የመቐለ ከተማና አካባቢው ኤሌክትሪክ አግኝቷል !
የመቐለ ከተማ ፣ ኲዊሀ ፣ አዲጉዶም አካባቢዎች ከሳምንታት የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ በኋላ ዛሬ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አገልግሎት ማግኘታቸውን #EEP አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በስፍራው የተሰማሩ የጥገና ባለሙያዎች ለሰሩት ስራ ምስጋና አቅርበዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ሱዳን ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንድትሸጥላት ጠየቀች። ሱዳንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት ፍላጎት አሳይተዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ተናግረዋል። በቅርቡ ሱዳን አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንደምትፈልግ ማሳወቋን ተከትሎ ባለፈው ወር የተቋሙ ሠራተኞች ወደ ካርቱም አቅንተው እንደነበረና…
የሱዳን ኤሌክትሪክ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ ገቡ።
በሱዳን ኤሌክትሪክ ኩባንያ (ሱዳን ኤሌክትሪክ ትራንስሚሽን ኮርፖሬሽን) ዋና ሥራ አስፈጻሚ የቴክኒክ አማካሪ የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል በቀጣይ ስለሚኖረው የኃይል ትስስር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች ጋር ለመደራደር አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
በዋና ሥራ አስፈጻሚው የቴክኒክ አማካሪ ሚስተር አህመድ አደም ኡመር የተመራዉና 5 አባላትን ያካተተው የልዑካን ቡድን ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስትራቴጂና ኢንቨስትመንት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ተሾመ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
አቶ ወንድወሰን የልዑካን ቡድኑን በተቀበሉበት ወቅት እንደተናገሩት የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ የገባው በሁለቱ ሃገራት መካከል የኃይል ትስስሩን ለማጠናከር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ ድርድር ለማድረግ ነው፡፡
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በመገኘት ከኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ድርድር መካሄዱን አስታውሰዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚካሄደው ድርድር ከዚህ በፊት በነበሩ ድርድሮች የተነሱ ጉዳዮች እልባት እንዲያገኙና በቀጣይ ስለሚኖረው የአሰራር ሁኔታ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል፡፡
ድርድሩ የሱዳን የኤሌክትሪክ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ባቀረበው ጥያቄ ላይ እንዲሁም ተጨማሪ ኃይል ለማቅረብ መከናወን ባለበት የመስመር ዝርጋታ እና ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ እንደሚሆን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
ድርድሩ ከጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
#EEP
@tikvahethiopia

#SafaricomEthiopia #EEP
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከሳፋሪኮም - ኢትዮጵያ ጋር የኦፕቲካል ፋይበር ኪራይ ሥምምነት ተፈራርሟል።
ስምምነቱ በመጀመሪያ ምዕራፍ 4097 ኪ.ሜ፣ በ2ኛው ምዕራፍ 2078 ኪ.ሜ እንዲሁም በ3ኛው ምዕራፍ 2904 ኪ.ሜ የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ኪራይን ያጠቃልላል፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የሳፋሪኮም -ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንዋር ሶውሳ ናቸው፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

#Update
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝቷል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ላለፉት 17 ቀናት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ እንደነበር ገልጿል።
ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገቡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይም ተደጋጋሚ ስርቆት ስለሚፈፀም የተቋረጠውን ኃይል መልሶ የማገናኘት ሥራውን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር አስታውቋል።
ለቀናት መስመሩን ለማገናኘት ጥረት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ተሳክቷል።
ከቀኑ 9:05 ሰዓት ጀምሮ አካባቢዎቹ ኤሌክትሪክ አግኝተዋል።
" በአንድ አካባቢ የሚፈፀም የኃይል መሰረተ ልማት ስርቆት ተፅዕኖው ሰፊ ነው " ያለው መ/ቤቱ " በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኃይል መቋረጥ በግልፅ የታየው ይኸው ነው " ብሏል።
በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ህብረተሰቡ እና የሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላት ለመሰረተ ልማቱ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

" በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።
የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።
#EEP
@tikvahethiopia
ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።
የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።
#EEP
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል
በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።
ማዕከሉ እንዳስታወቀው ፦
- በአዲስ አበባ 85 በመቶ በሚሆነው በአብዛኛዎቹ አካባቢ ፣
- በአዳማ፣
- በሀዋሳ፣
- በጅማ፣
- በአርባምንጭ፣
- በወላይታ ሶዶ፣
- በሻሸመኔ፣
- በወልቂጤ፣
- በመቐለ፣
- በዓድዋ፣
- በአላማጣ፣
- በዲላ፣
- በቦንጋ፣
- በሚዛን እና ሀገረማርያም ኃይል ተመልሶ ተገናኝቷል።
እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን የገለፀው ማዕከሉ በቀሪዎቹ አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ርብርቡ መቀጠሉን ገልጿል።
የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አለመፈታቱ የተገለጸ ሲሆን ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

" እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ። ማዕከሉ እንዳስታወቀው ፦ - በአዲስ አበባ 85 በመቶ በሚሆነው በአብዛኛዎቹ አካባቢ ፣ - በአዳማ፣ - በሀዋሳ፣ - በጅማ፣ - በአርባምንጭ፣…
#Update
ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ ተከስቶ የነበረው የኃይል መቋረጥ ወደነበረበት መመለሱን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታውቋል። #EEP