#ጽዮንማርያም
የ2017 ዓ/ም የአክሱም ህዳር ፅዮን ሃይማኖታዊ በዓል ከነገ በስቲያ ህዳር 21 ይከበራል።
የትግራይ ባህልና ቱሪዝምና ቢሮ ፤ " በቅድስት የአክሱም ከተማ እና በሌሎችም የክልሉ አከባቢዎች የህዳር ፅዮን በዓል የሚያከበሩ ገዳማት ቱሪዝምን በማነቃቃት የበኩላቸው አስተዋፅኦ አላቸው " ብሏል።
ቢሮው ፤ ህዳር 21 የአክሱም ፅዮን በዓልን ለሚያከብሩ ሁሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ህዝቡ በዓሉ ለአገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች ያለው አስተዋፅኦ በመገንዘብ በየአከባቢው የሚገኙ ቅርሶች በመንከባከብና ትውፊታዊ መልኩ በጠበቀ መልኩ በዓሉ እንዲያከብር ጥሪ አስተለልፏል።
በርካታ ምእመናን ቅዳሜ ለሚከበረው በዓል ወደ አክሱም እየተጓዙ ይገኛሉ።
ለበዓሉ ሁሉም አይነት ዝግጅቶች መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ወደ ስፍራው እየተጓዘ ሲሆን በከተማው ከደረሰ በኃላ ያለውን የበዓል መረጃዎችን ያካፍላል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
በሶማሊያ ያለው ከፍተኛ ውጥረት ወዴት ያመራ ይሆን ? ⚫ የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ መንግሥት አሕመድ ማዴቦ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። የጁባላንድ መንግሥት ደግሞ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አውጥቷል። በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ ራስገዝ አስተዳደር መሪዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ሰንበትበት ብሏል። ምክንያት ? በአገሪቱ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየውን ክልላዊ…
#Update
የጁባላንድ መንግሥት ከሶማሊያ ፌዴራሉ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ይፋ አደረገ።
የጁባላንድ ካቢኔ ስብሰባ ካደረገ በኃላ ይፋ እንዳደረገው " ሙሉ በሙሉና በይፋ ከሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን የስራም ሆነ ማንኛውንም ግንኙነት " አቋርጧል።
የጁባላድ መንግሥት ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድን ፦
- ኃይላቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም
- የእርስ በእርስ ጦርነት በማነሳሳት
- ሰራዊትን በማውደም
- በሙስና ... ከሷል።
ሕገመንግስቱን በማጣስ ወንጅሎም " በፌዴራል መንግሥት የተደረጉ የሕገመንግስት ማሻሻያዎችን አንቀበልም " ሲል አሳውቋል።
ቀደም ሲል የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ መንግሥት በጁባላንድ ፕሬዝዳንት አሕመድ ማዴቦ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።
የጁባላንድ መንግሥት በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ እንዲታሰሩ የእስር ትዕዛዝ በማውጣት አፀፋውን መልሷል።
በፌዴራል መንግሥቱ እና በጁባላንድ መንግሥት መካከል ውጥረቱ መባባሱ ተሰምቷል።
NB. ባለፈው አመት የፑንትላንድ መንግሥት ከማዕከላዊው የሶማሊያ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

#DStvEthiopia
ዲኤስቲቪ ሁሉንም የእግር ኳስ ውድድሮችን ባንድ ላይ ማግኘት የሚያስችል አዲስ የሜዳ ስፖርት ፓኬጅ አቀረበ
ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ለተመልካቾች በማቅረብ የሚታወቀው ዲኤስቲቭ አዲስ የስፖርት ፓኬጅ አቅርቧል።
አዲሱ የዲኤስቲቪ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅ በሜዳ እና በሜዳ ፕላስ ፓኬጆች መካከል አንዱ ተጨማሪ ፓኬጅ በመሆን ይፋ ሆኗል።
የእግር-ኳስ አፍቃሪያን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ የጣሊያን ሴሪ ኤ እና ላ ሊጋን ጨምሮ ሌሎች የእግርኳስ ይዘቶችን እንዲሁም አለም አቅፍ ተከታታይ ፊልሞችን እና ሃገርኛ ድራማዎችን እና መዝናኛዎችን በአቦል ቲቪ እና በማዲ አቦል ቻናሎች- ሁሉንም በአንድ ላይ በሜዳ ስፖርት ፓኬጅ መቅረቡ ተገልጿል።
ሁሉንም የእግር ኳስ ውድድሮችን ባንድ ላይ እንዲያገኙ ተደርጎ የተዘጋጀው ይህ የሜዳ ፓኬጅ በወር በ1 ሺህ 699 ብር ያስከፍላል ተብሏል።
አዲሱ የዲኤስቲቪ ፓኬጅ - ሜዳ ስፖርት ከሕዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለደንበኞች ቀርቧል።

#Update የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ወንጀል ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ ገፁ በሰጠው ማብራርያ ፤ " ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 :00 ሰዓት አካባቢ ከአክሱም ወደ መቐለ ከተማ በመኪና በመጓዝ ላይ የነበሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ የሚያጣራ ቡድን ተቋቁመዋል…
#Tigray
በቅርቡ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው የተናገሩት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ በአዲስ አስተዳዳሪ ተተኩ።
ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ፤ ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ በተባሉ አዲስ አስተዳዳሪ ነው የተተኩት።
አዲሱ የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ህዳር 18 / 2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ መተካታቸው ለማወቅ ተችላል።
በአቶ ሰለሞን መዓሾ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ የትግራይ ክልል ፓሊስ እያጣራሁት ነው ማለቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#ጥቆማ
እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኘውን የ " The Earthshot Prize 2025 " ኢትዮጵያውያን እንዲወዳደሩ ጥሪ ቀረበ።
በእንግሊዝ ልዑል ዊሊያምና ሮያል ፋውንዴሽን በፈረንጆቹ 2020 የተቋቋመውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአካባቢና አየር ብክለት የፀዳ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያበረክትና ለተፈጥሮ ተስማሚ የሆነ ስራ እየሰሩ ያሉ ተቋማትን ፣ የቢዝነስ ፈጠራ ባለሙያዎችን (ኢንተርፕረነሮችን) ወይም ግለሰቦችን የሚሸልመው " The Earthshot Prize 2025 " የዘንድሮ እጩ ተወዳዳሪዎችን መቀበል ጀምሯል።
በአፍሪካ የውድድሩ ዋና አጋር መልቲቾይስ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
በ5 የተለያዩ ምድቦች የሚካሄደው ይህ ዓመታዊ ሽልማት ላይ በተለይ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑና ተፈጥሮን የማይበክሉ ቢዝነሶችን የሚያንቀሳቅሱ ኢትዮጵያውያን መሳተፍ ይችላኩ።
ውድድሩ እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኝ ነው ተብሏል።
ፕሮጀክቶቻቸውን ለማስፋፋትና እየተባባሰ ለመጣው የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ እንዲያበረክቱም ያግዛል።
መልቲቾይስ አፍሪካ ፤ በደቡብ አፍሪካ በተከናወነው የ2024 ውድድር ከጋና " ግሪን አፍሪካ ዩዝ ኦርጋናዜሽን " እንዲሁም ከኬንያ " ኪፕ ኢት ኩል" የተሰኙ የአረንጓዴ ጉዳይ አቀንቃኞችና የሥራ ፈጣሪዎች አሸናፊ እንደሆኑ አስታውሷል።
ለዚህ ዓመቱ ሽልማት ማመልከት የሚቻለው እስከ ፈረንጆቹ ዲሴምበር 04 / 2024 ሲሆን ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እና ተቋማት በ https://www.multichoice.com/earthshot-nomination.php#prId=324466 እንዲያመለክቱ ጥሪ አቅርቧል።
#TikvahEthiopia
Via @TikvahethMagazine

" ምን ያልተጎዳ አለ፣ አገሩ በሙሉ ነው የተጎዳው " - ሰብላቸው የተጎዳባቸው አርሶ አደር
ሰሞኑን በአማራ ክልል ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አቅራቢያ የጣለው ከባድ ዝናብ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን አርሶ አደሮች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ 700 የሚጠጉ አርሶ አደሮች ሰብላቸው ወድሟል።
ዝናቡ በደረሱ የስንዴ ፣ የቦቆሎ ፣ የገብስና ሌሎች አዝርዕቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
ለእንሳቱ የሚሆን ቀለብ እንኳ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ወድሟል።
እንስሳቱም ለርሀብ መጋለጣቸውን አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።
ከ600 በላይ አባዎራዎችም ለችግር ተዳርገዋል።
ቃላቸውን የሰጡ አርሶ አደሮች ሕዳር 14 ቀን 8 ሰዓት ጀምሮ ከ30 ደቂቃ በረዶ ቀላቅሎ በዘነበው ከባድ ዝናብ " በገብስ፣ ባቄላና ጤፍ ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል " ብለዋል።
ከዛሬ ነገ የደረሰውን ሰብል በደቦ ለመሰብሰብ እየተዘጋጁ በነበረበት ወቅት ነው ድንገት የዘነበው ዝናብ ውድመት ያደረሰው።
በዝናቡ ሰብላቸው ከተጎዳባቸው አርሶአደሮች መካከል አቶ ቢራራ ሁነኛው "... የደረሰ ባቄላና ገብስ ነበረኝ፣ በጣም ጉዳት ደርሶበታል፣ ምን ያልተጎዳ አለ፣ አገሩ በሙሉ ነው የተጎዳው " ብለዋል።
በጉዳቱ 10 ኩንታል ምርት የወደመባቸው ሌላው አርሶአደር ዝናቡ ባልተጠበቀ መንገድ ጉዳት አድርሷል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
ፎቶ ፦ ኤኤምሲ

Photo
ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት።
አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ነው የሾመው።
ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል።
" ጊዜያዊ አስታዳደሩ በተቋቋመበት ህግ እና አሰራር መሰረት ወደ ስራ ገብቻለሁ አሁን ላይ በፅ/ቤት ስራ ርክክብ እያደረኩ ነው " ብለዋል።
ዛሬ ደግሞ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ዓዲግራት ከተማ በተካሄደ የም/ቤት ጉባኤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩትን ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
አቶ ረዳኢ ሹመቱን አረጋግጠዋል።
" TPLF ተወዳድሮ በተመረጠበት ትግራይ እስካሁን ያለው የTPLF ም/ቤት አባላት ናቸው ፤ እኔም እንደ TPLF አንድ አካል ተወካይ ሆኜ ነው የቀረብኩት " ሲሉ ሹመቱ በም/ቤት እንደፀደቀላቸው ተናግረዋል።
አቶ ዓለም ስለ ረዳኢ ሹመት የማውቀው የለም ብለዋል።
" በምክር ቤት ስለተደረገው ሹመት በማህበራዊ መገናኛ ነው ያየሁት በይፋ በመንግሥት መዋቅር አልሰማሁም " ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ረዳዒ ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ሹመት ምንም ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።
" ሹመት እንደተሰጠው ሰምቻለሁ ያው ትግራይም ኢትዮጵያም ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አካሄዳችን የአንድ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አስተዳደር የራሱ ምክር ቤት አለው ምክር ቤቱ ነው ከንቲባም ፣ የወረዳ አስታዳዳሪም ፣ ካቢኔም የሚያፀድቀው በዚህ ም/ቤት ያላለፈው ከንቲባ ወይም አስተዳዳሪ የመሆን እድል የለውም " ብለዋል።
" እንደ ድርጅት ከምክር ቤት ውጭ ከመጣ ተቀባይነት አለው ብዬ አላምንም እንደ ህወሓት አቋማችን ይሄው ነው " ያሉት ረዳኢ ከምክር ቤት ውጭ ማንም ሰው ደብዳቤ እየፃፈ የሚሾመው ተቀባይነት የለም ሲሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሰጠውን ሹመት አጣጥለዋል።
ትላንት በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ የወረዳና የከተማ ም/ ቤቶች አብላጫው መቀመጫ በህወሓት በመያዙ ከባለፈው ጉባኤ በኃላ የአመራር ማስተካከያ እያደረግን ነው ብለው ነበር።
የጊዛያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመመራው ቡድን ጊዜያዊ አስታዳደሩን ስራ አላሰራ እንዳለና የወረዳና የከተሞች ም/ቤቶችን በመጠቀም በመንግሥት የተመደቡ አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ መሆኑን ይህም መፈንቅለ መንግሥት እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።
የዚህ መረጃ ባለቤት ቪኦኤ ሬድዮ ነው።

ጠብታ አምቡላንስ በድንገተኛ አደጋ ያሉ ጉዳቶችን ለመቀነስ እንዲሁም በዘርፉ የነበረውን የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት ለመቅረፍ በነፃ የትምህርት ዕድል በኢመርጀንሲ ሜዲካል ሰርቪስ ደረጃ 4 እያሰለጠነ ይገኛል።
በዚህም ሁለት ባቾችን ያስመረቀ ሲሆን የ3ኛ ዙር ሰልጣኞችን በቅርብ ቀናት ውስጥ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
አሁንም ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በድንገተኛ በኢመርጀንሲ ሜዲካል ሰርቪስ ደረጃ 4 ሰልጣኞችን በመቀበል ለ20 ወራት ያለምንም ክፍያ ለማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
🕒 የመመዝገቢያ ጊዜ እስከ ታህሳስ 5/2017 ይቆያል።
የምዝገባ ቦታ ፡ ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ
አድራሻ ፡ የካ ክፍል ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 207 (22 አካባቢ ጆቫኒ ሆቴል ጀርባ ገባ ብሎ
ያለው ውስን ቦታ በመሆኑ ቅድሚያ መመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ
ለበለጠ መረጃ 0943302400/ 0923514151 /0912419354/ 0910855115 ላይ ይደውሉ!
https://www.tebitaambulance.com
ሕይወት ለማዳን 8035 ይደውሉ

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሕብረት ባንክ ቤተሰብ ይሁኑ!
ሕብረት ባንክ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና ወቅታዊ መረጃዎች በቀላሉ ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም: https://t.iss.one/HibretBanket
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን: https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/hibretbank/
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/@hibretbanket
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://t.iss.one/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
#Hibretbank #getconnected #digitalcommunity #subscribe