TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
Elias Meseret : የሀሳብ ማዕድ

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው ሁለተኛው "የሀሳብ ማዕድ" ዝግጅት በስኬት፣ በሰላም ተጠናቋል!

#ከትግራይ
#ከኦሮሚያ
#ከደቡብ
#ከአፋር
#ከአማራ
#ከሱማሌ...የተጋበዙ አክቲቪስቶች እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተፅእኖ የሚፈጥሩ ግለሰቦች ተገኝተው ነበር👏

@tsegabwolde @tikvahethiopia
' ሕዝበ ውሳኔ '

የአማራ ክልል መንግሥት የማንነት እና የወሰን ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ እንዲፈታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ሲል አሳወቀ።

የክልሉ መንግሥት ይህን ያሳወቀው ዛሬ በኮሚኒኬሽን ቢሮው በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።

የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫቸው ፤ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ጥያቄ የሚያነሱባቸውን የማንነት እና የወሰን ጉዳዮችን በተመለከተ አንስተዋል።

አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ፤ " የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ቢያንስ ከ30 ዓመት በኃላ በ #ሕዝበ_ውሳኔ በሕጋዊ መንገድ እንዲያልቅ #ስራዎች_እየተሰሩ_ይገኛሉ " ብለዋል።

የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ አቶ ግዛቸው ገልጸዋል።

ትላንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፤ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ የሰጡት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል ስላለው የይገባኛል ጥያቄ ጉዳይ አንስተው ነበር።

ዶ/ር ዐቢይ " በአማራና ትግራይ መካከል ያሉ ባለፉት 30 ዓመታት ጥያቄያቸው ሲነሳ የነበሩ ቦታዎች አሉ ፤ ይሄ በተለይ ታላቁ የአማራ ህዝብ ፣ የትግራይ ህዝብ በሰከነ መንገድ እንዲያየው መክራለሁ " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ፤  " #በመሬት ምክንያት መባላት ፣ መገዳደል አያስፈልግም ፤ መሬት የፀብ ምንጭ መሆን የለበትም ፤ ህዝቦች ተወያይተው ተመካክረው በ ' win win approach ' ጊዜ ወስደው በሰከነ መንገድ የትኛው ክልል መኖር እንደሚፈልጉ መወሰን ይችላሉ ፤ ይህንን ሲዳማ ላይ አድርገነዋል፣ ደቡብ ምዕረብ ላይ አድርገነዋል፣ ትላንትም ወስነናል ስለዚህ በሰከነ መንገድ ሰዎች ወስነው ሰው ሳይሞት ማድረግ ይቻላል ፤ ከዛ ውጭ ያለው አማራጭ ጥሩ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" መነጣጠቅ ጥቅም የለውም፤ ዘላቂ ሰላም ማምጣት ያስፈልጋል " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " #አማራን እንዳለ ቆርጦ #ከትግራይ ጉርብትና ማንሳት አይቻልም ትግራይንም እንዲሁ ፤ አብሮ የሚኖር ህዝብ ነው ፤ ዋናው አስፈላጊ ነገር ሰላም ነው ፤ ይሄን ታሳቢ በማድረግ ፦
- በሰከነ መንገድ በውይይት
- የተፈናቀለውን መልሰን፣
- የተጎዳውን ጠግነን
- የተጣላውን አስታርቀን በ #ህዝብ_ውሳኔ ነገሮች በህጋዊ መንገድ ለዘለቄታው እልባት እንዲያገኙ በልበ ሰፊነት ካልሰራን በስተቀር ጥፋት ነው ፤ ብንዋጋም ዘላቂ ድል አናመጣም " ብለዋል።

በአማራና ትግራይ ክልሎች የማንነትና የወስነ ጥያቄ ከሚነሳባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው የወልቃይት አካባቢ አሁን ላይ #በኃላፊነት_ደረጃ እያገለገሉ የሚገኙት ኮሎኔሌ ደመቀ ዘውዱ ፤ ከሳምንታት በፊት የህዝበ ውሳኔ ጉዳይን በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር።

በወቅቱም ፤ ' ሕዝበ ውሳኔ ' ተገቢም እውነትም ነው ብለው እንደማያስቡና ወልቃይት ጠገዴ በጉልበት ወደ ትግራይ የተጠቃለለ በመሆኑ፣ በሕግም በታሪክም ተጣርቶ ሕጋዊ ምላሽ ይሰጠናል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረው ነበር።

ኮሎኔል ደመቀ ፤ " ዘላቂ መፍትሄ የሚገኘው የተፈጸሙ በደሎችን እና ታሪካዊ እውነታዎችን ታሳቢ ያደረገ ፖለቲካዊ ውሳኔ ሲሰጥ ነው " ያሉ ሲሆን " እኛ ሕግን መሠረት አድርገን ነው የጠየቅነው፣ ከሕግ አንጻር ጉዳዩ ተዘርዝሮ መታየት አለበት። እየጠየቅን ያለነው ፣ የማንነት ጥያቄያችን ምላሽ እንዲያገኝ ብቻ ሳይሆን፣ እስካሁን ለደረሰብን በደልም ካሳም ጭምር ነው " ሲሉ ገልጸው ነበር።

ከዚህ በተጫማሪ ፤ የወልቃይት እና አካባቢው ጉዳይ ከውይይት ውጭ በሆነ መንገድ ይፈታል ብለው እንደማያምኑ፤ ለአካባቢው ጦርነትና ግጭት መፍትሄ እንደማይሆንም አስገንዝበዋል።

በወልቃይት ጉዳይ ከትግራይ ክልል አስተዳደር ጋር ለመነጋገር ፍላጎት ያላቸው እንደሆነም ተጠይቀው ፤ " ጉዳያችን ሊያልቅ የሚችለው በመነጋገርና በመወያየት ብቻ ነው ፤ በጉልበት የሚያልቅ ነገር የለም። እኛ ብቻ አይደለንም መላው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ፣ መላው የአማራ ሕዝብ ሊነጋገር ይገባል እንዲሁም የትግራይ እና የአማራ ሕዝብም ተገናኝቶ መነጋገር ይገባዋል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተው ነበር።

@tikvahethiopia