TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በውሃ እጥረት ምክንያት ነዋሪዎች እየተቸገሩ ነው።

ከዚህ ቀደም ፕሮግራም ውሃ የሚመጣባቸው አካባቢዎች ላለፉር ተከታታይ ቀናት ውሃ ማግኘት አልቻሉም፤ ይህም ደግሞ በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከሰሞኑ እየታየ ካለው የውሃ እጥረት ጋር በተያያዘ የከተማው ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ምላሽ ሠጥቷል።

ባለስልጣኑ እንደሚለው ከሆነ ሰሞኑን በመዲናይቱ በተፈጠረ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የውሃ ምርት እና ስርጭት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው።

የኤሌትሪክ መቆራረጥ ችግሩ በአቃቂ ጉድጓዶች እና ግፊት መስጫ ጣቢያዎች ላይ መፈጠሩንም ገልጿል፤ ይህ ሁኔታ ውሃ ለደንበኞቹ በወጣው መረሀ ግብር መሰረት እንዳይሰጥ ችግር እንደፈጠረበት አስውቋል።

በዚህም ፦
- ገላን አካባቢ፣
- ሳሪስ፣
- ሀና ማርያም፣
- ሀይሌ ጋርመንት፣
- ላፍቶ፣
- ጀሞ፣
- ቆሬ፣
- ሳር ቤት፣
- ሜክሲኮ፣
- ልደታ፣
- ጌጃ ሰፈርና ቤቴል አካባቢዎች ውሃ ለማሰራጨት #አልተቻለም ተብሏል።

በተጨማሪ ፥ በለገዳዲ ጉድጓዶች ላይ በየሰዓቱ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በባለስልጣኑ አገልግሎት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የችግሩን ስፋት በመረዳት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰራጨው ፅሁፍ ጠይቋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦዲት #ኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር  ከፍተኛ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት መካከል መሆናቸው ተሰምቷል። ለውሎ አበል እና ለመጓጓዣ እንዲሁም ለግዥ የተሰጠ ክፍያ ሰራተኛው ስራውን አጠናቆ ከተመልሱ በኃላ በ7 ቀናት መወራረድ እንዳለበት መመሪያ አለ። ነገር ግን በ124 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው ብር 14.1 ቢሊዮን በወቅቱ ያልተወራረደ ወይም ያልተሰበሰበ ተሰብሳቢ ሂሳብ…
#ኦዲት

የተሰበሰበው ገቢ #ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ሂሳብ ኦዲት ሲደረግ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት #በዶላር የተሰበሰበ 1.3 ሚሊዮን ገቢ ትክክለኝነቱን ማረጋገጥ #አልተቻለም

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ማንኛውም ገቢ ተገቢ ማስረጃ ሳይሟላ በገቢ መመዝገብ ፍጹም ትክክል እንዳልሆነ አስገንብዝቦ የገቢ ማስረጃዎች በትክክል ተደራጅቶ እንዲያዝ ተገቢው ማስተካከያም እንዲደረግና እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።

@tikvahethiopia