TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በአመራሮች መካከል ከፍተኛ ክፍፍል የፈጠረውና በምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈገው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ በዝግ ሲመክር ውሏል። በዛሬ ውሎው የአዘጋጅ ኮሚቴ ሪፓርት አቅርቦ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በሙሉ ድምፅ ማፀደቁ ተሰምቷል።  ከመላው ትግራይ በድምፅ መሳተፍ ከሚገባቸው 950 ጉባኤተኞች 785 ማለትም 83% ተገኝተዋል ተብሏል። የተለያዩ ወረዳዎች በድምጽ የሚሳተፍ ሰው እንዳላኩ ተሰምቷል። ከዛሬው…
#TPLF

ከህወሓት ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆኑት የማይጨው ከተማ ከንቲባ አቶ የማነ ንጉስ ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል ፤ " ጉባኤው የተወሰነ ቡድን ለማጥቃት በችኮላ የተጠራ ነው " ብለዋል።

በዚህም እሳቸው ጨምሮ በርካቶች ተቃውሞዋቸውን በመግለፅ ከመድረኩ መቅረታቸውን አመልክተዋል።

የህወሓት ማእከላዊ ቁጥጥር ኮምሽን ሊቀ መንበር አቶ ተክለብርሃን አርአያ ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ " 14ተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተብሎ የተጀመረው ስብሰባ ህወሓትን ወደከፋ ችግር የሚያስገባ ነው " በማለት ጉባኤውን አውግዘዋል።

አቶ ተክለብርሃን ፥ " አንድነታችን ይዘን ፣ የፕሪቶርያው ውል ማእከል አድርገን፣ ለአላዊነታችን አረጋግጠን በተጨማሪም አንድ ላይ በመንቀሳቀስ ሕጋዊ እውቅናችን መልሰን ሊደረግ የሚገባው ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ ጉባኤ ግን ወደ ቅርቃር ውስጥ የሚያስገባን ነው " ብለዋል።

" ተግባብተን ወደ አንድ መንገድ መጥተን ልናደርገው ይገባ የነበረ ነው። ላይ ያለው አመራሩ ብቻ ሳይሆን ታች ያለው አባልም ጭምር መግባባት የፈጠረበት ሊሆን ይገባ ነበር " ማለታቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " ሁሉንም የፓለቲካ ሃይሎች ያቀፈ መንግስት በአስቸኳይ መመስረት ያስፈጋል " - ሦስት የፓለቲካ ፓርቲዎች በትግራይ የሚንቀሳቀሱት ባይቶና፣ ሳወት፣ ናፅነት የፓለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ ፤ " ሳምንቱን በስርዓቱ ባለቤቶች መካከል በመካሄድ ያለው ህገ-ወጥ እንቃስቃሴና ፍጥጫ ተው መባል ይገባዋል " ብለዋል። በህወሓት አመራሮች የተፈጠረው ፍጥጫ ተከትሎ በህዝቡ የሚታየው መረበሽ…
#TPLF

" በህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ስም ማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም " - እነ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ጉባኤ ውሳኔ

በአመራሮች መካከል ክፍፍል የፈጠረው የህወሓት ጉባኤ ባወጣው መግለጫ ፥ " የተለየ ሃሳብ አለኝ " የሚል በጉባኤ ያልተገኘ አካል ወደ ጉባኤው ቀርቦ ሃሳቡ በነፃነት እንዲገልፅ ፣ በዴሞክራሲያዊ ምጉት ለሚተላለፉት ውሳኔዎች ተገዢ እንዲሆን ነሃሴ 8/2016 ዓ.ም ጥሪ ማቅረቡ አስታውሰዋል።

" የድርጅቱ ጉባኤ ከተሰየመበትና ከተጀመረበት ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም ቀን በኋላ ተራ አባል እንጂ የማእከላዊ ኮሚቴ የሚባል ሃላፊነት የላቸውም " ብሏል የእነ አቶ ጌታቸው ረዳ አቋም በመደገፍ ጉባኤውን ላወገዙ የቀድሞ ጉምቱ አመራሮቹ።

" ስለሆነም ከህግና ተቋማዊ የደርጅታችን አሰራር ውጪ በአሁኑ ወቅት በህወሓት ስም ማንኛውም የፓለቲካ ስራ ለመፈፀም ሃላፊነት ያለው የማእከላዊ ኮሚቴና የማዕከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ሆነ ሌላ አካል የለም " በማለት አብራርቷል።

" ስለዚህ ህዝባችንና መላ አባላችን ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የጉባኤውን ውሳኔ በመረዳት እንዲተገብሩና እንዲተገበር  እንዲሰሩ ጥሪ እናቀርባለን " በማለት አክለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፤ ቀደም ብሎ ለዚህ ጉባኤና በጉባኤው ለሚተላለፉ ማናቸውም ውሳኔዎች ምንም እውቅና እንደማይሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

በምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰረት አሰራሩን ያልተከተለ ጉባኤ null and void / ምንም እውቅናና ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው።

በሌላ በኩል ፥ በአሁን ሰዓት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት እና የህወሓት ም/ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ እየሰጡ ናቸው፤ ያነሷቸውን ሀሳቦች እናደርሳችኋለን።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን : በመቐለ ከተማ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ በወቅታዊ የህወሓት የፓለቲካ ሁኔት ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ መድረኩ ላይ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " ብለው የተቃወሙ ፦ ➡️ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ፣ ➡️ የድርጅቱ የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን ፣ ➡️ የክልል ፣ የዞን ፣ የወረዳና ሌሎች አመራሮች…
#TPLF

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

ዛሬ መቐለ ሁለት ስብሰባ ሲካሄድ ውሏል።

አንዱ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚገኙበት 14ኛ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን ሌላኛው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጉባኤውም የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ የክልል፣ የዞን እና ወረዳ አመራሮች የተገኙበት ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

-  ያለ ልዩነት (በአመራሮች መካከል) " ጉባኤ ይደረግ አይደረግ " የሚል ሳይሆን እንዴት ይደረግ የሚል ነው።

- የእውቅናው ጉዳይ ከፌደራል መንግስት ጋር በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት መፍትሔ እንዲገኝለት ሁሉም ተግባብቶ እያለ፥ የተወሰኑ ግለሰቦች በጎን በመንቀሳቀስ ወደ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወረቀት በማስገባት ከመግባባቱ ያፈነገጠ ስራ ከውነዋል።

- የተፈጠረው አለመግባባትና ክፍፍል፥ የፕሪቶሪያ ስምምነት ያለባለቤት የሚቀርበት ዕድል የሚፈጥር ነው። ይህን አደጋ ለመቀልበስ ጥረት ይደረጋል።

- ሁኔታው የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ሂደት ባለቤት አልባ ሊያደርግ የሚችል ነው። ይህን ጉባኤ የፌደራል መንግስት አልተቀበለውም። ፌደራል አለመቀበሉ የራሱ ትርጉም አለው። ዋናው ነገር ግን በፓርቲያችን ውስጥ አንድነት እና መቀራረብ፣ በሐሳቦች ዙርያ አብሮ መስራት ሳይሆን መከፋፈል እና መራራቅ የሚያስከትል አደገኛ መድረክ ነው።

- የተፈጠረው ልዩነት አስጊና 'ጠላቶች' ሊጠቀሙበት የሚችል ነው።


ትላንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ፥ " የህዝብ የሰላም ፍላጎት ወደጎን በመተው፣ ለግዜው ማን መሆኑ በግልፅ ከማይታወቅ እና እነሱ ደጀን ይሆነናል ያሉት የውጭ ኃይል ተማምነህ፥ ያልሆነ ዝግጅት፣ የተወሰነ ግለሰቦች ጠባብ ፍላጎት ሲባል የትግራይ ህዝብን ዳግም ወደ አደጋ ለመዳረግ የሚደረግ እንቅሰቃሴ ነው እየተካሄደ ያለው " ብለው ነበር።

ለዚህ ቃላቸው የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ቃል አቀባይ አቶ አማኑኤል አሰፋ ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ አማኑኤል " ይህ አገላለጽ ትክክል አይደለም። ህወሓት እምነቱ በትግራይ ሕዝብ፣ በፕሪቶሪያው የሰላም ሥምምነት በተቋማዊ አሰራር ነው። ሁሉም ችግሮች በሰላማዊ ፖለቲካዊ መንገድ ይፈታሉ ብለን ነው የምናምነው " ነው ያሉት። #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል። ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል። " በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት…
ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ?

" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ

በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል።

አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ተሰብስቦ ስለ አንድ ድርጅት ውስጣዊ ጉዳዮች መወሰን ወደ ጦርነት የሚያስገባ አንድም ምክንያት የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ጦርነት በዚህን ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ ርካሽ አይደለም " ብለዋል።

" ጦርነት አስፈላጊ ሆኖ አማራጭ ቢሆን ኖሮ ትግራይ ውስጥ ያሉት ችግሮች ሌላ ጦርነት ይጋብዙ ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።

እንዚህ ችግሮች ለተፈጸሙ ወንጀሎች የተጠያቂነት አለመረጋገጥ ፣ በህገመንግስት ላይ የተቀመጠው የክልሉ ግዛት አለመመለስ ፣ የተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው አለመመለስ ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ ...ወዘተ እንደሆኑ ነው የጠቆሙት።

" ዛሬም ትግራይ ውስጥ ብዙ ችግሮች አሉ። ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለባቸው ነው ግን የተጀመረውን የሰላም ተስፋ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገር ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለ እየኖረ ነው " ብለዋል።

" ያሉ ችግሮች ወደ ጦርነት ሳያስገቡ አንድ ህወሓት የሚባል ድርጅት በፕሪቶሪያ ስምምነት አካል የሆነ ባለቤት የሆነ ውስጣዊ ችግሮች አጋጥመውት ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል ስራ በመስራቱ ወደ ጦርነት ሊገባ አይችልም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ ብለዋል ... እንዲህ ብለዋል ተብሎ የተለያየ ትርጉም ከተሰጠው በኃላ ይሄን በሚመለከት ህወሓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን engage አድርጓል። " ብለዋል።

" በዚህ ደረጃ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባን ነገር እንደሌለ ግልጽ ሆኗል " ሲሉ አክለዋል።

" ህወሓት አንድ ድርጅት ነው " ያሉት አቶ አማኑኤል አሰፋ ፥ " የተለያዩ ስራዎች ሊሰራ ይችላል ፤ ያን ስራ በሚመለከት መወያየትና መነጋገር ይቻላል። ችግሮች ካሉ ለመወያየት እና አብሮ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የተጀመረ የሰላም ማዕቀፍ አለ ያን መሰረት አድርጎ መወያየት እና መፍታት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ የተደረጉ ጦርነቶች ናቸው የዛሬውን ችግር ያመጡት " የሚሉት አቶ አማኑኤል " ብዙ ችግር ባለበት ሀገር ሆነን አሁንም ጦርነት ውስጥ ለመግባት የሚያስችል ምንም ምክንያት የለም " ብለዋል።

" ስለተሰበሰብን ፣ አንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ህወሓት የሆነ ነገር ስላደረገ ጦርነት አይመጣም ፤ እንዴት ጦርነት በዚህ ልክ ርካሽ ይሆናል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው ፤ ውስጣዊ ችግሩን ለመፍታት ነው ጉባኤ የሚደረገው " ሲሉ ለወይን በሰጡት ቃለ መጠየቅ ተናግረዋል።

#TPLF #TIGRAY

@tikvahethiopia