TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተከፍቷል
በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ጋር በተያያዘ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ክፍት ተደርገዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከብሯል።
ከላይ በፎቶ የተያያዘው በላዛሪስት ገዳም ፂዮን ማርያም ቤተክርስቲያን የነበረውን የደመራ በዓል አከባበር የሚያሳይ ነው።
#የኢትዮጵያካቶሊካዊትቤተክርስቲያን
@tikvahethiopia
ከላይ በፎቶ የተያያዘው በላዛሪስት ገዳም ፂዮን ማርያም ቤተክርስቲያን የነበረውን የደመራ በዓል አከባበር የሚያሳይ ነው።
#የኢትዮጵያካቶሊካዊትቤተክርስቲያን
@tikvahethiopia
#Tigray
° " እርባና የሌለው ልዩነታችንን ትተን ለህዝባችን ሰላምና እፎይታ እንስጠው " - አቶ ጌታቸው ረዳ
° " ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግላችን ማጠናከር ይገባል " - የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ በትግራይ ፣ መቐለ ጮምዓ ተራራ ሲከበር የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ሌ/ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ተገኝተው ነበር።
አቶ ጌታቸውም ንግግር አድርገዋል።
" በፓለቲካዊ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ትርጉም የሌለው ልዩነት ወደ ጎን በመተው የህዝቡ ሰላም ማስጠበቅ ከስጋት ተላቅቆ ኦፎይታ እንዲያገኝ መስራት ይገባል " ብለዋል።
አቶ ጌታቸው " እንደ አመራር እርባና የሌለው ልዩነታችንን ወደ ጎን በማለት ለህዝባችን ሰላምና እፎይታን እንስጠው ፤ አንድነታችንን አጠናክረን ብቁ አመራር በመስጠት ወጣቶቻችንን ከህገወጥ ስደት እንታደግ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
" ከቡድናዊነት በመውጣት የጋራ ፍላጎት በማስቀደም ለህዝብና አገር መስራት አለብን " ብለዋል።
" መስቀላችን አንድነታችን የምናጠናክርበት ፣ ሰላማችን ጠብቀን በመከራ ላይ የሚገኘው ተፈናቃይ ህዝባችን ወደ ቄየው የምንመልስበት ፤ የትግራይ ግዛት ሙሉ በሙሉ ተረጋግጦ ወደ እድገት የምናማትርበት ጊዜ ይሁንልን " ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፥ የመስቀል በዓልና ደመራን ምክንያት በማድረግ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት ያስተላለፉት የህወሓት ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለመላ ህዝቡ ፣ ለዳይስፖራው እና ለጸጥታ ኃይሎች እንኳን አደረሳችሁ ካሉ በኃላ" " የተጠናከረ ፓለቲካዊ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ይገባል " በማለት አሳስበዋል።
በዓሉ መስከረም 17/2017 ዓ.ም በዓዲግራት መከበር የሚቀጥል ሲሆን የሃይማኖት መሪዎችና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መምእምናን በተገኙበት እንደሚከበር ዓዲግራት የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
ፎቶ/ቪድዮ፦ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በመቐለ ጮምዓ

ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ። #ኦርቶዶክስተዋሕዶ @tikvahethiopia
#Ethiopia
" በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል " - የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
በመላው ሀገሪቱ በተለይም #በአዲስ_አበባ መስቀል አደባባይ የተከበረው የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።
የፌዴራል ፖሊስ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ህዝብ ፣ ለሀይማኖት አባቶች ፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ፣ ለወጣቶችና በተለይ ደግሞ የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡት የፀጥታ እና ደኅንነት ኃይሎች ምስጋና አቅርቧል።
በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ጨምሮ በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቀዋል።
ከንቲባዋ ፥ " በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አስተዋፅዖ ላደረጉ የሀይማኖት አባቶች ፣ የከተማው ወጣቶች ፣ ሲያስተባብሩ ለነበሩ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እንዲሁም ዶፍ ዝናብ ሳይበግራቸው በዓሉ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዲከበር ላደረጉ የጸጥታ ሃይሎችና የከተማው ነዋሪዎች ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና እናቀርበላ " ብለዋል።
#የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋሕዶቤተክርስቲያን
#Ethiopia #AddisAbaba

#ኢትዮጵያ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦
" ባለፉት ዓመታት ሲፈታተኑን የቆዩ ዙሪያ መለስ ችግሮች መስቀሉ ባስተማረን ሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኝና ህዝባችን ያለምንም ስጋት ወጥቶ እንዲገባ ፣ ሰርቶ እንዲያተርፍ ፣ ተምሮ እንዲያውቅ ፣ ሃይማኖቱን በነጻነት እንዲከተል መንግሥትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለዘላቂ ሰላምና አንድነት አበክረው እንዲሰሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። "