TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

ዛሬ በአክሱም ከተማ የብዙዎች መነጋገሪየ የሆነ ፓለቲካዊ ክስተት ተከስቷል።

በመካከላቸው በተፈጠረው ፓለቲካዊ ልዩነት በርቀት በመግለጫዎች ሲጎነታተሉ የከረሙት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በዓመታዊው አክሱም ከተማ የዓይኒ ዋሪ በዓል አከባበር ላይ ተገናኝተዋል።

በመድረኩ በቅደም ተከተል ንግግር ያደረጉት ሁለቱ መሪዎች ከምር ይሁን ከአንገት በላይ በማይታወቅ የእጅ ሰላምታ ተጨባብጠዋል።

ከአክሱም ከተማ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከንግግራቸው በላይ አነጋገሪ የሆነው " በዓሉ ላይ እኔ ነኝ መገኘትና መሳተፍ ያለብኝ " የሚል ክርክርና ሰጣ ገባ መነሳቱ ነው።

ክርክርና ሰጣ ገባቸው የሃይማኖት አባቶች መሃል ገብተው አስማምተው ሁለቱም በመድረኩ እንዲገኙና ንግግር እንዲያደርጉ ለማሳመን የወሰደው ጊዜ ፕሮግራሙ ሳይጀመር ለሰዓታት እንዲራዘም ሆኗል።

ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት ሰጣ ገባ ደጋፊዎቻቸው ደረስ ዘልቆ እስከ አሁን ድረስ በማህበራዊ የትስስር ገፆ እያከራከረ ይገኛል።

ቀድመው ንግግር ያደረጉት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ድርጅታቸው በቅርቡ ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና አተገባበራቸው ያተኮረ ሲሆን ቀጥለው የተናገሩት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በንግግራቸው የጊዚያዊ  አስተዳደሩ የስራ አቅዶችና አንድነትን የሚመለከት ነበር። 

ፕሬዜዳንት ጌታቸው በስም ያልገለፁዋቸው " የውጭ  ጠላቶች " የሚያደርጉት ሙከራ ከትግራይ አቅም በላይ አይደለም ፤ ስለሆነም ከጨለማ ለመውጣት በአንድነት መጓዝ አለብን ብለዋል።

ለሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ትግራይ የነበሩት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ውጥረት መርገብ እንዳለበት ማሳሰባቸው መዘገባችን ይታወሳል። 

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዕለታዊ : የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። የሌሎችም ምንዛሬ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጨማሪ ታይቷል። (ንግድ ባንክ) 💵 አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ 104.0934 ፤ መሸጫ 115.3244 💷 ስተርሊግ መግዣው 128.1856፤ መሸጫው 142.6853 💶 ዩሮ መግዣ 114.4293 ፤ መሸጫ 126. 7877 🇰🇼 የኩዌት ዲናር መግዣው 324.8780…
#ዕለታዊ_ምንዛሬ 

የዶላር ዋጋ ባለፉት ተከታታይ ቀናት ከነበረው ዛሬ ጭማሪ አሳይቷል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት 7 ቀናት ጭማሪ ሳይታይ ወጥ ሊባል የሚችል የምንዛሬ ዋጋ ነበር።

በዛሬው ዕለት ዶላር መግዣው ወደ 105.4304 ከፍ ሲል መሸጫው ወደ 117.0277 ጨምሯል።

ፓውንድ መግዣው 132.5631 ፤ መሸጫው 147.8322 ገብቷል።

ዩሮ 116.7747 መግዣው ሲሆን 129.6199 መሸጫው ነው።

በግል ባንኮች አንዱ ዶላር መግዣው ከ104 ብር አንስቶ እስከ 120 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው።

(በተለያዩ የግል ባንኮች ያለው የምንዛሬ ዋጋ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " መጀመሪያ 250 ሚሊዮን ብር ከዛ 200 ሚሊዮን ብር ጉቦ ጠየቁን " - ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሀገር ጥለው አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ዛሬ አሜሪካ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል። " ከሀገረ የወጣሁት በግፈኞች ምክንያት ተገድጄ ነው " ብለዋል። ባልፈው የግላቸውን ጨምሮ የድርጅቱ የባንክ አካውንቶች በሙሉ በመንግስት…
#PurposeBlack

የፐርፐዝ ብላክ ኢ ቲ ኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ሥራ አስፈጻሚዎቹ ስልጣንን አለአግባብ በመገልገል እና ከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው ዛሬ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በማኅበሩ ተጭበርብረናል ያሉ ባለአክሲዮኖች ለፖሊስ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ምርመራ ተጀምሮ የአክሲዮን ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ማኅበሩ መሀል ሜክሲኮ ላይ ገና በእጁ ባላስገባው መሬት እና ይዞታ ቤት ገንብቶ ባለ 3 መኝታ አፓርትመንት በ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ እና በራሪ ወረቀቶች በማስተዋወቅ ከሕዝቡ ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱን በተለያየ መንገድ ከሕብረተሰቡ ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎች ያመላክታሉ ተብሏል።

በዚህ መነሻም ሥራ አስፈጻሚዎቹ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፍትሕ ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ፍስሃ እሸቱ ከወራት በፊት ሀገር ጥለው አሜሪካ መግባታቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
🌼 እንቁጣጣሽ የአዲስ ዓመት የንግድ ትርኢትና ባዛር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ !

በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የዐውደ ዓመት ገበያ ደርቷል፤ ለአዲስ ዓመት የሚያስፈልግዎትን ለመሸመት ጎራ ይበሉ!

በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ወይም *127# የመግቢያ ትኬት ሲገዙ እንዲሁም ሲገበዩ እስከ 2500 ብር ድረስ ላለው 10% ተመላሽ ያገኛሉ።

🗓 እስከ ጳጉሜ 05/2016 ዓ.ም ይቆያል

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #SmartAfrica #RealizingDigitalEthiopia
#MesiratEthiopia

💼 ቢዝነሱን ማሳደግ ለሚፈልግ ⬇️
- በፋይናንስ፣
- በማርኬቲንግ፣
- ችሎታን በማዳበር፣
- በቴክኖሎጂ፣
- በኔትወርኪንግ፣
- የባለሙያ አማካሪዎችን በማግኘት፣
- በፖሊሲ፣
- በአገልግሎት ሰጪነት እና
- በአማካሪነት ድጋፍ ለማግኘት https://mesirat.acceleratorapp.co/application/new ላይ ተመዝገቡ።

የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም አባል ይሁኑና ቢዝነስዎ እንዲያድግ አጠቃላይ ድጋፍን ያግኙ።

ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ!
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert🚨 ኦሞ ወንዝ በከፍተኛ ሁኔታ በመሙላቱ የወንዙ ውሃ እና የቱርካና ሀይቅ ይዞታውን እያሰፋ በመሆኑ በኦሞራቴ ከተማ በ1.9 ኪ/ሜ ርቀት አከባቢ በተለያዩ ቦታዎች የመሬት መሰንጠቅ እዲሁም ውሃው ውስጥ ለውስጥ እየሄደ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል። @tikvahethiopia
#ትኩረት🚨

ኦሞራቴ ዙሪያ 500 ሜትር እርዝመትና ሁለት ሜትር ጥልቀት ያለዉ የመሬት መሰንጠቅ ተከስቷል።

የከተማዉ ነዋሪዎች " የመሬት መሰንጠቁ ውሀዉ መድረሱን ያሳያልና ድረሱልን " እያሉ ነው።

ከሰሞኑን የኦሞ ወንዝ መሙላቱን ተከትሎ በርካታ አርብቶ አደሮች መፈናቀላቸውንና አካባቢው በውሀው ከመጥለቅለቁ ባለፈ የወረዳው ዋና ከተማ ኦሞራቴ መቅረቡ የከተማውን ማህበረሰብ ስጋት ውስጥ እንዳስገባው ነግረናችሁ ነበር።

አሁን ደግሞ የተፈጠረዉ የመሬት መሰንጠቅ ሌላ የድንጋጤ ምክኒያት ሆኗል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች " ውሀው ከመቅረቡ ባለፈ በአካባቢው የመሬት መሰንጠቅ መፈጠሩ በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል " ብለዋል።

ውሀው ወደ ከተማው መጠጋቱን ለመከላከል እና አቅጣጫውን ለማስቀየር በሰው ሀይል ጥረት ቢደረግም ውሀው ውስጥ ለውስጥ መጠጋቱን የፈጠረዉ የመሬት መሰንጠቅ ይጠቁማል ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸዉን የሰጡን የወረዳዉ አስተዳዳሪ አሁን ላይ ህዝቡን ያሰጋዉ አምስት መቶ ሜትር ርዝመትና ሁለት ሜትር ጥልቀት ያለው የመሬት መሰንጠቅ በመፈጠሩ ነው ብለዋል።

አንድ ዶዘር መድረሱንና ስካቫተር እየመጣ መሆኑን ጠቁመው ይህም የውሀዉን አቅጣጫ ለመቀየርና ለማፍሰስ ይረዳል በማለት ይህም እየተከሰተ ያለውን የመሬት መሰንጠቅ አስቁሞ ማህበረሰቡን ያረጋጋል ብለዋል።

አሁን ላይ ምንም እንኳን ዶዘር መድረሱና ስካቫተር እየመጣ መሆኑ ተስፋ ቢሰጠንም የነዳጅ የሰዉ ሀይልና አጠቃላይ ኦፕሬሽን ኮስት ስለሚያስፈልገን የክልሉና የፌደራሉ መንግስት ሊያግዘን ይገባል ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia