TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ?

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፤ በውስጡ ባለው #ሙስና እና ብለሹ አሰራሮች ምክንያት እጅግ በርካቶች ይማረሩበታል፤ በተደጋጋሚ ጊዜ የዚህ መስሪያ ቤት ጉዳይ ቢነገርም ችግሩ ግን ዛሬም ድረስ ሊቆም አልቻለም።

ዜጎች #በህጋዊ መንገድ ማግኘት ያለባቸውን አገልግሎት በሙስና ሰንሰለት በተጣመሩ አካላት ምክንያት ከፍተኛ ክፍያ እንዲከፍሉና ከሌሎች በፊታ ያለ አንዳች ወረፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል።

በዚህ መስሪያ  ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ የሚማረሩ፣ የሚበሳጩ እና እንግልት የደረሰባቸው በርካቶች ናቸው።

ከሰሞኑን ደግሞ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ (ኢቲቪ) አንድ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ ሰርቶ አየር ላይ አውሎ ነበር።

በዚህ የምርመራ ስራም በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ውስጥ ፦

-   በፓስፖርት እድሳት እና ከአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ዜጎች ለሕገ-ወጥ አሠራር ተጋላጭ ሆነዋል።

- በሕጋዊ መንገድ ከ6 ሺህ 500 ብር በታች በሆነ ወጪ መጨረስ የሚቻለውን ፓስፖርት እስከ 40 ሺህ ብር በመክፈል አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተረጋግጧል።

- ዜጎች መብታቸው ለሆነው አገልግሎት ሕገ-ወጥ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ ፤ ተቋሙ ባለበት አካባቢ እስከ ውስጥ ድረስ የተያያዘ የሙስና ሰንሰለት አለ።

ለመሆኑ ይህ ተቋም ይህን ሁሉ ችግሮች ለመቅረፍ ምን እያደረገ ነው ?

ቃላቸው ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሰጡት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙሉጌታ  ፦

" ከ33 በላይ የተቋሙ ሠራተኞች ላይ የሥነ -ምግባር እርምጃ ቢወስድም ዛሬም ግን በሙስና እና በብልሹ አሠራር እየተፈተንን ነው።

ዜጎች በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ቅሬታ ካላቸው ከቅሬታ ሰሚ ዴስክ አንሥቶ እስከ ተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ድረስ በመገናኘት ቅሬታቸውን ቢያሰሙ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን። 

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም 95 በመቶ የሚሆነው ከፓስፖርት ሕትመት ጋር ተያይዞ ያሉ ግብዓቶች ጭምር በሀገር ውስጥ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሥራዎች ተጠናቀዋል።

አገልግሎቱ እንዲጓደል የሚያደርጉ የተቋሙ ሠራተኞች በቅርብ በሚካሄድ የአደረጃጀት ሪፎርም ላይ ይጋለጣሉ እርምጃም ይወሰድባቸዋል። " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia