TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሊዝ #አዲስአበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መሬትን በሊዝ ለማስተላለፍ 2ኛ ዙር ጨረታ አውጥቷል። መሬትን በሊዝ የማስተላለፍ ተግባር ለአራት ዓመታት ከተቋረጠ በኋላ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ 2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታም ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም መውጣቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቢሮና ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ መረጃውን አግኝቷል። …
በአዲስ_አበባ_2ኛው_ዙር_የመሬት_ሊዝ_ጨረታ.pdf
5.3 MB
በአዲስ አበባ ከተማ የ2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ ፦
- በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
- በኮልፌ ቀራንዮ፣
- በአራዳ፣
- በአቃቂ ቃሊቲ፣
- በየካ፣
- በቦሌ፣
- በአዲስ ከተማ፣
- በቂርቆስ፣
- በጉለሌ
- በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

(ዝርዝር የጨረታው መረጃ በPDF ተያይዟል - ይመልከቱ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የጨረታ መረጃ ባለቤት አዲስ ልሳን መሆኑን ያሳውቃል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU #Fraud #CBE ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ #ከ6_ሚሊዮን_ዶላር_በላይ (367 ሚሊዮን ብር) ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ፍድር ቤት ቀርበውም ለፖሊስ ተጨማሪ ቀን ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ ንግድ…
" ከቤተክርስቲያን ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም " - መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፤ የቀሲስ በላይ መኮንን ጉዳይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም ብላለች።

" ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚገለግሉ ቢሆንም ተጭበርብሯል ከተባለው ሰነድ ጋር ግን ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም " ነው ያለችው።

የቀሲስ በላይን ጉዳይ በተመለከተ የመንበረ ፓቲሪያርክ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ክፍል ዋና ኃላፊ  መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

መምህር ዶ/ር አካለወልድ ፥ " ሊቀአዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር በዋሉበት ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የመከታተል ጥረት ላይ ትገኛለች " ብለዋል።

" እስካሁን በተደረገው ክትትል ግን በህግ ጥላ ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ እንደሌለና በግል ህይወታቸው ውስጥ የገጠማቸው ነገር እንደሆነ ነው የተረዳነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በቀጣይ ግን ጉዳዩ የቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር አለወይ ? ለሚለው በህግ ክፍል በኩል ማጣራት እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል አመልክተዋል።

ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ #ከ6_ሚሊዮን_ዶላር_በላይ (367 ሚሊዮን ብር የሚሆን) ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ሊዝ #አዲስአበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፤ በአራዳ ክፍለ ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ በ10 ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ የልማት ስራዎች የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ለ1 የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር መክፈል የግድ እንደሆነ ተነግሯል።

የጨረታው ሰነድ እስከ ሚያዚያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ እየተሸጠ እንደሚቆይም ታውቋል።

አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም ተብሏል። ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኘም ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል።

🔵 ከላይ ሙሉ የጨረታው ዝርዝር መረጃ የተያያዘ ሲሆን በአራዳ ክፍለ ከተማ ከተራ ቁጥር 5 - 13 ወረዳ 01 በሚል የተገለፁ ቦታዎች ትክክለኛ መገኛ " ወረዳ 05 " መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Humanity❤️

ይህ የሆነው በአሜሪካ ሀገር ሚኒሶታ ነው።

በሚኒሶታ በሚገኝ #ፈጣን_መንገድ ላይ አንድ አሽከርካሪ መንገድ ስቶ ወጥቶ ከመብራት ፖል ጋር ተጋጭቶ እዛው መኪና ውስጥ እያለ መኪናው በከፍተኛ እሳት መያያዝና መንደድ ይጀምራል።

በመንገዱ ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች ይህን አይተው አላለፉም።

መኪናቸውን አቁመው ከሚነደው መኪና ውስጥ አሽከርካሪውን ለማውጣትና ለማዳን ርብርብ ጀመሩ።

ከእሳት ነበልባል ጋር #እየታገሉ ፤ በሹፌሩ በር በኩል ያለውን መስታወት ሰብረው ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል በኃላ አሽከርካሪውን በእሳት ተያይዞ ከሚነደው መኪና ውስጥ በህይወት አወጡት።

በኃላም ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ።

አሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት የከፋ ጉዳት አልደረሰበትም ተብሏል።

ከከፍተኛ እሳት ጋር ተጋፍጠው የሰው ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ሲያደርጉ ከነበሩት አንዱ ከድር ቶላ ይባላል። (ጥቁር ጁንስ ሱሪ በነጭ ጫማ ያደረገው)

ወደ ስራ እየሄደ በነበረበት ሰዓት ነው ይህ ክስተት ያጋጠመው።

ከድር የነፍስ አድን ስራውን ፥ " በህይወቴ እጅግ በጣም አስፈሪው ቅጽበት ነበር። ይህንን መቼም ቢሆን አልረሳውም ሁሌም ቢሆን አስታውሰዋለሁ " ሲል አስረድቷል።

አሽከርካሪው በህይወት እንዲተርፍ ቦታው ላይ የነበሩ ሁሉም ሰዎች ላደረጉት ፍጹም #ሰብዓዊ ተግባርና ርብርብ ፈጣሪን አመስግኗል።

የነበረውን የህይወት አድን ርብርብ የሚያሳይ ቪድዮ ከድር ቶላ መኪና ላይ በነበረ የዳሽቦርድ ካሜራ የተቀረጸ ነው።

Video Credit : Kadir Tolla / ከድር ቶላ

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ እስከ 500 ሺህ ብር ድረስ ገንዘብ መላክ መቻሉ ብዙዎች ለንግድ ቅልጥፍና ሞባይል አፓችንን ተመራጭ አድርገውታል።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
#BankofAbyssina #mobilebanking #boamobile #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
በነፃ ማውጋት፣ በቴሌብር ሱፐርአፕ ተችሏል!

በዘመነው ቴሌብር ሱፐርአፕ ከግብይት፣ ገንዘብ እና የአየር ሰዓት መላላክ ባሻገር ቪዲዮ፣ ድምጽ፣ ፎቶ፣ ጽሁፍ እና ፋይሎችን በነጻ በመጋራት ማህበራዊ ግንኙነትዎን ያጠናክሩ፤ ቢዝነስዎን ያቀላጥፉ!

በቴሌብር ኢንጌጅ፣ የዲጂታል ህይወትዎን ያቅልሉ!

መተግበሪያውን ለማዘመን ወይም ለመጫን https://onelink.to/fpgu4m ይጠቀሙ፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 38 #ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸው አልፏል " - በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ #የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወታቸውን እንዳጡ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል። ትላንትና ሰኞ በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ " #ጎዶሪያ " በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስልሳ (60) ኢትዮጵያውያን…
" የ5 ሕፃናት እና ሴቶችን ሕይወት ጨምሮ 16 ዜጎቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል " - በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

በጀልባ መገልበጥ አደጋ #የ16_ኢትዮጵያውያን ሕይወት ሲጠፋ አብረው የተሳፈሩ 28 ዜጎችን እስካሁን ማግኘት አልተቻለም።

ትላንት ምሽቱን ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ " አራ " ከሚባል ስፍራ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ " ጎዶሪያ " በሚባል አካባቢ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ እስካሁን ድረስ የ5 ሕፃናት እና ሴቶችን ሕይወት ጨምሮ 16 ዜጎቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል።

እስካሁን አብረው ተሳፍረው የነበሩት ውስጥ 28 ፍልሰተኞችን ማግኘት እንዳልተቻለ እና 1 ሴትን ጨምሮ 33 ፍልሰተኞች በሕይወት ተርፈው ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው።

ከ2 ሳምንት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በደረሰ አደጋ የ38 ፍልሰተኛ ዜጎች ሕይወት አልፎ ነበር።

ከጅቡቲ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ህገ ወጥ ጉዞ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው የዜጎችን ሕይወት እያሳጣ እንደሆነ በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

በዚህም ዜጎች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለከፋ አደጋ እየዳረጉ ይገኛሉ ብሏል።

ዜጎች #በህገወጥ_ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ እና የፍትህ አካላትም ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ከገጠራማ የአገራችን አካባቢዎች ዜጎቻችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጓቸው ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
" ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው " - ህወሓት

ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድር እያደረገ ነው " የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ህወሓት ግን " ይህ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው " ብሏል።

ህወሓት ፥ " ከብልጽግና ጋር በተከታያይ እየተካሄደ ያለው ውይይት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው " ሲል ገልጿል።

ከብልጽግና ፓርቲ ጋር #መሰረታዊ የሆነ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳለው የገለጸው ህወሓት ፤ " ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች አሉ " ብሏል።

" ህወሓት ከብልጽግና ጋር ሊቀላቀል / ሊዋሃድ ንግግሮች ተጀምረዋል " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia