" ተስፋ ቆርጠናል " - ቆጣቢዎች
በአዲስ አበባ የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት በሚል መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም የኮንዶሚንየም ቤት ምዝገባን በ1997 እና 2005 ያደረገ ሲሆን እጣው የዘገየባቸው ነዋሪዎች " ተስፋ ቆርጠናል " ሲሉ ገለጹ።
ነዋሪዎቹ ቃላቸውን የሰጡት #ለአሃዱ ነው።
ከተመዘገቡ 19 እና 11 ዓመታት እንዳለፋቸው የተናገሩት ተመዝጋቢዎች " ከወደ መንግስትም ምንም አይነት መረጃ እየወጣ አለመሆኑ ጥያቄ ፈጥሮብናል " ብለዋል።
" የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን " የሚሉት ተመዝጋቢዎቹ " በመንግስት በኩል ቅድሚያ እየተሰጣቸው ያሉ ነገሮች ተመዝጋቢዎቹ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ያስገባ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋን።
ለአብነትም ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን 3 ሺህ የሚሆኑ ቤቶችን በመግንባት ለሽያጭ ማቅረቡን በማስታወስ " ለምን እንዲህ ይደረጋል ? የሚል ጥያቄ ብናቀርብም ሰሚ አልነበረም " ብለዋል።
የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ምን አለ ?
ኮርፖሬሽኑ " አትቆጥቡ ያለ አካል የለም ከመንግስት በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግንባታዎች እየተካሄዱ ነው " ብሏል።
" ተመዝጋቢዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ " ሲልም ጠይቋል።
ለኮንዶሚኒየም ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎች የት ቦታ ምን እየተሰራ እንደሆነ መግለጽ ከተቻለ በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፤ " እየተሰራ መሆኑን መግለጽ በቂ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮንዶሚንየም ተመዝጋቢዎች ምን ስራዎችን እየከወነ ይገኛል ? በሚል ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢቀርብም ጽ/ቤቱ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።
ሁለት አስርት ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ወራት የቀረው ተመዝጋቢ ለሌሎች ዓመታት በትዕግስት እንዲጠብቅ ተገልጾለታል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሃዱ ነው።
#AddisAbaba #AhaduRadioFM
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM