TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ ከጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር እንዲወያዩ የተሰየሙት ልዑካን ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) መግባታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ይህ ልዑክ የቀድሞውን የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ዮአኪም ቺሳኖ ፣ የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ሰርሊፍ ጆንሰንና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዝደንት የነበሩትን ጋሌማ ሞትላንቴ የያዘ ነው።

3ቱ የቀድሞ መሪዎች "ግጭቱ የሚያበቃበትን" መንገድ ለመወያየት ነው አዲስ አበባ የመጡት።

ልዑኩ ወደ አዲስ አበባ የገባው መንግስት የህግ ማስከበር እርምጃው ወደ #መጨረሻው ምዕራፍ ተሸጋግሯል ብሎ ባሳወቀበት ጊዜ ነው።

ዛሬ ጥዋት ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ በመቐለ የሚካሄደው የ3ኛው ምዕራፍ ኦፕሬሽን መጀመሩን አሳውቀዋል።

ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል ባለስልጣናት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሕግን ማስከበበር ስለሆነ ከህወሓት አመራሮች ጋር ምንም አይነት ድርድር ለማድረግ ፍላጎት እንደሌለ ከዚህ ቀደም መግለፃቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia