 124,827,576 ብር የወጣ ሲሆን ያልተከፈለ 47 ሚሊዮን 672 ሺህ ብር ያለበት በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገረ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ቀሪ ክፍያውን ለማጠናቀቅ ታኅሣሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም የቀጥታ ስርጭት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር እንዲሁም ታኅሣሥ 27 ቀን በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ልዩ የምስጋና መርሐግብር ተዘጋጅቷል።

የካቴድራል የዕድሳት እና የጥገና ሥራ ከተጀመረ 773 ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን በየጊዜው በገጠመው የሲሚንቶ ችግር እና ሌሎችም ምክንያቶች ተጨማሪ 225 ቀናት መውሰዱን ተጠቁሟል።

#TMC

@tikvahethiopia
“ የሰብዓዊት መብት ተቋማት ባለበት ሂደው ይመልከቱት ቢያንስ መጀመሪያ በሕይወት እንዲቆይ ” - የአቶ ክርስቲያን ታደለ ቤተሰብ

ለ1 አመት ከ4 ወራት በእስር ላይ ሆነው ፍትህ እየተጠባበቁ የሚገኙት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አበል አቶ ክርስቲያን ታደለ ከባድ የጤና እከል ስለገጠማቸው በሕይወት እንዲቆዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዲጎበኟቸው የቅርብ ቤተሰባቸው አሳሰቡ።

ከፍትህ በፊት በሕይወት መቆየታቸው እንደሚቀድም ገልጸው፣ “ የሰብዓዊት መብት ተቋማት ባለበት ቦታ ሂደው ይመልከቱት ቢያንስ መጀመሪያ በሕይወት እንዲቆይ ” ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስበዋል።

የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ የጤናው ሁኔታ አሁንም በጣም አሳሰቢ ነው። ሰርጀሪ ተደርጎለት በሰዓታት ልዩነት ነው ወደ ማረሚያ ቤት የተመለሰው። እዛም ሆኖ የደም መፍሰስ አለበት።

ሰኞ እለት ቀጠሮ ስለነበር ሂዶ ነበር የሚፈሰው ደም ምን እንደሆነ ለማወቅ ብለው ደም ወስደዋል። ባለፈው ከአንጀቱ ውስጥ በሰርጀሪ የወጣውንና የተወሰደውን ደም ውጤት ለማወቅ ለነገ ሐሙስ ተቀጥሯል።

ህመም አለው። ‘ከፍተኛ ህመም ነው የሚሰማኝ’ ነው የሚለው። ለጊዜው የሚያስታግስለትን መድኃኒት ነው የሚጠቀመው።

ከዚህ ቀደም አያመውም ነበር። አዋሽ አርባ ከሄደ በኋላ ነው የታመመው። አሁን ሲነግረን አሟቸው ከአዋሽ ወደ አዲስ አበባ አምጥተዋቸው ነበር። የዛኔም ምርመራና በቂ ህክምና አላደረገም። 

የዛኔ አብረዋቸው ከአዋሽ የመጡ አካላት ፕራይቬሲያቸውን በሚጥስ ሁኔታ ‘አብረን ገብተን እንመለከታለን ህክምናውን’ በሚል አለመግባባት ተፈጥሮ ህክምና ሳያገኙ ተመልሱ።

የዛኔ ቢታከም መታጠብ ነበር የሚጠበቅበት ለሰርጀሪም አይደርስም ነበር። ህመሙ በድርቀት የሚመጣ ሲሆን፣  አንጀቱ ውስጥ ሌላ የቋጠረ ነገር ነበር።

እሱንም አሁን ሀኪሞቹ ለማብራራት ቆርጠው ካወጡት በኋላ ለምርመራ ተወስዷል። ነገ ነው ውጤቱ የሚገለጸው።

የፍርድ ሂደቱን በተመለከተ በሚገርም ሁኔታ በጣም ረጅም፣ ረጅም የሆነ ቀጠሮ ነው የሚሰጠው። አሁንም ገና ለጥር 13 ነው ቀጠሮ የተሰጣቸው።
 
እንደ ቤተሰብ ከምንናገረው በላይ እጅግ በጣም ከባድ ነው ያለንበት ሁኔታ። እሱ በነበረበት ወቅት ጥሩ በሚባል ሁኔታ ላይ ነው የነበርነው፣ አሁን ላይ እንደዛ አይደለም።

ፍትህ እንጠብቃለን። ተስፋ አንቆርጥም። ግን አሁን ያለው ሂደት በፍትህ ስርዓቱ ክርስቲያንንም ተስፋ እንዳቆረጠው ነው በተደጋጋሚ የሚነግረን፣ እኛም የምናየው።

የደም መፍሰሱ እንኳ አልቆመለትም በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ነው ያለው። የሰብዓዊት መብት ተቋማት ባለበት ቦታ ሂደው ይመልከቱት ቢያንስ መጀመሪያ በሕይወት እንዲቆይ።

በቂ የሆነ ህክምና እንዲያገኝ ያለበትን ሁኔታ ተረድተው የሰብዓዊ መብት አካላት እንዲጎበኙት እንፈልጋለን ”
ሲሉ ተማጽነዋል።

(የአቶ ዮሐንስ ቧ ያለው የቅርብ ቤተሰብ ለቲክቫህ ያቀረቡት እሮሮ በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ የሰብዓዊት መብት ተቋማት ባለበት ሂደው ይመልከቱት ቢያንስ መጀመሪያ በሕይወት እንዲቆይ ” - የአቶ ክርስቲያን ታደለ ቤተሰብ ለ1 አመት ከ4 ወራት በእስር ላይ ሆነው ፍትህ እየተጠባበቁ የሚገኙት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አበል አቶ ክርስቲያን ታደለ ከባድ የጤና እከል ስለገጠማቸው በሕይወት እንዲቆዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዲጎበኟቸው የቅርብ ቤተሰባቸው አሳሰቡ። ከፍትህ በፊት በሕይወት መቆየታቸው…
“ አሁንም በጣም ከፍተኛ በሆነ ህመም ውስጥ ነው ያለው ” - የአቶ ዮሐንስ ቧያለው የቅርብ ቤተሰብ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ዮሐንስ ቧያለው መጀመሪያ ታስረውበት ከነበረው በአዋሽ አርባ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አብረዋቸው ካሉ እስረኞች ጋር ተዘዋውረው ፍትህ እየተጠባበቁ ቢገኙም የጤናቸው ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የቅርብ ቤተሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

አቶ ዮሐንስ ከታሰሩ 1 አመት ከ5 ወራት አስቆጥረዋል።

ልጆቻቸውና ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ሲተዳደሩ የነበረው በአቶ ዮሐንስ አማካኝነት እንደነበር የገለጹት የቅርብ ቤተሰባቸው “ በጣም ከፍተኛ ችግር ላይ ነን ” በማለት፣ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

እኝሁ የአቶ ዮሐንስ ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

“ አሁንም በጣም ከፍተኛ በሆነ ህመም ውስጥ ነው ያለው። ደሙም ከመፍሰስ አልቆመም። ምክንያቱም አዋሽ አርባ እስር ቤት እያሉ በወቅቱ ስላልታከሙ ነው።

ህመሙ የጀመረው አዋሽ አርባ እስር ቤት እያለ ነው። እዛ እያለ ታመመ። በጣም እንደታመመ እዛ ላሉት አካላት ቢነግራቸውም በሰዓቱ ወደ ህክምና አልወሰዱትም ነበር።

በኋላ ላይ በጣም ሲታመምባቸው እሱንና አቶ ክርስቲያን ታደለን ይዘው ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በድብቅ ይዘዋቸው ገቡ። ከዚያ በኋላ ዶክተሮቹ ሊያክሙ ሲሉ አብረው የሄዱ ጥበቃዎች ‘የሚታከሙትን ነገር ገብተን እናያለን’ አሉ። ይሄ ደግሞ ፕራይቬሲን መጣስ ነው።

በመሆኑም ‘በዚህ ሁኔታ ውስጥ አንታከምም ይቅርብን እንጂ’ ብለው እንደተመለሱ ነው አሁን ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ የነገረን። 

እንደገና ከአዋሽ አርባ ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ ሜክሲኮም ሲገቡ ሲጠይቁ ነበር ‘ውስጣችን ደኀና አይደለም መታከም አለብን’ እያሉ። ያኔም መልስ አልተሰጠውም።

ቃሊቲም እያለ ‘እባካችሁ አሳክሙኝ እየታመምኩ ነው፣ የምመገበው ምግብ እየተስማማኝ አይደለም’ እያለ ሲጠይቅ ነበር። ከቤቱ ነው ምግብ የሚሄድለት ግን ምንም አይነት ምግብ ውስጡ አይረጋም፣ ይታመም ነበር።

አሁን በብዙ መከራ ባለፈው ለህክምና ፈቅደውላቸው ሄዱ። በጣም በኃይለኛው ከመቆጣት አልፎ አንጀቱ አብጦ ነበር። ያ በአፋጣኝ በሰርጀሪ ተቆርጦ መውጣት ነበረበት። ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር በቼካፕ ቀን ነው ወዲያው ‘ሰርጀሪ መሰራት አለበት’ ተብሎ የነበረው።

ግን ሰርጀሪ ለመሰራት ሁለት ቀናት ምግብ ሳይመገብ መቆዬት ነበረበት። ለሁለት ቀን ምግብ አቁሞ በሦስተኛው ቀን ሰርጀሪ ተሰራ። ሰርጀሪም አድርጎ ወዲው ተመለሰ። አሁንም ገና ክትትል ያስፈልገዋል። ለነገ ቀጠሮ አለው።

ውስጡ ያለው ነገር ሰላም መሆኑን፣ ወደ ቦታው መመለሱን ነገ ነው የምናውቀው። በአንዴ የሚታወቅ ነገር አይደለም። ምክንያቱም ቶሎ ባለመታከሙ ውስጡ በጣም ተጎድቷል።

የፍርድ ቤቱ ሁኔታ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ ምንም አይነት ፍትህ አልተገኘም። ምንም አይነት መልስም እያገኘ አይደለም። እስካሁን ‘ምርመራ ላይ ነን’ ነው የሚሉት።

ምንም ያቀረቡት ነገር የለም መመላሰስ ብቻ ነው እንጂ አፋጣኝ ፍትህ አልተገኘም። 

ቤተሰቡ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው። ቤተሰብ እሱ በመያዙ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንድንገባ ተገደናል። ምክንያቱም ሙሉ ቤተሰቡን የሚያስተዳድረው እሱ ነበር።

ልጆችና ሌሎች በሱ ስር የሚተዳደሩ ቤተሰቦች አሉት። እሱ በመታሰሩ ያ ሁሉ ተበትኗል። በጣም ችግር ውስጥ ነን። ዴሞክራት ነኝ ከሚል መንግስት ፍትህ ይጠበቃል።

እሱም እያለ ያለው ‘ፍትህ ይሰጠኝ’ ነው። ስለእውነት ነው እያወራ ያለው፣ ስለእውነት ነው እየታገለ ያለው። ቤተሰብና ልጅ በቶኖ በጣም ኃይለኛ እንግልት ላይ ነን በእውነት ”
ብለዋል።

አቶ ክርክቲያን ታደለና አቶ ዮሐንክ ቧ ያለው አዋሽ አርባ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት  ህመም ሲጀምራቸው በወቅቱ ባለመታከማቸው ለአንጀት ድርቀት በሽታ ተዳርገው ሰሞኑን ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው፣ ነገም የሀኪም ቀጠሮ እንዳላቸው ቤተሰቦቻቸው ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia