TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Tigray የትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው የተደገፈ ይፋዊ ምክክር አደረጉ። ዛሬ በዓፋርዋ ሰመራ ከተማ የተሳለጠው ግንኙነት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ እና በዓፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ የተመራ ነው።  በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ሰመራ ከተማ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ፕሬዜዳንት አወል አርባ እና ካቢኔያቸው አቀባበል አደርገውለታል። የሁለቱ…
#Afar #Tigray

ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ።

በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል።

ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል አጎራባች ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጸጋይ ገብረተኽለ ፥ " ውይይቱ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ጉርብትና ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያግዝ ውጤታማ ውይይት ነው " ብሎውታል።

" በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጀመር ፣ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ ፣  ነፃ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እና የቆየው የሰላም እና የልማት ግንኙነት እንዲቀጥል በውይይቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል " ብለዋል።

" ሁለቱ ክልሎች በሚያዋስኑ አከባቢዎች ተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚከሰቱ " የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው " ግጭት ጠማቂዎችና ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ ፣ የጋራ የሰላም እና የፀጥታ እቅድ እንዲኖርና በየወሩ እየተገመገመ እንዲመራ ትግራይ እና ዓፋር ተስማምተዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል የነበረው የአንድ ቀን ቆይታ አጠናቅቆ ወደ መቐለ መመለሱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት በመጥቀስ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia  
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Tigray ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ። በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል። ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል…
#Afar #Tigray

" የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ ነው " - ሀጂ አወል አርባ

የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከፍተኛ አመራርን ላካተተዉ ሉዑካን ቡድን ምን አሉ ?

" የአፋርና ትግራይ ህዝቦች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ ነው።

የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ መረጋጋትን ለመፍጠር የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል።

ለክልሉ ሰላምና መረጋገት የድርሻችንን እንወጣለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ህጋዊ እና ትክክለኛ 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን " - በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት   " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ " በሚል መሪ ቃል ሰብሰባ የተቀመጠው በምክትል ሊቀመንበር  አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት  ሰብሰባውን ቀጥሏል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ ካድሬዎች " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ…
#Tigray

" የህወሓትን ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል ሲል " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ገለጸ።

በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ህወሓት ከመስከረም 20 አስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት የአቋም መግለጫ አውጥቷል። 

በዚህም ፥ " የህወሓት ህጋዊነት ለመመለስ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል " ገልጿል።

" ውይይቱን የሚያስቀጥል የትግራይ የሰላም ልኡክ አንደ አዲስ እንዲደራጅና በሰው ሃይል እንዲጠናከር ይደረጋል " ብሏል።

" ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የሪፎርም እቅድ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል " ሲልም ገልጿል።

አቶ ጌታቸው የሚመሩት ህወሓት " ድርጅቱን በማጠናከር የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እንሰራለን " ብሏል። 

በትግራይ የሚታየው ቀላል የማይባል የህግ ጥሰት ስርዓት ለማስያዝና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ በመግለፅም የፀጥታ መዋቅርና የህዝብ ድጋፍ ጠይቋል።

በአቶ ጌታቸው የሚማራው ህወሓት " ከጎረቤቶች ጋር የሚደረግ ግንኙነት ለማሻሻል ሰላማዊ ዝምድና ለማጠናከር ከሁሉም ጎረቤቶች በጋራ እንሰራለን " ብሏል።

ቡድኑ ባካሄዘው የ3 ቀን ውይይት በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከሰባቱ  የትግራይ ዞኖች የተወጣጡ ከፍተኛ ካድሬዎች መገኘታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

@tikvahethiopia 
ኮሚሽነር ግርማይ ማንጁስ !

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና ህይወታቸው እስካላፈበት ጊዜ ድረስ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ኮሚሽነር ግርማይ ባደረባቸዉ ህመም ምክንያት ህክምናቸውን ሲከታተሉ በቢቆዩም በተወለዱ በ60 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።

ከነሐሴ 01 ቀን 1994 ዓ/ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ከዋና መምሪያ እስከ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ኃላፊነት ሠርተዋል።

እስከ ህልፈታቸው ጊዜ ድረስም የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ህዝባቸውን ሲያገለግሉ ነበር።

ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ።

ዛሬ አስክሬናቸው በልዩ ወታደራዊ አጀብ እና ሃይማኖታዊ ስነርዓት ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ተሸኝቷል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ነገ እሁድ ከጠዋቱ  3፡00 ሰዓት በመቐለ ጽርሃ አርያም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

#FederalPolice #Tigray #CommissionerGirmayKebede

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

" ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስርዓት አልበኝነት ለመቆጣጠር " የጥፋት ሃይል " ሲል በስም  ባልገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።

" ህግና ስርዓት ለማስክበር የተጀመሩ ጥረቶች በማጠናክር የህዝቡ ስጋት ከግምት ያስገባ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ " ብሏል ጊዚያዊ አስተዳደሩ።

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 27/2017 ዓ.ም ያወጣውን የመንግስታዊ ስልጣን ሹም ሽር የነቀፈው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ " ቡድኑ ወደ ስርዓት አልበኝነት ለመሸጋገር የሚያስችለው ግልፅ  መንግስታዊ ግልበጣ ማካሄዱን አውጇል " ሲል ከሰዋል።  

" ቡድኑ የመንግስት ስልጣን እንዴትና በምን ሁኔታ እንደሚያዝ ተደብቆት ሳይሆን ከዛሬ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ለማሳካት ሆን ብሎ ያደረገው ነው " ብሏል የጊዚያዊ አስተዳደሩ። 

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህንን ስርዓት አልበኝነት በትእግስት አያልፈውም " ብሎ " የጥፋት ሃይል " ሲል በገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል ብሏል።

" በሂደቱ ለሚፈጠር ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " ሲል አስጠንቅቋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በጉባኤ ያልተሳተፉ 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች በጉባኤ በተሳተፉ 14 አመራሮች ለመተካት " ወሰኛለሁ " የሚል መግለጫ ዛሬ መስከረም 27/2917 ዓ.ም ማውጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#DDR #Tigray

የእንግሊዝ (UK) መንግስት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም (DDR) የሚያግዝ የ16 ነጥብ 9 ሚሊዮን ፓወንድ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታዉቋል፡፡

የድጋፍ ማእቀፉን ያሳወቁት በብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሎርድ ኮሊንስ የተመራው ልዑክ በመቐለ በመገኘት የብሄራዊ ተሀድሶ ቦርድ አባል ሌ/ጀ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ እና ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንዲሁም የዩኤንዲፒ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የቀድሞ ተዋጊዎች ዲሞቢላይዜሽን ማእከል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

#UKinEthiopia

@tikvahethiopia
#Tigray

" ጠቅላይ ሚንስትሩ ያስቀመጡት የመፍትሄ አቅጣጫ ተግባራዊ አልሆነም " - የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ግብረ ሃይል ተወካዮች

የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ግብረ ሃይል ተወካዮች ከሰሞኑን ውይይት ተቀምጠው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ " ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በትግራይ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የተከማች የብድር ወለድና ቅጣት መልክ እንዲይዝ ባለፈው ዓመት የሰየሙት የመፍትሄ አፈላላጊ ቡድን እስካሁን ያስቀመጠው ተጨባጭ ነገር የለም " ብለዋል።

" ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት የአመራር አቅጣጫ የገንዘብ ሚንስቴር ፣ የብሄራዊ ባንክና ልሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግስት የስራ ሃላፊዎች ያካተተ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ቢቋቋምም እስከ አሁን የሚዳሰሰ የሚጨበጥ ለውጥ አልመጣም " ሲሉ ገልጸዋል።

ተወካዮቹ ፥ " ከ7 ወራት በፊት በ2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አዲስ አበባ ከጋበዟቸው የንግድ ማህበረሰብ ያካተተ ልኡክ ጋር ባካሄዱት ውይይት ማጠቃለያ በጦርነቱ ጊዜ የተከማቸው የብድር ወለድና ቅጣት ተሰልቶ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መፍትሄ እንዲሰጠው አቅጣጫ ቢያስቀምጡም እስከ አሁን ጠብ የሚል መፍትሄ አለመጣም ይህም በጣም አሳዝኖናል " ብለዋል።

አበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት የሰጡት የብድር ወለድ ከነቅጣቱ እንዲመለስ የንግድ ማህበረሰቡ ማስጨነቅ እንደጀመሩ በዚሁ ውይይት ወቅት ተነግሯል።

ተግባሩ በጦርነት ምክንያት የደቀቀው የክልሉ ኢኮኖሚያዊ አቅም ይበልጥ ጉልበት የሚያሳጣ መሆኑ በመገንዘብ አገራዊ የፓሊሲና የፓለቲካ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።

ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጥ አይደለምና " አስቸኳይ ትኩረት እና መፍትሄ " እንደሚያሻው አፅንኦት ተሰጥቷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የፌደራል መንግስት የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ የሚታደግ የመፍትሄ እርምጃ እንዲያስቀመጥ ተጠይቋል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
#Tigray

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " - የትግራይ ክልል የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ 

የትግራይ ክልል ፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፤ " የህዝብ እና የሰራዊት አንድነት በማላላት የአርስ በርስ ግጭት እንዲከሰት የሚሰሩት ግለሰቦች እና አካላት አንታገስም " ብሏል።

እንዲህ ያለው ተግባር ላይ ስለተሰማሩት ግለሰቦችና አካላት በግልጽ ስም ጠቅሶ ያለው ነገር የለም።

ቢሮው ፥ " በአገር ውስጥ እና በውጭ በመሆን በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በመጠቀም በሬ ወለደ ውሸት በመንዛት በክልሉ የፀጥታ ሃይልና ህዝብ መካከል ያለው አንድነት እንዲላላ እየተሰራ እያየን በትእግስት ለማለፍ መርጠናል " ብሏል።

" ከአሁን በኋላ ህግ እንዲከበር በጥብቅ ይሰራል " ሲል አስታውቀዋል ።  

" በፀጥታ ሃይሉ ጉድለት አለ የሚል አካል ተጨባጭ አሳማኝ መረጃ በማቅረብ ህጋዊ በሆነ መልኩ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል " ያለው ቢሮው " ይሁን እንጂ ፓለቲካ አስታኮ የሚነዛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ውሸት በግለሰብም ሆነ በየትኛውም አካል አያሰጠይቅም ማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቀዋል። 

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረውም ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " ሲልም ገልጿል።

ቢሮው ፤ " የፀጥታ ሃይል የማንም የፓለቲካ ቡድን መሳሪያ አይደለም " ሲልም አክሏል።

የፀጥታ ኃይሉ በክልሉ ባለው የፓለቲካ መከፋፈል መካከል ገብቶ የአንዱ ደጋፊ የሌላው ተቃዋሚ እንዲሆን ታልሞ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ መሆኑን የገለጸው ቢሮው " ይህ አይሳካም ፍፁም ተቀባይነት የለውም፤ ይህንን ተላልፎ የሚገኝ ግለስብና አካል በህግ እንዲጠየቅ በማድረግ የህግ ልእልና እንዲከበርና የህዝቡ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር እንሰራለን " ብሏል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia