TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረው ግለሰብ ተያዘ።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ሁለት ሺሕ #ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀል ችሎት አስታውቋል።

የቀድሞው የፖሊስ አባል፣ ፉልጌንሴ ካይሼማ፣ ፍ/ቤቱ በይፋ ክሥ ከመሠረተበት ካለፉት 22 ዓመታት ጀምሮ በሽሽት ላይ ነበር።

በተመድ የተቋቋመው ችሎት፣ ሥራውን ለሩዋንዳ በማስረከቡ፣ ካይሼማ፥ ለሩዋንዳ ተላልፎ እንደሚሰጥ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ካይሼማ ያለበትን ለሚጠቁም፣ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

ሌላው የዘር ማጥፋቱ ጠንሳሽ የተባለው ፌሊሲን ካቡጋ፣ ከ26 ዓመታት ሽሽት በኋላ ከሦስት ዓመት በፊት በፈረንሳይ ውስጥ መያዙ ይታወቃል።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ፣ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800ሺሕ የሚሆኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

#ቪኦኤ #ሩዋንዳ #Genocide

@tikvahethiopia
👍1.37K😢136105👎48🕊30😱20🙏20🥰15