TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiotelecom

🎉 ጥሪ ማሳመሪያ ዳግም በሽልማት ተመልሷል!!

ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎችን እንደገዙ ከ 645 ለሚደርስዎት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ!

📺 ስማርት ቴሌቪዥኖች
💻 ላፕቶፖች
📱 የ5ጂ ስማርት ስልኮችና ሳምሰንግ ታብሌቶች
🎁 እንዲሁም በርካታ የሞባይል ጥቅሎችን በሽልማት ያግኙ!

ለመመዝገብ 822 ወይም *822# ይደውሉ አልያም https://www.crbt.et ይጎብኙ!

🗓 እስከ ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም ብቻ!

#CRBT #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ፥ " ለ20 ዓመታት ቤት ይደርሰናል ብለን ስንጠብቅ ከሰሞኑን የሰማነው ነገር አሳዝኖናል ፤ ፍትህ ተጓድሎብናል መፍትሄ እንፈልጋለን ፤ በቤት ኪራይ ተሰቃየን ፤ የቤት ችግር ኑሯችንን ፈተና ላይ ጥሎታል " ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ትላንት ምሽት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ አስተዳደሩ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በኩል ማብራሪያ ሰጥቷል።

ኮርፖሬሽኑ ምን አለ ?

" ብቁና ንቁ የነበሩ የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል " ብሏል።

" በ1997 ዓ/ም የቤት ባለቤት ለመሆን ተመዝግበው የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎች በ2005 ዓ.ም በተካሄደው ዳግም ምዝገባ ወቅት ' ነባር ' የሚል መለያ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን ዳግም ከተመዘገቡና ውላቸውን ካደሱ ጊዜ ጀምሮ ሳያቋርጡ ሲቆጥቡ የነበሩ ናቸው " ሲል ገልጿል።  

" እነዚህ ተመዝጋቢዎች ቀደም ብለው የተመዘገቡ እንደመሆናቸው መጠን በ20/80 የቤት ልማት መርሃ ግብር ተገንብተው ለእጣ ከሚተላለፉት ቤቶች ውስጥ የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በወጣው መመርያ ቁጥር 3/2011 መሰረት በነበሩት ዙሮች ቅድሚያ እየተሰጣቸው ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል " ሲል አሳውቋል።

" በ2005 ዳግም ምዝገባ ያደረጉ ከ140 ሺህ በላይ ተመዝጋቢዎች ሳያቆራርጡ እስከ እጣ ማውጫ ቀን ድረስ እየቆጠቡ ለነበሩት እስከ 13ኛ ዙር በነበረው የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ ሲሰተናገዱ ቆይተዋል " ብሏል።

" ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለ14ኛ ዙር በተላለፉት የ20/80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ላይም የ1997 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ነው የተስተናገዱት " ሲል አብራርቷል።

" በ14ኛ ዙር እጣ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ንቁና ብቁ የነበሩ ከ43 ሺህ ያልበለጡ ቆጣቢዎች ቅድሚያ በመስጠት ሙሉ በሙሉ እንዲሰተናገዱ ተደርጓል " ነው ያለው።

" በእጣ ማውጫ ጊዜ በመረጃ ቋት ውስጥ የቀሩት የ1997 ተመዝጋቢዎች በጊዜው ንቁና ብቁ ያልነበሩ ናቸው "ብሏል።

" እነዚህና ሌሎች ቤት ፈላጊዎች በከተማ አስተዳደሩ እየተተገበሩ በሚገኙ የተለያዩ የቤት የልማት አማራጮች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ " ሲልም አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ፥ " በአሁኑ ወቅት በከተማዋ እየተካሄዱ በሚገኙ የልማት ስራዎች ምክንያት ከመኖርያ አካባቢያቸው ለሚነሱ የልማት ተነሽዎች በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የወጣው በጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ማስተላለፍ መመርያ ቁጥር 3/2011 አንቀጽ 23 በተገለጸው መሰረት በከተማ መልሶ ማልማት ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት ለመመደብ በተቀመጠው አሰራር መሰረት እየተስተናገዱ ናቸው " ብሏል።

ኤጀንሲው " በልማት ምክንያት የሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት የሚሰጣቸው ከላይ በተጠቀሰው መመርያ ላይ በሰፈረው መሰረት በከተማ አስተዳደሩ ከሚገነቡ የጋራ መኖርያ ቤቶች ውስጥ ለልማት ተነሺ በሚል በመጠባበቂያ ከተያዙት ቤቶች እንጂ በመደበኛነት ለተመዝጋቢዎች ከሚተላለፉ ቤቶች አይደለም " ብሏል።

" የልማት ተነሺ ሆነው የጋራ መኖርያ ቤት ምትክ የወሰዱና በ20/80 ወይም በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ተመዝጋቢ የሆኑ ነዋሪዎች ከምዝገባ ቋት ውስጥ የሚቀነሱ ይሆናል " ሲልም አመልክቷል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ። በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል። ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።…
#MoE #Placement

🔴 " እስካሁን ድረስ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፎርም አልሞላንም ፤ ... ውጤት የመጣላቸውን ደግሞ ዝም ብለው መድበዋል " - ተማሪዎች

⚫️ " እውነት ነው ! ጉዳዩን ለክልል ብናሳውቅም መፍትሔ አልተገኘም " - አቶ ዘሪሁን ደርጫቦ

በ2016 ዓ/ም የ 12ኛ ክፍል መውጫ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያመጡ እና በሪሚድያል ፕሮግራም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያመሩ ተማሪዎች በተመደቡ መምህራን ፎርም እንዲሞሉ የት/ት ሚንስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።

በዚህም ሀሙስ ቀን ወደ ክፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ይሁንና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን አመካ ወረዳ ላይ በዲምቢቾ፣ ጌቻ እና ገነዶ ት/ት ቤቶችን እንዲሁም በጎምቦራ ወረዳ ሀቢቾ እና ቢሻና ትምህርት ቤቶች ፎርም አለመሙላታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት ጥቆማ ለማወቅ ተችሏል።

በወረዳው ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እስካሁን ፎርም እንዳልሞሉ እና ከመምህራኖቻቸው ' ሲስተም አስቸግሮናል ' የሚል ምላሽ እንዳገኙ የነገሩን ሲሆን ውጤት የመጣላቸው እንኳን ያልመረጡት እና ፍጹም ካላቸው ውጤት ጋር የማይገናኝ ዩኒቨርሲቲ እንደደረሳቸው ነግረውናል። 

በወረዳዎቹ ፎርሙን እንዲሞሉ የተወከሉት መምህራን ፎርሙን ለመሙላት ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት እንዳስቸገራቸውና መሙላት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

" እስከ ክልል ደውለን ለማሳወቅ ብንሞክርም ጥረታችን አልተሳካም " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዘሪሁን ደርጫቦ ነገሩ እውነት መሆኑን አረጋግጠዋል።

" እኚህ ብቻ ወረዳዎች አይደሉም ዛሬ ብቻ ከሻሸጎ፣ ሾኔ እና ሌሎችም ወረዳዎች እስከ 10 ከሚደርሱ ት/ትቤቶች ተደውሎልኛል" ብለውናል። 

ምክንያቱ ምን ይሆን ?

" የተማሪ ዳታ ሲሞላ በአምና user name ላይ ነበር እንዲሞላ የተደረገው የአምና ካልጠፋ / Delete ካልተደረገ በስተቀር አያስገባም እኔ ደግሞ በአምና ስገባ እኔን ያስገባኝ ቤንሻንጉል ላይ ነው የኔ አካውንት ካልጠፋ ሌላኛው ዞኑ ላይ መግባት አልችልም ማለት ነው የኔን አካውንት አጥፍታችሁ ዞኑ ላይ መልሱኝ ብዬ ለክልል ባሳውቅም ሳያደርጉ ቀርተዋል እዚህ ጋር ነው ክፍተቱ የተፈጠረው።

በዚህም ምንም ወረዳዎችን ላግዝ አልቻልኩም።

የትኛው ይሙላ አይሙላ የማውቀው ነገር የለም አድሚን ስትሆን አይደለ ሚያሳይህ እኔጋ የሚመጣው የቤንሻንጉል መረጃ ነው። ይህ እንዴት እንደሆነ አላውቅም ምናልባት ፌደራል ላይ መረጃ ሲገባ ሊሆን ይችላል ስህተቱ የተፈጠረው።

ምንም መረጃ ልንለዋወጥ አልቻልንም ሪሚድያል ሙሉ በሙሉ አልተሞላም ማለት ይችላል ክልል ላይ በተደጋጋሚ ለማናገር ሞክረን ነበር ነገር ግን አልተሳካም ከወረዳ ሲደወልልኝ ወደ ክልል እየላኳቸው ቆይቻለው " ብለዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ምሽት ብዙዎችን ያነጋገር መልእክትና ፎቶ በይፋዊና በተረጋገጠ የX ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።

ፎቶው ከደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር አብረው ያሉበት ነው።

አቶ ጌታቸው ፤ " ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም ለመቀራረቡ እኛ እንቀርባለን ብላችሁ እኛን ለማገናኘት በመጣር ላይ ያላችሁ ትግራዎት ክብር ይስጣችሁ። ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " ብለዋል ከፎቶው ጋር ባያያዙት ፅሁፍ።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጋራ የተነሱትን ፎቶ ብዙዎች በመጋራት አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አብዛኞቹ ምስሉ በአውንታ ተቀብለው ሲያስተጋቡ ፤ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ " ከአንገት በላይ " ያሉትን ፎቶና መልእክት ንቅፈው እየጻፉ ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለበርካታ ሳምንታት በሚዲያ እና በፅሁፍ መግለጫ ብዙ ሲባባሉ እንደነበር አይዘነጋም።

ምንም እንኳን ዛሬ በምን ጉዳዮች ላይ እንደተነጋገሩ በዝርዝር ባይታወቅም አቶ ጌታቸው ረዳ ያጋሩት ፎቶ ብዙዎችን እያነጋገረ ሲሆን ለአንዳንዶችም ' መካረሩ ያበቃለት ይሆናል ' የሚል ተስፋ የሰጠ ሆኖ ታይቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#MerttEka

🤩 እነዚህ የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የሁሉንም ዕቃዎች ዋጋ  ይሄንን👉 t.iss.one/MerttEka ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

አድራሻችን፦ አዲስ አበባ፤ መገናኛ፤ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል ፤ 3ተኛ ፎቅ ሱቅ 376
King's Computer !

ለግራፊክስ ዲዛይነሮች ፣ ለቢሮ ስራዎችና ለተማሪዎች የሚሆኑ ፥ አዳዲስ ጌሚንግ ላፕቶፖችን እና ዴስክቶፖቹን ፣ ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖችን ከመልካም መስተንግዶ ከተሟሉ ሶፍትዌሮች በጥራት እና በ ብዛት ከ እኛ ጋር ያገኛሉ።

እንገዛለን እንሸጣለን ይዘው ይምጡ ይዘው ይሒዱ። ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር። የተለያዩ ዓይነት ላፕቶፓች ለማየትና ለመምረጥ ሊንኩን ይጠቀሙ - Telegram-  👉https://t.iss.one/kingscom21
Inbox @Yime27

አድራሻ፦ (https://g.co/kgs/HGQYoEP)
መገናኛ ማራቶን ህንፃ አንደኛ ፎቅ 111 ቁጥር king's Computer
ስልክ - +251974060288 +251703077990
#Attention🚨

“ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረው አንጻር ለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚዲያ፣ የተቋማት ትኩረት በመቀነስ ላይ ይገኛል። የሕሙማን ቁጥር ግን እየጨመረ ነው ” - ሆስፒታሉ

የኤች አይ ቪ ኤድስ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ መሆኑን መረጃዎች እየጠቆሙ ቢሆንም የሚዲያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ለቫይረሱ ያላቸው ትኩረት እየቀነሰ መሆኑን ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማህጸን ጫፍ፣ የቆዳ ካንሰሮች ኤች አይ ቪ ኤድስ ሲጨመር አብረው የመጨመር እድል ስላላቸው ከዓመታት በፊት እንደነበረው ሁሉ የሚዲያዎችና ሌሎች ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ በአዲስ አበባ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንዱዓለም ደነቀ አሳስበዋል።

ፕሮፌሰሩ በዝርዝር አሉ ?

“ ኤች አይ ቪ ኤድስ እንደ ህመም አሁንም አለ። መረጃዎች እንደሚያሳዩት በተወሰኑ የአገራችን ክፍሎች አዲስ አበባን ጨምሮ የህሙማኑ ቁጥሩ እየጨመረ ነው። 

እኛ እንደ ተቋም የምንሰጠውን አገልግሎት አላቋረጥንም። እሱን እናካሂዳለን። ግን ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረው አንጻር ለኤች አይ ቪ ኤድስ የሚዲያ፣ የሌሎች ተቋማት ትኩረት በመቀነስ ላይ ይገኛል። 

ይሄ ጉዳይ መታሰብና መሻሻል አለበት። ኤች አይ ቪ ኤድስ የተወሰነ ህክምና አለው። ግን አንዳንዴ ህክምና ማለት ራሱ ቀላል ነገር አይደለም። አለመታመምን አይተካምና።

የኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና በእድሜ ልክ የሚወሰድ ህክምና ነው ያለውና በትኩረተ ሊሰራበት ይገባል የሚል እምነት አለን።

አንዳንዴ ደግሞ መድኃኒቱም ሳይድ ኢፌክት (የጎንዮሽ ጉዳት) አለው። ከመድኃኒቱ በተጨማሪ ከህመሙ ጋር በተያያዣነት ሌሎች ህመሞች ይመጣሉና። 

አንዳንዴ ደግም ሰዎች ላያውቁት ይችላሉ፤ ሳያውቁት ሊቆዩ ይችላሉ እስኪመረመሩ ድረስ። ስለዚህ ምርመራውንም በተቻለ መጠን አጠናክሮ መስራት ያስፈልጋል። 

ድሮ እናቶች ለእርግዝና ክትትል፣ ሌሎች ሰዎችም ለአንዳንድ ህክምና ሲመጡ ይመረመራሉና ያም ነገር አሁንም በደንብ ተያይዞ መቀጠል አለበት።

አንዳንድ ህመሞች ከኤች አይ ቪ ኤድስ ጋር ቁጥራቸውም የመከሰት እድላቸውም ይጨምራል። ለምሳሌ የማኀጸን ጫፍ ካንሰር አንዱ ነው። የአንጀትና የቆዳ ካንሰሮች ሁሉ አሉ።

ሀገርም ደግሞ ምንም ህክምና ቢኖር ካላት ኢኮኖሚ ላይ ሸርፋ ነውና ለዚያ የምታውለውና ከዚህም አንጻር ሲታይ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው።

እኛ እንደተቋም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን ቢያንስ በማከም፣ በማስተማር። ግን አጠቃላይ እንደ አገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚዲያዎችን ጨምሮ አስፈላጊውን ሥራ ሁሉ እንዲሰሩ ይጠበቃል።

ኤች አይ ቪ ኤድስ የጤና ጉዳይ ብቻ አይደለም። የልማት ጉዳይ ነው ተብሎ ለብዙ ጊዜ የተኬደበት ጉዳይ ነውና አሁንም እንደዛው ታስቦ ነው መኬድ ያለበት ”
ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" 7 ሰው ሞቷል ፤ 2 ሰው ተጎድቷል " - በወላይታ ዞን የካዎ ኮይሻ ወረዳ

በወላይታ ዞን፤ ካዎ ኮይሻ ወረዳ ላሾ 01 ቀበሌ እና ኮይሻ ላሾ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በቀን 19/02/2017 ዓ.ም ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት 7 (ሰባት) ሰው የሞተ ሲሆን በ2 ሰው ጉዳት ደርሷል።

በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በፊት በዛው በካዎ ኮይሻ ወረዳ ላይ ጤፓ ቀበሌ በመሬት ናዳ ምክንያት የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም ስሰራ ቢቆይም ተደጋጋሚ አደጋ በመከሰቱ ችግሩ እያባባሰው መምጣቱ ተገልጿል።

መረጀው የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ሥራ ሂደት ነው።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ዛሬ አገልግሎት የሚሰጡ ማደያዎች እና በመሰራጨት ላይ የሚገኝ የነዳጅ አቅርቦት መረጃ ከላይ ተያይዟል።

#AddisAbabaTradeBureau

@tikvahethiopia
#ረቂቅአዋጅ

የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ ትላንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ረቂቁ ምን ይዟል ?

🔵 የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነትና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ።

🔵 የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማስተማሪያነት ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ማስተማር ግዴታ ነው። ክልሎች ግን ከዚያ በፊትም የማስተማሪያ ቋንቋ ማድረግ ከፈለጉ ይችላሉ።

🔵 ተማሪዎች ቢያንስ 3 ቋንቋዎችን እንዲማሩ ይደረጋል። የአፈጻጸም መመሪያ በቀጣይ ይወጣል።

🔵 አንድ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ቋንቋ ከፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች መካከል የተማሪን አልያም የወላጅን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ ከ3ኛ-10ኛ ክፍል ድረስ እንዲማሩ ይደረጋል።

🔵 በአጠቃላይ አንድ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ክልሎች በሚመርጡት መሰረት ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በአማራጭነት ይሰጣል። የእንግሊዘኛ ቋንቋ ደግሞ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት አይነት ይሰጣል።

🔵የተማሪዎች ምዘናን በሚመለከት ደግሞ እስከ 1ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የሚባለው እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ተማሪዎችን በደረጃ ማስቀመጥን ይከለክላል፡፡

🔵 ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወርን በሚመለከት በሁሉም የትምህርት እርከኖች ከክፍል ወደ ክፍል ማለፍ የሚቻለው ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት አይነቶች 50 ከመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲያመጡ ብቻ ነው።

🔵 ክልላዊ ፈተናዎችን ማለፍ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሁለት ጊዜ በላይ በነጻ ፈተና ላይ መቀመጥ አይችሉም። ተፈታኞች በግላቸው እንዲፈተኑ ይደረጋል።

🔵 የመምህራንን ትምህርት እና ስልጠና ጉዳዮችን በሚመለከት ሴቶች ለመምህርነት ስልጠና በሚወዳደሩበት ጊዜ ለምልመላ የሚያስፈልጉትን አጥጋቢ መስፈርት አሟልተው በውድድር ወቅት ከወንዶች ጋር እኩል ነጥብ በሚያገኙበት ወቅት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ይደረጋል።

🔵 አንድ መምህር በስራ ላይ እያለ በመንግስት ወጪ ደረጃውን የሚሻሽል ስልጠና ከወሰደ ለእያንዳንዱ የስልጠና ዓመት አንድ ዓመት በሙያው ማገልግል ግዴታ አለበት።

🔵 ወሲባዊ ጥቃትን የሚመለከቱ ወንጀሎች መፈጸሙ ተረጋግጦ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠበት ሰው በማንኛውም የትምህርት ተቋም ውስጥ በመምህርነት እንዳይቀጠር ይታገዳል።

🔵 የግል ትምህርት ቤትን ማቋቋም በሚመለከት፥
° በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ የተሰጠበት ወይም እዳ መክፈል ያልቻለ ሰው ፣
° ትምህርት ቤቱን ለማቋቋም ፈቃድ ከሚጠይቀው አመልካች ውስጥ ድርሻ ያለው ሰው
° በወሲባዊ ወንጀል አልያም በህጻናት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆናቸው በፍርድ ቤት የተወሰበት ሰው ፈቃድ ማግኘት አይችልም።

🔵 ሀገር አቀፍ የትምህርት ፈንድ እንዲቋቋም አዋጁ ይፈቅዳል ይላል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአል አይን አማርኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ረቂቅአዋጅ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ ትላንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ረቂቁ ምን ይዟል ? 🔵 የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነትና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ። 🔵 የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማስተማሪያነት…
" የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ሳናሻሽል እንዴት አድርገን ነው የትምህርት ጥራትን የምናሳካው ? " - የፓርላማ አባል

አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ በትላንትናው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ቀርቦ በምክር ቤት አባላት አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ለሰው ኃብት ልማት ሥራ ስምሪትኛ ቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።

በዋነኛነት በረቂቅ አዋጁ ላይ የምክር ቤት አባላት ምን አነሱ ?

አንዱ የተነሳው ከትምህርት ጥራት እንዲሁም ከመምህራን ጋር የተነሳ ነው።

ከሦስት በላይ የምክር ቤት አባላት የትምህርት ጥራት በቀጥታ ከመምህራን ጥራት ጋር አገናኝተው ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

በመምህራን የሚቀርቡ ጥያቄዎችንም አዋጁ የሚያስተናግድበት መንገድ እንዲፈጠር ነው የጠየቁት።

የምክር ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የሆኑት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ሳናሻሽል እንዴት አድርገን ነው የትምህርት ጥራትን የምናሳካው ? ስለሚበላው ነገር የሚያስብ ፤ የት እንደሚያድር የሚያስብ መምህራንን ይዘን እንዴት ነው የምናሳካው ?

አሁንማ በሚገርም ሁኔታ ወሩን ጠብቆ ደሞዝ ስላልመጣ ሲያምጽ፣ ተቃውሞ ሲያሰማ የሚታሰርባቸው ክልሎች መኖሩን በተለያዩ ሜንስትሪም ሚዲያዎች የምንሰማበት ነውና የመምህራንን የትምህርት ጥራት ሳናሻሽል የትምህርት ጥራትን ማሳካት አንችልም።

ግብዓቶችን በጥቂቱ ሳናሟላ ውጤት መጠበቁ እንደማያዋጣ አያዋጣም።

ለትምህርት ጥራቱ ብዙ ነገሮች መታየት አለባቸው።

የሀገሪቷ የሥራ እድል ሁኔታ ምን ይመስላል ? ተማሪዎች ምንን አይተው ነው ተነቃቅተው የሚማሩት ወንድሞቻቸው እህቶቻቸው የት ደረጃ የተሻለ ኑሮ የሚኖሩትን አይተው ነው የሚማሩት ?

የሀገሪቷ ሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ፣ እንደዚህ አይነት በጣም ዘግናኝ የሆኑ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን እያዩስ በምን አይነት ተነሳሽነት አይተው ነው ተማሪዎች የሚማሩት ? እነዚህ ሁሉ ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው "
ብለዋል።

ሌላው በምክር ቤት አባላት የተነሳው ሀሳብ ቋንቋን በተመለከተ ነው።

በዚህ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት የምክር ቤቱ አባል ወ/ሮ አቡኔ ዓለም በተለይ ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ጋር በተያያዘ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩና ማብቂያውን በክልሎች እንዲወሰን በረቂቅ አዋጁ መቀመጡ የብሔረሰብ አስተዳደሮችን መብት የሚጋፋ እንደሆነ አስረድተዋል።

ሌላኛዋ የምክር ቤት አባል ወ/ሮ ሲቲ ሬዲዋን ፥ የአፍ መፍቻ ቋንቋ በክልሎች መወሰኑ " የዚያ አከባቢ ሰው ከሌለ የማኅበረሰብ ክፍሎች አሉ " ሲሉ ለክልሎች ኃላፊነቱ መሰጠቱን ተቃውመዋል።

" የወለኔ ህዝብ በአፍ መፍቻ ቋንቋው የመማር እድል አላገኘም " ሲሉ ለአብነት ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ ከአፍ ቋንቋቸው ውጪ " ከፌደራል የሥራ ቋንቋ አንድ መርጠው እንዲሰጡ " የሚለው አገላለጽ ህገመንግስታዊ መሰረት የሌለው ነው ተብሏል።

ይህንን ኃሳብ ያነሱት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ናቸው።

ምን አሉ ?

" ህገመንግስቱ ይሻሻል ችግር የለውም ዜጎች በቋንቋቸው የመማር መብታቸው ይከበር። በጣም የሚበረታታ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ህገ መንግስቱን ሳናሻሽል 5 የሥራ ቋንቋዎች ውስጥ ምረጡ ማለት አስቸጋሪ ነው። " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia