TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray #DDR

የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ በትግራይ ውስጥ ያሉ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት የተገመገመበት እንደሆነ ተገልጿል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው እስካሁን የተሰሩ ስራዎች መገምገማቸውን እና በቀጣይም ስለሚሰሩ ስራዎች ውይይት መደረጉን ከዚህ በተጨማሪ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ እና መልሶ የማቋቋም ስራዎች ላይ ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት ለመስራት መስማማታቸውን አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ' በኃይል ይዣለሁ ፣ ይዣለሁ ማለቱ ፍጹም ሰላም አያመጣም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ፥ " በወረራ " ተይዘዋል ያሏቸውን የትግራይ ክልል ግዛቶችን በሰላም ስምምነቱ መሰረት ነጻ እንዲወጡ እና የአካባቢዎቹ ሰላምና ደህንነት ተረጋግጦ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ኃላፊነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት…
" ስጋት ፈጥሮብናል " - ኤምባሲዎቹ

ሰሞነኛውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኙት ፦
- የካናዳ፣
- የፈረንሳይ፣
- የጀርመን፣
- የጣሊያን፣
- የጃፓን፣
- የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ኤምባሲዎች የጋራ አጭር መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ " #አወዛጋቢ " በሆኑት አካባቢዎች ከሰሞኑን የተፈጠረው ግጭት " ስጋት ፈጥሮብናል " ብለዋል።

ሁሉም ወገኖች የታጣቂ ኃይሎች ትጥቅ ማስፈታት ፣ ብተና እና መልሶ ማቋቋም /#DDR / እንዲሁም ተፈናቃዮችን #በሰላም ወደ ነበሩበት መመለስ ላይ አበክረው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

" ውጥረቱ እንዲረግብ እና #ሰላማዊ_ሰዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን " ብለዋል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የተወሳሰቡ የፖለቲካና የጸጥታ ቀውሶችን ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት ማድረግ ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
#DDR #Tigray

የእንግሊዝ (UK) መንግስት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም (DDR) የሚያግዝ የ16 ነጥብ 9 ሚሊዮን ፓወንድ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታዉቋል፡፡

የድጋፍ ማእቀፉን ያሳወቁት በብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሎርድ ኮሊንስ የተመራው ልዑክ በመቐለ በመገኘት የብሄራዊ ተሀድሶ ቦርድ አባል ሌ/ጀ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ እና ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንዲሁም የዩኤንዲፒ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የቀድሞ ተዋጊዎች ዲሞቢላይዜሽን ማእከል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

#UKinEthiopia

@tikvahethiopia