TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎች ፤ " ጤና ሚኒስቴር በሕግ የተወሰነልንን ልዩ አበል አልከፈለንም " አሉ። የጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት፤ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ / ም መከሰቱን ተከትሎ የጤና ማኒስቴር ባወጣው ጥሪ መሠረት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ / ም ባወጣው መመሪያ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ለመላው ሀኪሞች በቀን…
#ጤና_ሚኒስቴር #ክስ

የፍርድ ቤት ውሳኔን በተደጋጋሚ ጣሰ የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " ለ70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ -19 ልዩ አበል እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ አስተላለፈበት።

70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ወረርሽኝ #ልዩ_አበል እንዲሰጣቸው በመሰረቱበት ክስ መሠረት ገንዘቡን እንዲከፍል ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በተደጋጋሚ ጥሷል የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " አሁንም ከንግድ ባንክ አካውንቱ #እየቆረጠ_እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጤና ባለሙያዎቹ ገለጻና ከተጻፈው ደብዳቤ መረዳት ችሏል።

የጤና ባለሙያዎቹ ተወካይ የፍርድ ሂደቱ በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

* ፍርድ ቤት ለባንክ ሲያዝ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

* የፋይናንስ ክፍሉ ኃላፊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ድክመት ለፍርድ ቤት #ታስረው ቀርበው እንዲያስረዱ ቢታዘዝም ጉዳዩን እንዲያስፈፅም የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ መስሪያ ቤቱ ድርስ በመሄድ ቢጠይቅም እረፍት እንደወጡና እስከ ሰኞ (ያለፈው ሳምንት ሰኞ) እንደሚመጡ አሳውቀው ነበር። ከዚያ በኋላም ፍርድ ቤት መጥተው አያውቁም።

* ታስረው እንዲቀርቡም #ከሁለት_ጊዜ_በላይ ነው የታዘዘው።

* ፍርድ ቤት በራሳቸው እንዲፈፅሙ ግን በተደጋጋሚ (ከአምስት ጊዜ በላይ) ትዛዝ ሰቶ ነበር።

* ሰዎቹ በፍፁም ለህግ ተገዢ አለመሆናቸውን እና እምቢተኝነታቸውን በተደጋጋሚ ጊዜ አሳይተውናል።

* ለፍርድ ቤት ውሳኔ ያላቸው ንቀት በቃላት የሚገለፅ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ይሄንን የጤና ባለሞያዎች መረጃ በማደራጀት ሂደት የጤና ሚኒስቴርን ምላሽ እና ማብራሪያ ለማካከት ብዙ ቢደክምም ምላሽ ሰጪ አላገኘም።

አሁንም #በአካልም ይሁን #በስልክ ምላሽ ሰጣለሁ የሚል የሚኒስቴር መ/ቤቱን አካል ለማስተናገድ ዝግጁ ነው።

ዝርዝሩን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-14

የመረጃው ዝግጅት በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ሬዚደንት #JU

“ የ3 ወራት ያህል ደመወዝ አልተከፈለንም ” - የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬዚደንት ሀኪሞች

“ ይህ ጉዳይ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው ” - ዩኒቨርሲቲው

በ2016 ዓ/ም በጤና ሚኒስቴር #በጅማ_ዩኒቨርሲቲ  ተመድበው በሆስፒታሉ ሥራና ስፔሳላይዜሽን ስልጠና የሚወስዱ 70 የአንደኛ ዓመት ሬዚደንት ሀኪሞች የ3 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታ አቅርበዋል። 

“ የ3 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ከፍተኛ ችግርና ስቃይ ውስጥ ወድቀናል ” ያሉት ቅሬታ አቅርቤዎቹ፣ ጉዳዩ የሚመለከተውን አካል ቢያነጋግሩም ‘ መፍትሄ እየፈለግን ነው ፤ ዩኒቨርሲቲው በጀት የለውም ’ እንደተባሉ ገልጸዋል።

መጀመሪያ 100 ሬዚደንት ሀኪሞች እንደነበሩ ፤ በኋላ ግን ለቀው ለመሄድ በመገደዳቸው አሁን ላይ የቀሩት 70 ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ቤተሰብ ጭምር ይዘው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሄዱ ሬዚደንት ሀኪሞችም እንዳሉ ፤ የሚተዳደሩት ከደመወዝ በሚያገኙት ገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

“ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው። ደመወዙ በዚህ ሳምንት ሊገባልን ይገባል ” ሲሉ አሳስበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ፣ “ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው። እኛን አይመለከትም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመጠየቅ ወደ #ጤና_ሚኒስቴር የተደረገው ሙከራ ኃላፊዎቹ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ቃላቸውን ማካተት አልተቻለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia