TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ATTENTION🚨
" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።
በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።
ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።
በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።
ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።
ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።
" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።
ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።
አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።
ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።
#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

ትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከሐምሌ 24 እከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም የሚካሄድ እንደሆነ ገልጿል።
የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መማር ፍላጎቱ ያላቸው የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
@tikvahethiopia

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር መተግባር እንደሚጀምር ተሰምቷል።
በትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተፃፈ ደብዳቤ ተመልክተናል።
ደብዳቤው ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣ እና ትክክለኛ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደብዳቤው ከደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አረጋግጧል።
ደብዳቤው ከ2017 ትምህርት ዘመን ጀምሮ ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተግባር እንደሚጀምር ይገልፃል።
በዚህም፦
- የ1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ፦ መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም
- የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 9 እና 10/2017 ዓ.ም
- የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የ2017 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 27 ድረስ ይሰጣል።
(ሙሉው የ2017 ትምህርት ዘመን የአካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል።)
ምንጭ ➡️ @tikvahuniversity

የNGAT ፈተና መቼ ይሰጣል ?
ትምህርት ሚኒስቴር ፥ የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እና የፈተና ቀንን አሳውቋል።
በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ያመለጣቸው አመልካቾች እስከ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም ድረሰ በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ብሏል።
ለፈተናው የተመዘገቡ በየተመደቡበት የፈተና ማዕከላት እና የመፈተኛ ፕሮግራም መሰረት ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናው እንደሚሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
ተፈታኞች በፈተና ወቅት የተሰጣቸውን User Name and Password፣ እና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " - ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ " ፍትሃዊ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ! " በሚል ጭብት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሒዷል።
ጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፥ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርት ሥራን ከፖለቲካ መለየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " ብለዋል ሚኒስትሩ።
" ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በአካባቢ የሚመደብበት ሁኔታ እንደማይኖር " ገልፀዋል።
" የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባ በውድድር እና በብቃት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ይሠራል " ብለዋል።
Via @tikvahuniversity

#AAU #GAT አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መስከረም 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡ በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡ Via @tikvahuniversity
#MoE
ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን እንደ ፈተና ማዕከል መርጣችሁ ለነበራችሁ ተፈታኞች ፈተናው ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
"ዩኒቨርሲቲው በእድሳት ላይ በመሆኑ" የፈተና ማዕከል መቀየር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ ፈተናው መስከረም 3 እና 4/2017 ዓ.ም በሚከተሉት ሰባት ተቋማት ውስጥ እንደሚሰጥ አሳውቋል፦
1. በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣
2. በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
3. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
4. በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት፣
5. በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ፣
6. በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና
7. በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፡፡
የተሰጣችሁን የመፈተኛ ስም (Username) ተጠቅማችሁ በሚደርሳችሁ የመፈተኛ ማዕከል እና የፈተና ሰዓት (Exam Session) መሰረት ፈተናውን እንድትወስዱ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
(ፈተናው የሚሰጠበት ፕሮግራም ከላይ ተያይዟል፡፡)

#ExamResult : የ12ኛ ክፍል ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ2016 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል ? ሲል አንድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን ጠይቋል። እኚሁ ከፍተኛ ኃላፊ ፤ የፈተናው እርማት በጥንቃቄ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጸው እርማቱ እንደተጠናቀቀ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ " እርማቱ…
#MoE
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል።
የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል።

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።
በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።
በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

#MoE በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል። በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል። በመንግስት…
#MoE #Placement
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።