" ... ወንዶች በትምህርት ሰአት ሁሉ የቀን ስራ በመስራት ርሀባቸውን ለማስታገስ በጥረት ላይ ሲሆኑ ሴቶችም ላልተገባ ችግር ተጋልጠዉ መማር አልቻሉም " - የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር አደረኩት ባለው ማጣራት በክልሉ ውስጥ ባሉት የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህራን ሁሉም በሚባል መልኩ ትምህርታቸውን በፋይናንስ እጥረት በአግባቡ እየተማሩ አይደለም።
ዕጩ መምህራን በ2015 ዓ/ም ወደ ኮሌጆች ሲገቡ ከመንግስት የሚሰጣቸዉ 450 ብር በቂ እንዳልሆነ እየታወቀ ቢጀመርም እስካሁን ሊስተካከልላቸው አልቻለም።
ይህን ችግር በተመለከተ ኮሌጆቹ በቦርድ ደረጃ ያመኑበት ከመሆኑ ባለፈ ማስተካከያ እንዲደረግ ለክልሉ መንግስት ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
ይሁንና የክልሉ መንግስት ለጥያቄው ተገቢ ምላሽ ባለመስጠቱ በክልሉ በተለያዬ ደረጃ የመምህራንነት ስልጠና ለመዉሰድ ወደኮሌጆች ገብተዉ በትምህርት ላይ የሚገኙ በርካታ ዕጩ መምህራን በችግር እየተጠበሱና ትምህርታቸዉን ትተዉ ወደመጡበት እየተመለሱ መሆናቸዉን የክልሉ መምህራን ማህበር አውቂያለሁ ብሏል።
የመምህራን ማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ አማኑኤል ጳዉሎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ፤ " ከነዚህ ተማሪዎች መካከል አብዛኛዉ ወንዶች በትምህርት ሰአት ሁሉ የቀን ስራ በመስራት ርሀባቸውን ለማስታገስ በጥረት ላይ ሲሆኑ ሴቶችም ላልተገባ ችግር ተጋልጠዉ መማር አልቻሉም " ብለዋል።
" በመሆኑም ተማሪዎች በ450 ብር በልተዉና ጠጥተዉ እንዲሁም ሌሎች ወጭዎችን ሸፍነዉ መማር አይችሉምና የክልሉ መንግስት በተለይም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ባስቸኳይ ችግራቸዉን ይፈታላቸዉ ዘንድ ማህበሩ በደብዳቤ ሁሉ ጠይቋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ስለምን ተማሪዎቹ በዚህ ልክ እስኪሰቃዩ ድረስ መፍትሄ አልተፈለገም ? በማለት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።
ምላሽ ሲሰጥ ምላሹን የምናካትት ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia

" እጆቼን ማዘዝ ችዬ እኔን ለማገዝ የሚደክሙትን ሁሉ ከድካማቸዉ ባሳርፋቸዉ ደስ ይለኝ ነበር " - ጠንካራው የይቅርታ ሰዉ ዳግማዊ አሰፋ (ዳጊ)
የህግ ባለሞያና ደራሲ ዳግማዊ አሰፋ ከዓመታት በፊት በሀዋሳ ከተማ በእሱ እና በጓደኛው እጅ ላይ ከነበረ የፍትህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ " ጉቦ አንቀበልም !! " በማለቱ በአንድ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መጎዳቱ ይታወሳል።
በዚህ አደጋ ጠንካራ የወጣት እጆቹ አልታዘዝልህ ብለዉታል። በአከርካሪዉ ዙሪያ ያሉ ነርቮች መጎዳትም ቆሞ እንዳይሄድ እንቅፋት ሆነዉበታል።
በዚህ ምክኒያት በሰው እጅ መብላቱ መልበሱ እና መንቀሳቀሱ ፈተና ቢሆንበትም ዛሬም ተስፋው ከሱ አልፎ ለሰዎች ይደርሳል።
ያልተሰበረው መንፈሱ የተሰበሩትን ይጠግናል ፤ ያልወደቀው ምራሉም የወደቁትን ያነሳል።
በዚህ ትጋቱ ያልተገታዉ ዳግማዊ ከህመሙ ጋር እየታገለ ስቃዩን እየተሰቃዬም ቢሆን አርፎ መቀመጥን አልወደደም ሁለት መጽሀፍት ለተደራሲያን አብቅቶ ለብዙዎች ህይዎት መቃናት ምክኒያት ሆኗል።
በዚህ ዓመትም ሌላ መጽሀፍ ሊያስመርቅ እየሰራ ነው። የቀደሙ ሁለቱ መጽሀፍትም በአፋን ኦሮሞ ታትመዉ ለመዉጣት ጫፍ መድረሳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ከምንም በላይ ለሰዎች መትረፍ ሲችል የሰዎችን ድጋፍ ይፈልግ ዘንድ ብርቱ ክንዶቹ ዝለው ስራዎቹን መከወን ያቅታቸው ዘንድ ምክኒያት የሆነውን ሰው " ይቅር ብየሀለሁ " ማለቱ ለትንንሽ ጥፋት ይቅርታ ማድረግ ለከበዳቸዉ ሁሉ ታላቅ ትምህርት የሰጠ ሰው ነው።
ጠንካራው ዳግማዊ ከሁለት ዓመት በፊት ውጭ ወጥቶ መታከም ከቻለ መዳን እንደሚችል ሀኪሞች ማብሰራቸውን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ ተደስተዉ ጎ ፈንድሚ ቢያቋቁሙም ወቅቱ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሀገራችን ችግር ላይ የነበረችበት ወቅት በመሆኑ እንዳስቆመው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።
" አሁን ላይ ' ጎፈንድሚውን እንጀምር ዘንድ ፈቃድህን ብቻ ስጠን 'ላሉኝ ጓደኞቼ ፈቃዴን ሰጥቻለሁ " ብሏል።
ድኖ ለብዙዎች መትረፍ ሲችል ' ሀገሬ ችግር ላይ ናት " ብሎ የዘገየዉ ዳግማዊ ምንም እንኳን ብዙ ችግሮቹን " ወዳጆቼን አላስጨንቅም " ብሎ ቢደብቅም በቶሎ መታከም እንዳለበት ግን አሁን ላይ ብዙ ምልክቶችን አሳይቷል።
ይህ ተከትሎም ሁሉም ደጋግ ኢትዮጵያውያን እገዛ እንዲያደርግለት ወዳጆቹ እየተረባረቡ ይገኛሉ።
ዳግማዊ ፥ " ' 2 ሺህ የፌስቡክ ጓደኞቻችን ሁለት ሁለት መቶ ሰው ይዘዉ የአንድ ማኪያቶ የሚሆን 57 ብር በማዉጣት ያሳክሙሀል ' ብሎ ወዳጄ መምህር ወሌ ሀሳቡን ጀምሮታል " ብሏል።
" ዳግማዊ ገንዘቡ ተሰብስቦልህ ታክመህ ስትድን በእጆችህ ቀድመህ ልትሰራ የምታስበዉ ምንድን ነው ? " በማለት የቲክቫህ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል ጥያቄ አቅርቧል።
ከረዥም ዝምታ በኋላ ፦
" አይገርምህም አስቤዉ አላዉቅም ... ግን እጆቼን ማዘዝ ችዬ እኔን ለማገዝ የሚደክሙትን ሁሉ ከድካማቸዉ ባሳርፋቸዉ ደስ ይለኝ ነበር። "
ዳግማዊ አሰፋን ማገዝ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያላችሁ ደጋግ ኢትዮጵያዉያን ፦
በጎፈንድሚ 👉 https://gofund.me/d93d0840
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 👉1000310977938
በዳሽን ባንክ 👉 5016527877077
በአቢሲንያ ባንክ 👉 39796821 በኩል ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።
ስልክ እንፈልጋለን ለምትሉም ፦ 0909888857 ላይ መደወል ትችላላችሁ።

TIKVAH-ETHIOPIA
“ ባለፈው ሳምንት ብቻ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት ” - ነዋሪዎች በኮሬ ዞን ፤ #በታጣቂዎች አማካኝነት ንጹሃን ላይ የሚደርስ ጥቃት በእርቀ ሰላም ተፈቶ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ከ4 ወራት ወዲህ በማገርሸቱ የንጹሐን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ እየተፈጸመ መሆኑን የዞኑ ባለስልጣትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥም ተጠይቋል። ባለስልጣናቱና ነዋሪዎቹ ለድርጊቱ የ " ኦነግ…
#ኮሬ
° " የንጹሀን ሞት ይቁም፤ገዳዮች ለፍትህ ይቅረቡልን !! " - የዳኖ ቀበሌ ነዋሪዎች
° " በግጭቱ ሁለት ሰዎች ሲጎዱ የአንደኛው ህይዎቱ አልፏል " - የኮሬ ዞን የሰላምና ጸጥታ ሀላፊዉ ተፈራ ቦንዶሮ
በኮሬ ዞን ፤ ዳኖ ቀበሌ ከትናንት ጀምሮ የደረሰ በቆሎ ታጥቀው በመጡ አካላት በመጨፍጨፉ ምክንያት በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት አልፏል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ይህ ድርጊት ታጥቀው ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላናና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ ቀበሌያት ወደ ኮሬ ዞን ዘልቀው በገቡ አካላት ነው የተፈጸመው ብለዋል።
እነዚሁ ታጣቂዎች " ከዚህ ቀደምም ከብቶች ሲነዱብን አርሶአደሮች ሲገደሉብን ቆይተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
በዚህ አመት ብቻ #ከ20_በላይ ሰዎች መሞታቸውን አስረድተዋል።
በመሆኑም " እነዚህን አካላት መንግስት አስታግሶ ለህግ / ለፍትህ ያቅርብልን ፤ የንጹሀን ሞት ይቁም ፤ ሰሚ በማጣታችን እሄዉ ዛሬም ግጭቱ ቀጥሏል " ብለዋል።
በአካባቢው ያለዉ ተኩስም የታጠቁ አካላትን ወሰን አልፈዉና ወደመንደሩ ተጠግተዉ የጀመሩት ነው ሲሉ አስረድተዋል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የኮሬ ዞን የሰላምና ጸጥታ ሀላፊዉ ተፈራ ቦንዶሮ ፥ (ቃላቸውን በሰጡበት ሰዓት / ከሰዓት ) አካባቢው ላይ ከባድ ተኩስ እንደነበር ገልጸዋል።
ግጭቱን ለማርገብ ርብርብ ላይ በመሆናቸዉ ምላሽ ለመስጠት አይመችም ቢሉም ቆይተዉ የተብራራ ምላሽ ሰጥተዋል።
ከምዕራብ ጉጂ ዞን የመጡ ታጣቂ ሀይሎች አካባቢው በመመንጠርና የበቆሎ ማሳዎችን በመጨፍጨፋቸው ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።
በግጭቱ አንድ ሰው #ሲሞት ፤ አንድ ሰው ቆስሏል ብለወል።
ግጭቱን በቀሰቀሱት በኩል የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የሚያዉቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው አሁን ላይ አካባቢዉ መረጋጋቱን ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለዘላቂ ሰላም ምን ታስቧል ? ሲል ጠይቋል።
እሳቸውም ፤ ከአካባቢው በተወሰነ ርቀት ላይ የሀገር መከላከያ ሀይሎች እንደሚኖሩና ከሚቆጣጠሩት ቦታ በተጨማሪ የታጠቁ ሀይሎች የሚመጡበትን መንገድ እንዲቆጣጠሩ ለመነጋገር ማሰባቸዉን ገልጸዉ ይህ ግን በመከላከያው ፈቃድና የስምሪት ሁኔታ የሚወሰን ነው ብለዋል።
ግጭቱ ያለበት የኮሬና ጉጂ ማህበረሰብ መሀከል በአካባቢዉ ባህል መሰረት የእርቅ ስርዓት በተደጋጋሚ ቢካሄድም ዕርቁ ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱን ለማወቅ ችለናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በምዕራብ ጉጂ ዞን በኩል ምላሽ ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካም ፤ ከዚህ ቀደምም ሙከራ ቢደረግም ምላሽ ሰጪ አልተገኘም። አሁንም ምላሽ አለኝ የሚል ምላሹን መስጠት ይችላል።