TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአዲስ አበባ ከተሞ ቦሌ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከቀናት በፊት መገደላቸው የተነገረው የፋኖ አባላት ወላጆች የልጆቻቸው አስከሬን እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ተናግረዋል። ይህ የተናገሩት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጡት ቃል ነው። ባለፈው ሳምንት አርብ ዕለት የተገደሉት ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው ከሞቱ አራተኛ…
#AddisAbaba

ከአንድ ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ሚሊኒያም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ኃይል ጋር በነበረው የተኩስ ልውውጥ ወቅት ሁለት " የፋኖ አባላት (አንድ አመራር እና አንድ አባል) " ፦
- ናሁሰናይ አንዳርጌ
- አቤነዘር ጋሻው መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል።

ከዛ በኃላ እናቶቻቸው በሀዘን ውስጥ ሆነው አስክሬን ለመውሰድ እንዳልቻሉና እላይ ታች እያሉ እንደሆነ ግን ምንም መፍትሄ እንዳላሀኙ ተነግሮ ነበር።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የቤተሰቡ አባል ፥ እስካሁን አስክሬን ለቤተሰብ እንዳልተጠ ተናግረዋል።

የናሁሰናይ አንዳርጌ እናት ወ/ሮ ሀረገወይን አዱኛ እና የአቤነዘር ጋሻው እናት ወ/ሮ ኤልሳ ሰለሞን የልጆቻቸውን አስክሬን ለመጠየቅ በየቦተው እየተንከራተቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

" እንድህ ያለው ክስተት በዓለም ላይ ያልተከሰተ እስኪመስል ድረስ ነው ከሀዘን በላይ ስቃይ ሆኗል። በጥዋት ጉዳይ አስፈጻሚ መስለው ነው የሁለቱ እናቶች የሚሄዱት አዲስ አበባ ፖሊስ ይሄዳሉ ' እኛን አይመለከትም ፌዴራል ነው ' ይባላሉ ፌዴራል ይሄዳሉ ' እኛን አይመለከትም ' ይባላሉ ከዛ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እዛ ጭራሽ የሚያናግራቸው የለም " ብለዋል።

" ማንም ሰብዓዊ ሰው ይሄን ይረዳል ብዬ አስባለሁ። ሰው ሞቶ አስክሬን የተከለከልን ብቸኛ ሰዎች እኛ ነን ብዬ ነው የማስበው አስክሬን ማየት እንኳን ተከልክለናል። " ሲሉ አክለዋል።

ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይሄ ጉዳይ የሚመለከተው የፀጥታ እና ደኅንነት ግብረ ኃይል ወይም የፌደራል ፖሊስን እንደሆነ መናገሩ ይታወሳል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ደግሞ ፥ " ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ነው " ማለቱ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ፥ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አስክሬን ለመጠየቅ የሄዱ ሁለት የቤተሰብ አባላት (ዳዊት መንግሥቱ እና ዳዊት መኮንን የተባሉ) መታሰራቸውን እኚሁ የቤተሰብ አባል ገልጸዋል።

" መንግሥት ከሚለው አይነት ነገር ጋር ምንም ግንኝኑት የላቸውም በግል ስራ ነው የሚተዳደሩት አክሬን ለመጠየቅ ሲሄዱ ነው ቤታቸው እንዲፈተሽ ተደርጎ በቁጥጥር ስር የዋሉት " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 4 አባቶች ተገድለዋል " - ቤተክርስቲያኗ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም " እራሱን ' ኦነግ ሸኔ ' ብሎ የሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ 4 አባቶችን ገድሏል " ሲል አሳወቀ። ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ 3 አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ…
#ዝቋላ

በወራት በፊት የጥንታዊው እና በታሪካዊው ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት  በግፍ መገደላቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግድያው በ " ሸኔ ታጣቂዎች " መፈፀሙን መግለጿም አይዘነጋም።

በወቅቱ አንድ የገዳሙ መነኩሴ ከሟቾቹ ጋር የነበሩ ዱካቸው መጥፋቱም ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል።

እኚሁ መነኩሴ ግድያውን ፈጽሟል ከተባለው ታጣቂ ቡድኑ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተደርሶባቸው በእስር ቤት እንዳሉ ተሳምቷል።

ይህ የተሰማው ከቀናት በፊት በመንግስታዊ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በዝቋላ ገዳም በታጣቂዎች ስለሚደርሰው ግፍን በተመለከተ በተሰራጨ አንድ ፕሮግራም ላይ የገዳሙ አባቶች ሲናገሩ ነው።

በወቅቱ ምን ሆነ ?

የካቲት 12 /2016 ዓ/ም ከገዳሙ ከተወሰዱት እና በኃላም ለምምክር ተብለው ከተጠሩት 5 መነኮሳት አንድ መነኩሴ ሳይገደሉ በህይወት ተርፈው ወደ ገዳሙ ተመልሰዋል።

አባ ገ/ኢየሱስ ፀጋዬ ፦

" መጀመሪያውኑ መረጃውን የሚሰጥ ከኛ ውስጥ አደራጅተዋል። እነሱ ናቸው የኛን እያንዳንዱን መረጃ የሚሰጧቸው።

ይሄን እኛ አናውቅም በወቅቱ ፤ አሁንም ቢሆን ሀገር መከላከያ መጥቶ መረጃው እንዲህ እንዲህ ነው ብሎ ስልካቸውን ጠልፎ ያለውን መረጃ ከእንቅስቃሴያቸው አኳያ ነው ያወጣልን እንጂ ውስጡን አናውቅም።

እንደኛው ቆብ ያደርጋሉ፤ መናኝ ናቸው።

እነሱ ተርፈው የመጡት አባት የምንጠራጠራቸው መከላከያው በትክክል መረጃ አግኝቶባቸዋል።

እሳቸው ወደ ማታ መጡ ተባሉ ግን የሸኛቸው ሸኔ ነው እስከ ግማሽ መንገድ ከመጡ በኃላ በራቸውን ዘግተው በውጭ አስቆልፈው ተቀምጠዋል።

ማታ 2 ሰዓት ላይ ሀገር መከላከያ ሰራዊት መጡ እኚያን በአስቸኳይ መያዝ ስለነበረባቸው የት ነው ያሉት አሉ ? ሄደው ከቤታቸው ሲፈለጉ ጠፉ በውጭ ተቆልፏል ከዛ በሩ ይሰበር ተብሎ በሩን መከላከያዎቹ ሰብረው አገኟቸው በቁጥጥር ስር አዋሏቸው።

ከዛ መከላከያው እኛን የማረጋጋት ስራ ነው የሰራው። እርግጠኛ ሆኜ ምናገረው በወቅቱ ሀገር መከላከያ ባይመጣ አናድርም ነበር።

አሁንም በየጫካው ተሰማርተው ጥበቃ እያደረጉ ነው። "

አባ ተ/መድህን ገ/መስቀል ፦

" ገንዘባችንን ፣ መሳሪያዎቻችንን በመውሰድ ባላቸው ሲስተም ከውስጣችንም ሳይቀር ከነሱ ጋር የተዋሃደ ኃይል ያለውን ንብረታችንን ሁሉ እስከማጣት ደርሰናል። መከላከያ ኃይል በመረጃ ነው ሊያወጣቸው የቻለው። "

ገረመው ይርጋ (የሉበን ጩቃላ ወረዳ ሚሊሻ) ፦

" ይሄን ሁሉ ሲያደርጉ ብቻቸውን አይደለም። የራሳቸውን ሰው ከቤተክርስቲያን ውስጥ አሰማርተው ይህ ስራ ሲሰራ ነበር። ከህዝቡም ከነዋሪው አደራጅተው ያንን ስራ ይሰራ ነበር።

መጨረሻ ላይ እነዛ አባቶች ታግተው ሄደው አባቶችም መስእዋትነት ከፈሉ።

እነዛም ተመሳጥረው የነበሩት በጣም አደገኛ የተባለው ተይዟል። በቁጥጥር ስር የዋሉም አሉ። "

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፤ " ድሮም የሚጎዳው የውስጥ አዋቂ ነው " ብለዋል።

" የቀረቡ መስለው ፣ አብረው የመነኑ መስለው ፣ አብረው ከገዳሙ ሰዎች ጋር በደባልነት በአስመሳይነት የሚኖሩ እንደነበሩ ጭላንጭሎች ነበሩ ይሄን ሁላችንም እናውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል።

በዚሁ በቀረበው ፕሮግራም ላይ የገዳሙ አባቶች ፥ ታጣቂዎቹ ከውስጥ ባላቸው ሰዎች አማካኝነት እያንዳድኑ ንብረት የት እንደሚቀመጥ በማወቅ በተደጋጋሚ ጊዜ ዝርፊያ ሲፈጽሙ እንደከረሙ ተናግረዋል።

ይህንን ለፀጥታ ኃይል ካሳወቁ ቤተክርስቲያኗን ጭምር በቦምብ እንደሚያወድሙ ሲዝቱ እንደነበር ገልጸዋል።

#ዝቋላገዳም2016

@tikvahethiopia
" ለኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጠትም ሆነ መቆጣጠር የሚመለከተው እኛ ነው " - የስራና ክህሎት ሚኒስቴር

ዜጎችን ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ፍቃድ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር ብቻ የተሰጠ ሃላፊነት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በዚህ ጉዳይ በሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጫ ዴስክ ሃላፊ አቶ ተክሌ ተስፉ ለመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

" አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ኤጀንሲዎች ሰዎችን ' ካናዳ እና ወደ ሌሎችም የውጭ ሀገራት ስራ እናስቀጥራችኃለን ' በሚል የሚያስተላለፉት ማስታወቂያ ፈጽሞ ፈቃድ የሌለው እና ህገ ወጥ ነው ' ብለዋል።

ይህን ስራ በሚሰሩት ላይ በጥቆማና በፍለጋ ሲደረስባቸው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ገልጸዋል።

" ለኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጠቱንም ሆነ መቆጣጠሩንም የሚመለከተው የመንግስት ተቋም ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በፌደራልም በክልልም ያሉ ኤጀንሲዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈቃድ ከተሰጣቸው ብቻ ስራው ላይ መሰማራት እንደሚችሉ አስገንዝበዋል።
                    
በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች እየተበራከቱ መጥተዋል ያሏቸው ህገ ወጥ ኤጀንሲዎችን በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀዋል።

ዜጎችን ያለ ፍቃድ " ወደ ውጭ እንልካለን " የሚሉ ህገ ወጦች ምንም አይነት እውቅና የሌላቸው መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲረዳው ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው (መናኸሪያ 99.1 ኤፍ ኤም) በሰጡት ቃል አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
#ግሎባል_ባንክ

መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ !

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ (3ኛ ዙር
)

1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://t.iss.one/global_bank_referral_bot?start=476862805
2. START የሚለውን ይጫኑ፣
3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
4. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
5. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
6. መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከአንድ ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡

ሽልማቱ በየሳምንቱ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነጻ የጥሪ ማዕከል ቁጥራችን 8118 ☎️ ይደውሉ፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን
" በእስልምና አስተምህሮ የአንድን ሰው ሕይወት ማዳን ዓለምን ማዳን ነው " - ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ

በአፋር እና በሶማሊ (ኢሳ) ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱ ተነግሯል።

ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አደራዳሪነት የተደረሰ መሆኑን ም/ቤቱ ገልጿል።

ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ለበርካታ ወራት ሲያወያዩ ሰላምን ለመፍጠር ሲመክሩ እንደነበር ተነግሯል።

በመጨረሻም ፥ በአፋር እና በኢሳ ማኅበረሰቦች መካከል የነበረውን የወንድማማቾች ደም መፋሰስ እንዲቆም የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ተደርሶ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጓል።

የጠቅላይ ም /ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን ፤ ስምምነቱ ውጤታማ እንዲሁን የሁለቱም ክልል መንግስታት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የነበረው ደም መፋሰስ " በምሥራቅ አፍሪካ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ በተደረገው ጥረት ሰላም እንዲሰፍን የሚያስችል ውጤት መገኘቱ ገልጸዋል።

በእስልምና አስተምህሮ የአንድን ሰው ሕይወት ማዳን ዓለምን ሁሉ ማዳን መሆኑን ገልጸው ፥ " በመነጋገር ችግሮችን የመፍታት አካሄድ የሰላም ችግር ባሉባቸው በሌሎችም የሀገራችን ክልሎች ሁሉ ሊተገበር ይገባል " ብለዋል።

#Peace🤍

@tikvahethiopia
የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
" ' በኃይል ይዣለሁ ፣ ይዣለሁ ማለቱ ፍጹም ሰላም አያመጣም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ፥ " በወረራ " ተይዘዋል ያሏቸውን የትግራይ ክልል ግዛቶችን በሰላም ስምምነቱ መሰረት ነጻ እንዲወጡ እና የአካባቢዎቹ ሰላምና ደህንነት ተረጋግጦ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ኃላፊነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት…
" ስጋት ፈጥሮብናል " - ኤምባሲዎቹ

ሰሞነኛውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኙት ፦
- የካናዳ፣
- የፈረንሳይ፣
- የጀርመን፣
- የጣሊያን፣
- የጃፓን፣
- የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ኤምባሲዎች የጋራ አጭር መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ " #አወዛጋቢ " በሆኑት አካባቢዎች ከሰሞኑን የተፈጠረው ግጭት " ስጋት ፈጥሮብናል " ብለዋል።

ሁሉም ወገኖች የታጣቂ ኃይሎች ትጥቅ ማስፈታት ፣ ብተና እና መልሶ ማቋቋም /#DDR / እንዲሁም ተፈናቃዮችን #በሰላም ወደ ነበሩበት መመለስ ላይ አበክረው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

" ውጥረቱ እንዲረግብ እና #ሰላማዊ_ሰዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን " ብለዋል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የተወሳሰቡ የፖለቲካና የጸጥታ ቀውሶችን ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት ማድረግ ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ስጋት ፈጥሮብናል " - ኤምባሲዎቹ ሰሞነኛውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኙት ፦ - የካናዳ፣ - የፈረንሳይ፣ - የጀርመን፣ - የጣሊያን፣ - የጃፓን፣ - የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ኤምባሲዎች የጋራ አጭር መግለጫ አውጥተዋል። በዚህም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ " #አወዛጋቢ " በሆኑት አካባቢዎች ከሰሞኑን የተፈጠረው ግጭት " ስጋት ፈጥሮብናል " ብለዋል። ሁሉም ወገኖች የታጣቂ…
#Raya #UNOCHA

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት 29,000 ሰዎች ከአላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ፦
° በቆቦ / በሰሜን ወሎ
° ሰቆጣ / በዋግኽምራ በሚገኙ መጠለያዎች መጠለላቸውን ገልጿል።

23,000 ሰዎች ወደ ቆቦ ሰሜን ወሎ እንዲሁም 5,980 ሰዎች ወደ ሰቆጣ ዋግኽምራ ዞን ነው የተፈናቀሉት።

በአካባቢው ያለው ሁኔታ ሲታይ የተፈናቃዮች ቁጥር ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።

ከተፈናቀሉት ዜጎች በዋነኝነት 70 በመቶዎቹ ህጻናትና ሴቶች ሲሆኑ ቀሩት ደግሞ አዛውንቶችና ታዳጊዎች ናቸው።

እንደ UN OCHA ሪፖርት ፦

🔘 ተፈናቃዮች ባሉበት ከበድ ያለ #የምግብ እና የውሃ እጥረት በመኖሩ አስቸኳይ የሆነ የህይወት አድን እርዳታ ያስፈልጋል።

🔘 ክፍት በሆኑ ቦታዎች ላይ የተጠለሉ ቤተሰቦች አስቸኳይ መጠለያ ያስፈልጋቸዋል።

ኦቻ ድጋፍ በሚያደርጉ #አጋር_አካላት የግብዓት እጥረት ምክንያት በጣም ተጋላጭ ለሆኑት የምግብ እና ውሃ ድጋፍ እየተደረገ ያለው መደበኛ ባልሆነ መንገድ በህብረተሰቡ ነው ብሏል።

ተጨማሪ ፦

🛑 እስከ ትላንት ድረስ በራያ አላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ አንዳንድ መጠነኛ #ግጭቶች መከሰታቸውን ቢቀጥልም በአላማጣ ፣ ቆቦ ፣ ወልዲያ ከተሞች የጸጥታ ሁኔታው ​የተረጋጋ ነው።

⭕️ በአላማጣ እና በቆቦ መካከል ያለው መንገድ ተከፍቶ የንግድ ትራንስፖርት የቀጠለ ሲሆን እንደ ባንኮች ያሉ የህዝብ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ ቀጥለዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ ናት።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከ2020 ጀምሮ ምንም ፈንድ ያላገኘችው ኢትዮጵያ ብድር እንዲለቀቅላት ከIMF ተከታታይ ድርድሮች እያካሄደች ነው።

ከIMF 3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደጠየቀች ተነግሯል።

ድርጅቱ ብደሩን ለመስጠት ኢትዮጵያ ብር ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም #እንዲዳከም ማድረግ እንዳለባት እንደጠየቀ ተጠቁሟል።

ግን ይህ እንደቅድመ ሁኔታ ይቀመጥ አይቀመጥ ድርጅቱ ማረጋገጫ አልሰጠም። ነገር ግን ተለዋዋጭ የሆነ የገበያ ሁኔታ የሚወስን የውጭ ምንዛሬ ተመን መኖር  እንዳለበት እንደሚያምን ሮይተርስ አስነብቧል።

ምንም እንኳን እየተካሄዱ ባሉ ተከታታይ ድርድሮች በኢትዮጵያ እና IMF መካከል ልዩነቶች ቢኖሩም ስምምነት ላይ የመድረስ #ተስፋ_እንዳለ የIMF የኢትዮጵያ ልዑክ አልቫሮ ፒርስ ተናግረዋል።

ፒስርስ ፥ " አሁንም ልዩነቶች ቢኖሩም ድርድር ግን ቀጥሏል። አስቸጋሪ ነግሮች ቢኖሩም ስምምነት ላይ የመድረሱ ተስፋ አለ " ብለዋል።

የኢትዮጵያን #የኢኮኖሚ_ሪፎርም_መደገፍ ላይ በአብዛኛው ስምምነት እንዳለ ነው የተሰማው።

ከዶላር አንጻር የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም ከፍተኛ በሆነ የዋጋ ንረት እየተፈተነች ላለችው ኢትዮጵያ ይበልጥ ፈተና ሊሆንባት ይችላል።

ግን ደግሞ IMF የግዴታ ያ ካልተደረገ ብድር አለቀም ካለ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ውጭ ምንዛሬ እጥረት ውስጥ የምትገኝ በመሆኑ ሌላ አማራጭ ላይኖራት ይችላል የሚሉ አሉ።

ከቀናት በፊት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ እና የብሄራዊ ባንክ ገዢው ማሞ ምህረቱ በተገኙበት ከIMF ኃላፊ ክሪስታሊያ ጆርጂያ ጋር ተገናኝተው መክረው ነበር።

ምክክሩ IMF በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሪፎርም በሚደግፍበት መንገድ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተጠቅሷል። ዝርዝር ጉዳዩ ግን አይታወቅም።

መረጃው የሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ ናት። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከ2020 ጀምሮ ምንም ፈንድ ያላገኘችው ኢትዮጵያ ብድር እንዲለቀቅላት ከIMF ተከታታይ ድርድሮች እያካሄደች ነው። ከIMF 3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደጠየቀች ተነግሯል። ድርጅቱ ብደሩን ለመስጠት ኢትዮጵያ ብር ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም #እንዲዳከም ማድረግ እንዳለባት…
#Ethiopia #IMF

ኢትዮጵያ ከIMF ብድር ለማግኘት የብርን የመግዛት አቅም ለማዳከም ትስማማለች ? ሌላ አማራጭ የለም ?

የምጣኔ ሃብቱ ባለሞያ አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል ፦

" devaluation የሚቀር አይመስለኝም። በምን ያህል ደረጃ devalue ይደረጋል የሚለው ጥያቄ ነው እንጂ devalue ሳይደረግ IMF / World Bank ገንዘብ ይሰጣል ብዬ እንደ ራሴ አልገምትም።

አማራጭ ፖሊስ በራሱ መጥፎ አልነበረም። ቅደም ተከተሉን አለማስተካከል ነው ትልቁ ስህተት። ለምሳሌ ከሌሎች መጀመር ይቻል ነበር።

liberalization ሊቀድም ይችል ነበር ከdevaluation ፤ liberalization ሲደረግ አዲስ ካፒታል ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ይቻላል።

በዚህ ሂደት ካፒታል / ዶላር ይገኝ ነበር። ይህ ደግሞ የዶላርም ይሁን የሌላ ውጪ አሳሳቢ አይሆንም ነበር። እዳንም መቀነስ ይቻላል። አሁን ግን እዳ ይጨምራል።

ለምሳሌ ፦ የዛሬ 7 ዓመት ለባቡር ወይም ለሌላ የተበደርነው ዶላር ቢኖር መንግሥት ይጠበቅበት የነበረው 22 ብር ቀረጥ ሰብስቦ ወደ 21 ዶላር ቀይሮ መስጠት ነበር አሁን 56 እና 57 ታክስ መሰብሰብ አለበት።

የኑሮው ውድነት ?

ካለንበት ችግር በመነሳት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም ቢወሰን በዋጋ ንረት ላይ በኑሮው መወደደ ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ከባድ ነው።

ብዙ ነገር imported inflation የሚባለው ነዳጅ 39 ብር ነበር አሁን ከ70 በላይ ሆኗል ፤ ማዳበሪያውም ፣ ስንዴውም ፣ መኪናውም በብዛት 21 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት እቃ ወደ ሀገር ይገባል 3 - 4 ቢሊዮን የሚገመት export ታደርጋለች ይሄ ልዩነት ላይ ያለው 17 ቢሊዮን ብር የሚመጣውን እቃ ዋጋ ሊጨምረው ይችላል። ይሄ በእያንዳንዱ ቦታ ተበታትኖ በየሰዉ ኑሮ ላይ ተፅእኖ ያደርጋል።

inflation አሁን ትንሽ ረገብ አለ ቢባልም ከፍተኛ ነው። እንደገና ከፍ ሊል ይችላል።

ካፒታል ያላቸው ሰዎች ምንም ችግር የለባቸውም። ለምሳሌ ነጋዴ እቃ ቢወደድም ቢረክስም ችግር የለበትም የገዛበት ላይ ጨምሮ ነው የሚሸጠው ምናልባት ብዙ ላይሸጥ ይችላል ያ ሊጎዳው ይችላል።

ቁርጥ ያለ ገቢ ያለው ሰው ሊጎዳ ይችላል። ለምሳሌ የዛሬ 7 ዓመት 22 ሺህ ብር ደመወዝ የሚከፈለው ሰው 1000 ዶላር አካባቢ ነው አሁን ግን 450 ነው የሚያገኘው ስለዚህ ደመወዙ 50% ቅናሽ አድርጓል። በሌላ በኩል የመኖሪያ፣ የምግብ ዋጋ ጨምሯል።

ብዙ አማራጭ ያለ አይመስለኝም ከ devalue አንጻር። ያለውን ብር መቀበል ነው። አልያም ብሩን አልፈልግም ብሎ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነው። ወይም የሚባለውን አድርጎ የሚያስከትለውን ችግር መፍትሄ መፈለግ ነው። "

ይህ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ አስተያየት የተወሰደው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይገልጻል።

@tikvahethiopia