TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WOLAITA

በወላይታ ዞን በተከሰተው አለመረጋጋት በትንሹ ከ10 በላይ ሰዎች ሞተዋል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ኦቶና ሆስፒታል አባላት እንደገለፁት ደግሞ እስካሁን ባሉበት ሆስፒታል ብቻ ከ80 በላይ ሰዎች ተጎድተው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

ዛሬም በወላይታ ሶዶ እንዲሁም በሌሎችም ከተሞች 'የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት' እንደተዘጋ ነው። ከበርካታ የወላይታ ዞን የቲክቫህ አባላት ጋር መገናኘት አልቻልንም።

የወላይታ ሶዶ፣ አረካ፣ ቦዲቲ ቲክቫህ አባላት በስልክ ደውለው ያለውን ሁኔታ ያሳወቁ ሲሆን አሁንም የትንራስፖርት ፣ የንግድ እንቅስቃሴ የለም ፤ አንዳንድ ቦታ ውስጥ ለውስጥ አልፎ አልፎ ሱቆች ክፍት ናቸው ፣ ባንክ ቤቶች ዛሬም እንደተዘጉ ናቸው ፣ የሰዎች እንቅስቃሴ ግን ይታያል ካለፈው ቀን የተሻለ መረጋጋት አለ ብለዋል።

የየከተማው ነዋሪ በተፈጠረው ክስተት ክፉኛ ልቡ ተሰብሯል ፤ በዚህ ምክንያት እንደዋዛ ህይወታቸው በተቀጠፈውና በተጎዱት ወጣቶች ምክንያትም መሪር ሀዘን ላይ ይገኛል ብለዋል።

ከሶስቱም ከተሞች (ወ/ሶዶ፣አረካ፣ ቦዲቲ) የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ማረጋገጥ እንደቻልነው አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፀጥታ አስከባሪዎች መከላከያ ሰራዊትና የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Wolaita

ነገ ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ/ም በዎላይታ ዞን የድጋሜ ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ (ሪፈረንደም) ድምፅ አሰጣጥ ይካሄዳል።

ስለ ሪፈረንደሙ ምን እናውቃለን ?

- የመራጮች ምዝገባ እና የድምፅ መስጠት ሂደት በአንድ ቀን የሚደረግ ይሆናል።

- የቀረቡት ሁለት አማራጮች ናቸው። እነሱም ፦

ነጭ እርግብ ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #እንደግፋለሁ

ጎጆ ቤት ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #አልደግፍም

- ድምፅ መስጠት የሚጀመረው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ነው።

- በ1,812 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣል ፤ ለዚህም ዝግጅት ተደርጓል።

- ከአዲስ አበባ 5,215 ፤ ከዎላይታ ዞን 3,845 ተመልምለው በቦርዱ የሰለጠኑ አስፈፃሚዎች በምድብ ጣቢያዎቻቸው ላይ ይገኛሉ።

- ከነገ ድምፅ የመስጫ ቀን ጋር በተያያዘ በዞኑ በሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት ስራ አይኖርም።

- ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት #ዝግ ሆነው ይውላሉ።

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሆስፒታሎችን ጨምሮ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወ. ዘ. ተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን ይችላሉ። እንዲዘጉ አይገደዱም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ ይቀጥላል።

@tikvahethiopia