TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ክስ ተመሰረተባቸው። " የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል " በተባሉ 6 ግለሰቦች ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ክስ ተመሰረተ። የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ የመሰረተው ክስ ምን ይላል ? - አውሮፕላንን ያለአግባብ መያዝ ወንጀል፣ - የመንግስት ሰራተኛ የስራ ግዴታውን እንዳይፈጽም መቃወምና አለመታዘዝ የሚል…
#Update

የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ታዘዘ።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ ክስ የቀረበባቸው 6 ግለሰቦች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።

ግለሰቦቹ ፦
- ዮሃንስ ዳንኤል
- አማኑኤል መውጫ፣
- ናትናኤል ወንድወሰን፣
- ኤልያስ ድሪባ፣
- ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።

ዐቃቤ ህግ በ6ቱ ግለሰቦች ላይ የወንጀል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

የቀረበባቸው ክስ ለተከሳሾች ከደረሰ በኋላ በተከሳሾች ጠበቆች በኩል ደንበኞቻቸው " የተከሰሱበት ድንጋጌ በመርህ ደረጃ ዋስትና ሊያስከለክል አይችልም " በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድ ጠይቀዋል።

ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ፤ የወ/መ/ስ/ህግ ቁጥር 67/ለ ጠቅሶ በልዩ ሁኔታ ዋስትና ሊያስከለክል ስለሚችል በሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም የተሰጠባቸው ማለትም ፦
➡️ ከወንጀሉ ከባድነትና ከክሱ ተደራራቢነት፣
➡️ ከጉዳዩ ባህሪና ከከባቢያዊ ሁኔታዎች አንጻር ዋስትና ሊያስከለክሉ የሚችሉበትን ትርጉም የተሰጠባቸው የሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥሮችን ጠቅሶ የዋስትና መብታቸው እንዲታለፍ ጠይቆ ነበር።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት የግራ ቀኝ የዋስትና ክርክሩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ብይን ሰጥቶበታል።

በዚህም ተከሳሾቹ ከቀረበባቸው ተደራራቢ ክስ አንጻር ቢወጡ የዋስትና ግዴታቸውን አክብረው ሊቀርቡ አይችሉም በማለት የጠየቁት የዋስትና ጥያቄን ውድቅ ተደርጎ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ታዟል።

ክሱን ለመመልከትም ለጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡ #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

° “ ልጆቻችን ችግር ላይ ናቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በሕይወታቸው ይድረስልን ” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያን ቤተሰቦች

° “ የእኛ ኤምባሲ ከዛ አገር መንግስት ጋር እየተነጋገረ ልጆች የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየተሞከረ ነው ” - የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ (ባለሥልጣን)

በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፦
➡️ ከአገር ሲወጡ በተዋዋሉት መሠረት ሳይሆን በተቃራኒው ህገወጥ የማጭበርበር ተግባር ላይ እንዲሰማሩ እንደተገደዱ፣
➡️ በአግባቡ ደመወዝ እንደማይከፈላቸው፣
➡️ ይባስ ብሎ ድብደባ እየተፈጸመባቸው አካላቸው እስከመጉደል እንደደረሱ በቤተሰቦቻቸው ጭምር በቲክቫህ ኢትዮጵካ በኩል መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ስለጉዳዩ ምላሽ የጠየቅናቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ “ መረጃው ትክክል ነው፡፡ ዜጎች ችግር ላይ ናቸው ተቋሙም ኃላፊነት ወስዶ ለወገኖቻችን ለመድረስ ጥረት እያደረገ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተውን ነበር፡፡

በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አሁንስ ቤተሰቦች ምን አሉ ?

“ ልጆቻችን ችግር ላይ ናቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በሕይወታቸው ይድረስልን፡፡ ትንሽ ክፍተት አግኝተው ደውለው ሲነግሩን የከፋ ችግር ውስጥ እንደሆኑ ነው የሚያስረዱን፡፡ ተጨነቅን እኮ!

በእርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ ግን ልጆቻችን በዬቀኑ ድብደባና እንግልቱ እየከበደባቸው ነውና መንግስት በቻለው መጠን ተነጋግሮ ወደ አገራቸው እንዲገቡ እንድያደርግልን እንማጸናለን፡፡

መንግስትንም ለማጣደፍ የተገደድነው የወላጅ አንጀት አልችል ቢለን ነው፡፡ ልጆች በባዕድ አገር በእንዲህ አይነት የከፋ ችግር ውስጥ ሆነው ማየት ሀዘኑ መራራ እንደሆነ የወለደ ሁሉ ያውቀዋል ” ብለዋል።

በችግር ላሉት ኢትዮጵያዊያን ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉና ጉዳዩን ከጅምሩ ጀምሮ የሚያውቁት ባለሥልጣን በበኩላቸው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

“ ኢትዮጵያ እንደ አገር እዛ አካባቢ ካሉ አገራት ጋር የሥራ ስምሪት ስምምነት የላትም፡፡ ስለዚህ ልጆቹ በግላቸው ነው የሄዱት፡፡ ማንኛውም ሰው ለሥራ የመንቀሳቀስ መብት አለው፡፡ ከዛ አኳያ ሂደዋል፡፡

ነገር ግን ዜጎች ችግር ላይ ሲወድቁ መንግስት ዝም ብሎ ስለማይመለከት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን ከሰማ ጀምሮ እየሰራ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ የሚሄዱት በታይላንድ በኩል ነው፡፡ ጉዳዩን የሚከታተሉት ህንድና ጃፓን ያሉት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ናቸው፡፡

ከዚህ ቀደም ታይላንድ ላይ ታግተው የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን ማስመለስ ተችሏል፡፡ እኛም የሥራ ስምሪት ወደ እዛ አገር ስለሌለ ዜጎች ወደዛ ባይሄዱ ይመረጣል የሚል መልዕክት ሰጥተናል፡፡

መሄዳቸው ልክ አይደለም ብቻ ሳይሆን ኃላፊነትም መውሰድ መቻል አለባቸው፡፡ ችግር ሲያጋጥም ብቻ መንግስት ላይ መጮህ ተገቢ አይደለም፡፡

ግን እዛ አካባቢ ተቸግረው የነበሩ ልጆችን መንግስት አስመልሷል፡፡ ነገር ግን ወደ ማይናማር የተሻገሩ አሉ፡፡ ወደ ማይናማር የተሻገሩት የሄዱበት ቦታ አስቸጋሪና ታጣቂዎች ያሉበት ቦታ ነው፡፡ የእኛ ኤምባሲ ከዛ አገር መንግስት ጋር እየተነጋገረ ልጆች የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየተሞከረ ነው። ” ብለዋል፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ከሰጡን ማብራሪያ በተጨማሪ፣ “ በተለይ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ወደ ደቡብ አፍሪካ መስመር ነበር የተለመዱት፡፡ አሁን ደግሞ ባልተለመደ ሁኔታ በጣም አዲስ ነገር ነው ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ ሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር በተለይ በደላሎች አማካኝነት ለአደጋ የሚያጋልጥ እንደሆነ ማንኛውም ዜጋ በተለይ ወደ ውጭ አገር ሲንቀሳቀሱ መጠየቅ፣ ማጣራት ያስፈልጋል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የሆነው ሆኖ ግን ውጪ ጉዳይ ኢትዮጵያዊያኑ ካሉበት ችግር እንዲወጡ እየሰራ መሆኑን አመላክቷል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia