TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EOTC #አሁን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ እየሰጠች ነው።

ቤተክርስቲያኗ ፤ ከሃያ (20) ዓመታት በላይ በጅማ የም ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የሚያገለግሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ዛሬ በጅማ ዞን  ፖሊስ ታስረው መዋላቸውን ገልጻ ድርጊቱን በፅኑ አውግዛለች።

በአሁኑ ሰዓት ሊቀ ጳጳሱ #በግዳጅ ከጅማ እንዲወጡ መገዳቸውን እና ከሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያን የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ጋር ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ መሆናቸውን ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ፤ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከክልል የተሰጠ ትዕዛዝ ነው በማለት በነገው እለት በጅማ የቅድስት ድንግል ማርያም ሕንጻ ቤተመቅደስ ቡራኬ ቤተክርስቲያን ሳያከናውኑ በፀጥታ ኃይሎች ወደ አዲስ አበባ  እንዲመለሱ የተገደዱት ብሏል።

በተጨማሪ ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ " በሕገ ወጥ ከተሾሙ አባቶች መካከል ይቅርታ ጠይቀው የተመለሱትና ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታቸውን የተቀበለው መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋዘአብ አዱኛ ከመንበረ ፓትርያርክ ማረፊያ ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል " ስትል ገልፃለች።

በመግለጫው መንግሥት ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀች ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ በሚገኙበት ግቢ አፈና መፈጸሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ ነው ብላለች።

#Update : መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ታፍነው ከተወሰዱበት ተለቅቀዋል።

@tikvahethiopia