TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba
" በቦታው ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ምክረ ሃሳብ ቀርቧል። ያቀረብነው ምክረ ሃሳብ ቦታው እንደ አዲስ በመልሶ ማልማት እንዲለማ ነው " - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በትላንትናው ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ የእሳት አደጋ ያጋጠመው በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ገበያ የሚገኝ አካባቢ፤ " በመልሶ ማልማት እንዲለማ " ምክረ ሃሳብ ቀረበ።
ምክረ ሃሳቡን ያቀረበው የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።
ትላንት እሁድ ህዳር 8/2017 እኩለ ቀን ገደማ የእሳት አደጋ የደረሰበት የመርካቶ ገበያ ስፍራ፤ በተለምዶ " ድንች ተራ " የሚል ስያሜ ያለው ነው።
ስፍራው ከሁለት ሳምንት በፊት በተመሳሳይ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ከነበረው " ነባር የገበያ ማዕከል " በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።
የእሁዱ ቃጠሎ የደረሰበት ስፍራ፤ " በነባር የገበያ ማዕከል " ላይ የሚነግዱ ነጋዴዎች ንብረቶቻቸውን የሚያስቀምጡበት መጋዘን እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች " ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጽ ተናግረዋል።
የእሳት አደጋው " ጌሾ ግቢ " ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከሚገኘው መጋዘን በተጨማሪ በአቅራቢያው የሚገኙ መደብሮች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ውድመት አድርሷል።
ትላንት በአደጋው ወቅት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ነጋዴዎች የእሳት ቃጠሎው ወደ ሌሎች የገበያ ማዕከሎች እና መደብሮች እንዳይዛመት በስጋት ሲያስተውሉ ነበር።
የተወሰኑ የአካባቢው ወጣቶች እና ከእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ጋር በመሆን ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማድረግ ርብርብ ሲያደርጉ ነበር።
በአንድ ሰዓት ተኩል ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋለውን የእሳት አደጋ ለመከላከል፤ ሰባት የውሃ ቦቴዎች እና 18 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጽ ገልጸዋል።
ከእነዚህ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ የኮሚሽኑ እና የቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንሶች፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ወደ ህክምና ተቋማት በመውሰድ ተሳትፈዋል።
በትላንቱ የእሳት አደጋ ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እና ሁለት የኮሚሽኑ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በዚሁ አካባቢ በደረሰው ተመሳሳይ አደጋ፤ ዘጠኝ ሰዎች መጎዳታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁ አይዘነጋም።
የትላንቱ አደጋ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች አካባቢውን በገመድ በማጠር ጥበቃ ሲያደርጉ ነበር።
ክልከላውን አልፈው ለመግባት ሲሞክሩ የነበሩ ነዋሪዎች እና ነጋዴዎችን፤ የፖሊስ አባላቱ ወደ ቦታው እንዳይጠጉ በኃይል ሲከላከሉም ነበር።
ፖሊሶች እና የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ከመድረሳቸው በፊት ግን የተወሰኑ ነጋዴዎች ንብረቶቻቸውን ከቃጠሎ ማትረፍ ችለዋል።
በዚህም ምክንያት በአደጋው " የከፋ ጉዳት " አለመድረሱን አቶ ንጋቱ አስረድተዋል።
ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላም፤ ነጋዴዎች ንብረታቸውንን ከአካባቢው ለማራቅ ሲጥሩ ታይተዋል።
ነጋዴዎች፤ አካባቢው በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ እያጋጠመው በመሆኑ ምክንያት " መንግስት ከስፍራው ያነሳናል " የሚል ከፍተኛ ስጋት አላቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አካባቢውን " ለአደጋ ተጋላጭ " በሚል አስቀድሞ መለየቱን የገለጹት አቶ ንጋቱ፤ በቦታው ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን አስረድተዋል።
" ያቀረብነው ምክረ ሃሳብ ቦታው እንደ አዲስ በመልሶ ማልማት ወይም የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ቧሟላ፣ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ መገንባት ይኖርበታል ነው። ምክረ ሃሳቡን ተቀብሎ በመልሶ ማልማት ለመስራት የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉ መረጃው አለን። በሂደት ላይ ነው ያለው። ታምኖበታል። ምን አልባትም በዚህ አመት ሊጀመር ይችላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።
#AddisAbaba #Merkato #EthiopiaInsider
@tikvahethiopia

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አፈጸሚ አቶ ሰዒድ አሊ ያለመከሰስ መብት ተነሳ።
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ነው።
በዚህም ጉባኤ የምክር ቤቱ አባል የሆኑትን የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰዒድ ዓሊን ያለመከሰስ መብትን ተነስቷል።
በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት ነው ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው።
ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተደረገው ከሙስና ጋር በተያያዘ ነው።
ምክር ቤቱ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ መወሰኑ ተሰምቷል።

ዛሬ ያለመከከስ መብታቸው የተነሳው የልደታ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአ/አ ም/ቤት አባል ሰዒድ አሊ በምንድነው የተጠረጠሩት ?
ዛሬ የአዲስ አበባ ም/ቤት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ሰዒድ አሊን ያለመከከስ መብት አንስቷል።
ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው በሙስና ተጠርጥረው እንደሆነ በም/ቤቱ የሰላም ፣ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል።
ኮሚቴው ምን አለ ?
" ከሜክሲኮ እስከ ቄራ ባለው የኮሪደር ስራ ያልተካተቱ እና በመንግሥት ይፈርሳሉ ተብለው ያልተያዙ የመንግሥት ቤቶችን ከባለሃብት እና ከሰራተኞች ጋር በመመሳጠር ግምታቸው ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት እንዲሰጥ አድርገዋል።
የፈረሱት የመንግሥት ቤቶች ግለሰቦች ተከራይተውት የነበረ ነው።
እነዚህን ቤቶች እንዲፈርሱ አስደርገው ይዞታውን ከቤቶቹ አጠገብ ለተሰራው " ዋይልድ አፓርትመንት " ለተባለ ህንጻ ባለቤት ምቹ በማድረግ ግንባታ እንዲገነባና የግሉ እንዲያደርገው ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል።
አጠቃላይ 6 መኖሪያ ቤቶች እና 1 ንግድ ቤት ፦
- ግለሰቦች እየኖሩበትና ንግድ እየተከናወነ ባለበት፤
- ካቢኔው ይፍረሱ ብሎ ባልወሠነበት
- ፕላን፣ ፎርማት እና የካቢኔ ውሳኔ ባልተያዘበት በ503 ካ/ሜ ላይ ያረፉትን ቤቶች እንዲፈርሱ ሰራተኞችን ሰብስበው በማስወሰንና ትዕዛዝ በመስጠት ፤ ቤቶቹ ያሉበት ቦታ በአካል ጭምር በመሄድ እንዲፈርስ መመሪያና ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
የመንግሥት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በኪራይ ይኖሩ ለነበሩት ግለሰቦች አጠቃላይ 3,383,202 ብር ከ77 ሳንቲም የሆኑ 6 የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እንዲሰጣቸው አድርገዋል።
ይዞታውን ሀጂ በገን ኸይሩ ነጋሽ ለተባሉ በአካባቢው አፓርትመንት ላላቸው ግለሰብ እንዲሰጥና ግንባታ እንዲገነባበት አድርገዋል።
ተጠርጣሪው ለዚህ ስራ ጉቦ መቀበሉ ማስረጃ አለን ብሏል።
በባለቤታቸው ስም ከባለሃብቱና ከድርጅቱ 6 ሚሊዮን ብር ጉቦ ተቀብለዋል። ይህን ብር ከሌላ ግለሰብ ካተላለፈው 8 ሚሊዮን ብር ጋር በመቀላቀል በባንክ ብድር ለገዙት 30,000,000 ብር ለሚያወጣ ቤት 14,000,000 ብር ለቤቱ ግዥ ብድር ክፍያ ከፍለዋል ፤ በዚህም የሙስናና ህገወጥ ገንዘቡን ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል መፈጸም ምርመራ እየታጣራ ይገኛል " ብሏል።

" የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት ስትቀጥሩ በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን ይሁን " - ፖሊስ
በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱ የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ነው፡፡
ግለሰቧ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በ3ኛው ቀን ቆይታዋ ነው ዝርፊያውን የፈጸመችው።
የግል ተበዳይ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን ሰርቃ በመሰወሯ የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡
ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት ለ3 ወራት ተከራይታ በነበረበት ቤት ተደብቃ በክትትል የፖሊስ አባላት ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት፣ የተለያዩ የሴትና የወንድ ጫማዎች፣ 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ፣ የተለያዩ የወርቅና ልዩ ልዩ ጌጣጌጦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ ገልጿል።
በ2 የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያዎች እንደተገኘባትም ፖሊስ አመልክቷል።
የግል ተበዳይ ተጠርጣሪዋን ለስራ ሲቀጥሯት ያቀረበችው የተያዥ ፎርም የራሷን ፎቶ በትክክል እንዳይለይ አድርጋ የለጠፈች ሲሆን የግል ተበዳይ ይህን ሳያረጋግጡ በእምነት የቀጠሯት መሆኑን ገልፀዋል።
ፖሊስ ፥ ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት መቅጠሩ ተገቢ ቢሆንም በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን መቅጠር እንደሚገባ አሳስቧል።
ውድ የሆኑ ንብረቶችን እንዲሁም ገንዘቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ በማስቀመጥ በተገቢው ሊቆጣጠሩና ንብረታቸውን ከስርቆት ወንጀል ሊታደጉ እንደሚገባም አሳስቧል።
NB. በዚህ የፖሊስ መረጃ ላይ እንዴት አንድ ሰው ቤት ውስጥ ይሄ ሁሉ የአሜሪካ ዶላር በጥሬው ሊቀመጥ እንደቻለ፣ የተገኘው የተጠርጣሪዋ መታወቂያ ከየት እና እንዴት እንደወጣ የተብራራ ነገር የለም።
መረጃውን የተመለከቱ በርካቶች የገለሰቧ መያዝ ትክክል ሆኖ ሳለ እንዴት ይሄ ሁሉ ዶላር ግለሰብ ቤት ተቀምጦ ተገኘ፣ መታወቂያውን የሰጣት አካላስ ማነው ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊስ በቀጣይ ስለ ጉዳዩ የሚሰጠው ማብራሪያ ካለ እናቀርባለን።

“ አያት 49 ግሎባል ባንክ አካባቢ የጥበቃ ሠራተኛው ሲገደል ጓደኛው ደግሞ ቆስሏል ” - የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል
“ የድርጊቱ ምርመራው ገና አላለቀም ” - የፓሊስ መረጃ ክፍል
በለሚኩራ ክ/ከተማ አያት 49 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የግሎባል ባንክ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተመትቶ መገደሉን በስፍራው ያሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል።
በጥይት የተመታው ጥበቃ ሠራተኛ ጓደኛ እንደቆሰለ አስረድተው፣ ገዳዩና አቁሳዩ በሌላ ብራንች የሚሰራ የጥበቃ ሠራተኛ ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል።
“ 40/60 ሳይት 3 አያት 49 ግሎባል ባንክ ዘበኛው አሁን በጥይት ተመትቶ ሞተ። ግድያው የተፈጸመው ጠዋት አንድ ሰዓት አካባቢ ነው ” ሲሉ አንዱ የስፍራው ነዋሪ ገልጸዋል።
ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ገደማ እንደሆነ፣ የግድያውን ምክንያት ግን በግልጽ እንዳላወቁ፣ የተመታው የባንክ የጥበቃ ሠራተኛ መሆኑን ነግረውናል።
የወንጀል ድርጊቱን ሰምተው እንደሁ የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ ጉዳዩን እንዳልሰሙ፣ ተፈጽሞ ከሆነ ደግሞ መሰማቱ እንደማይቀር ገልጸዋል።
ኮማንደሩ፣ ጉዳዩን ለማጣራት የፓሊስ መረጃ ክፍል እንዲጠየቅ ያመላከቱ ሲሆን፣ ስለጉዳዩ የጠየቅነው የፓሊስ መረጃ ክፍል ደግሞ ጉዳዩን ካጣሩ በኋላ፣ “ ምርመራው አላለቀም ትንሽ ይጠብቁ አልጨረሱም ገና ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
ድርጊቱን ፈጻሚው አካል አልተያዘም እንዴ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፣ “ የድርጊቱ ምርመራው ገና አላለቀም ” ብለው ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA