TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ወጣቶቻችን😥

" ከአንድ ወረዳ ብቻ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው 200 ያህሉ ለህልፈት ተዳርገዋል " - የእገላ ወረዳ አስተዳደር

እገላ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ወረዳዎች አንድዋ ስትሆን የኤርትራዋ ፆሮና ጎረቤት ናት።

ከትግራዩ ጦርነቱ በፊት የወረዳዋ ዋና ከተማ በሆነችው ገርሁስርናይ በቀን በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚተላለፉባት ነበረች።

ከጦርነቱ በኋላ በእገላ ወረዳ በተለይ በገርሁስርናይ ከተማ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል።

ወረዳዋ በተለይ ከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ ወድመዋል።

አሁንም ድረስ ወረዳዋ በኤትርራ ድንበር የምትገኝ በመሆንዋ የተሟላ ፀጥታ አላት ለማለት ያስቸግራል ይላሉ የአከባቢው ነዋሪዎች።

በወረዳዋ የሚታየው ህገ-ወጥ ስደት እጅግ አስደንጋጭና አስፈሪ መሆኑ የአደጋው ሰለባዎች እና የመንግስት አካላት ጭምር ይናገራሉ።

አቶ ዘርኢሰናይ መንግስቱ የተባሉ የገርሁስርናይ ከተማ ነዋሪ ለትግራይ የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ሬድዮ ባጋሩት መረጃ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሹፌር በመሆን ሲተዳደር የነበረው የ22 ወጣት ልጃቸው ህገ-ወጥ ስደት ተነጥቀዋል።

ከእገላ ወረዳ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው 2016 ዓ/ም የመጨረሻ ወራት ብቻ 192 ሴቶች የሚገኙባቸው ከ 2 ሺህ በላይ  ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው ከ1300 በላይ በስደት በተጓዙበት አገር ፓሊስ በአጭር ጊዜ ተይዘው ሲመለሱ 200 የሚያህሉ ግን ለህልፈት ተዳርገዋል።

የወረዳው ከፍተኛ አመራር ፅጌ ተ/ማርያም እንዳሉት፤ በአከባቢው የሚታየው ህገ-ወጥ የስደት ፍልሰት እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ነው።

ወረዳው ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ይህ ነው የሚባል በጀት ያለው ባይሆንም የወጣቶች ስደት ለማስቀረት ያለመ የመስሪያ ቦታ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተያዘው የበጀት ዓመት የህገ-ወጥ ስደት ፍልሰት በከፍተኛ ቁጥር ለመቀነስ ወረዳው አቅዶ እየሰራ ነው።

ይሁን እንጂ ጦርነት ወለዱ የበጀት እጥረት ለተያዘው እቅድ መሳካት ሳንካ ሊሆን ስለሚችል በወጣቶች አቅም ግንባታ እና ህገ-ወጥ ስደት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲያግዙዋቸው ሃላፊው ጥሪ አቅርባዋል።

#Ethiopia #TigrayRegion

@tikvahethiopia